መጠበቂያ ግንብ—የጥናት እትም ጥቅምት 2013

በዚህ እትም ላይ የፍጥረት ሥራዎች የፈጣሪን ኃይልና ጥብብ የሚገልጡት እንዴት እንደሆነ ይብራራል። በተጨማሪም ፍቅር ከተንጸባረቀበት የኢየሱስ ጸሎት ጋር ተስማምተን መኖር የምንችለው እንዴት እንደሆነ እንመረምራለን።

ራሳቸውን በፈቃደኝነት አቅርበዋል—ፊሊፒንስ

አንዳንዶች ሥራቸውን ለቅቀውና ንብረታቸውን ሸጠው በፊሊፒንስ ወደሚገኙ ራቅ ያሉ አካባቢዎች በመሄድ እንዲያገለግሉ ያነሳሳቸው ምን እንደሆነ እንድታነብብ እንጋብዝሃለን።

ፍጥረት ሕያው የሆነውን አምላክ ይገልጣል

ሌሎች ስለ ፈጣሪ እውነቱን እንዲያውቁ እንዲሁም በእሱ ላይ ጠንካራ እምነት እንዲኖራቸው መርዳት የምንችለው እንዴት እንደሆነ እንድታነብብ እንጋብዝሃለን።

“ይሖዋን እንደ ባሪያ አገልግሉ”

የሰይጣን ባሪያ ላለመሆን ምን ማድረግ ይኖርብናል? ይሖዋን እንደ ባሪያ በታማኝነት ማገልገል ምን በረከቶች ያስገኛል?

የሕይወት ታሪክ

በይሖዋ መታመናችን በረከት አስገኝቶልናል

ማልኮም አለን እና ግሬስ አለን እያንዳንዳቸው ከ75 ለሚበልጡ ዓመታት ይሖዋን አገልግለዋል። የእነሱን የሕይወት ታሪክ እንድታነብብና ይሖዋ በእሱ የሚታመኑ ሰዎችን የሚባርከው እንዴት እንደሆነ እንድትመለከት እንጋብዝሃለን።

በሚገባ ከታሰበበት ጸሎት የምናገኘው ትምህርት

ሌዋውያኑ ካቀረቡት ጸሎት ምን ትምህርት እናገኛለን? ጸሎታችን ይበልጥ ትርጉም ያለው እንዲሆን ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው?

ፍቅር ከተንጸባረቀበት የኢየሱስ ጸሎት ጋር ተስማምቶ መኖር

ኢየሱስ ጸሎት ሲያቀርብ የሚፈልገውን ነገር ከመለመኑ በፊት አስቀድሞ የጠቀሰው ከይሖዋ ፈቃድ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ነው። እሱ ካቀረበው ጸሎት ጋር በሚስማማ መንገድ መኖር የምንችለው እንዴት ነው?

ሰዎችን ለማስጠንቀቅ የበለጠ ጥረት ማድረግ ትችላለህ?

አንዳንዶች የዕለት ተዕለት ተግባራቸውን በሚያከናውኑበት ወቅት ለሚያገኟቸው ሰዎች በሙሉ ለመመሥከር አጋጣሚውን የተጠቀሙበት እንዴት እንደሆነ እንድታነብብ እንጋብዝሃለን።