መጠበቂያ ግንብ—የጥናት እትም ግንቦት 2013

ይህ እትም የወንጌላዊነት ተልእኳችንን መወጣት የምንችለው እንዴት እንደሆነ ያብራራል፤ በተጨማሪም በቤተሰብ ውስጥ ጥሩ የሐሳብ ልውውጥ ለማድረግ የሚረዱንን ባሕርያት ይገልጻል።

ወንጌላዊ እንደመሆናችሁ መጠን ያለባችሁን ኃላፊነት ተወጡ

በዛሬው ጊዜ ሰዎች ምሥራቹን መስማታቸው አንገብጋቢ የሆነው ለምንድን ነው? የወንጌላዊነት ኃላፊነታችንን በተሳካ ሁኔታ መወጣት የምንችለውስ እንዴት ነው?

‘ለመልካም ሥራ ትቀናላችሁ?’

ይህ ርዕስ በቅንዓት የምናከናውነው የስብከቱ ሥራችንና መልካም ምግባራችን ሰዎች ወደ አምላክ እንዲሳቡ የሚያደርገው እንዴት እንደሆነ ያብራራል።

የአንባቢያን ጥያቄዎች

በጥንት ጊዜ የነበሩ በርካታ ብሔራት አንዳንድ ወንጀለኞችን ግንድ ወይም ምሰሶ ላይ በመስቀል በሞት ይቀጡ ነበር። በጥንቱ የእስራኤል ብሔር ውስጥስ ምን ይደረግ ነበር?

ጥሩ የሐሳብ ልውውጥ በማድረግ ትዳራችሁን አጠናክሩ

ጥሩ የሐሳብ ልውውጥ ደስታ ለሰፈነበት ትዳር ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረክታል። ይህ ርዕስ ጥሩ የሐሳብ ልውውጥ ለማድረግ የሚረዱ ባሕርያትን ይገልጻል።

ወላጆችና ልጆች—በፍቅር የሐሳብ ልውውጥ አድርጉ

ጥሩ የሐሳብ ልውውጥ እንዳይኖር እንቅፋት የሚሆኑት አንዳንድ ነገሮች ምንድን ናቸው? እንቅፋቶቹን እንዴት ማሸነፍ ይቻላል?

የሕይወት ታሪክ

ሕይወታችን ዓላማ ያለው ሊሆን የቻለው እንዴት ነው?

ፓትሪሻ ሁለት ልጆቿ እምብዛም የማያጋጥም በጂን ውስጥ በሚፈጠር እክል ሳቢያ የሚከሰት በሽታ ይዟቸዋል። አስቸጋሪ ሁኔታዎች ቢያጋጥሟቸውም ዓላማ ያለው ሕይወት መኖር የቻሉት እንዴት እንደሆነ እንድታነብ እንጋብዝሃለን።

ጥበብ የተሞላበት ምርጫ በማድረግ ውርሻችሁን አጥብቃችሁ ያዙ

ክርስቲያኖች ምን ዓይነት መንፈሳዊ ውርሻ ተዘጋጅቶላቸዋል? ማስጠንቀቂያ ከያዘው የዔሳው ምሳሌ ምን ትምህርት ማግኘት እንችላለን?

ከታሪክ ማኅደራችን

‘በፈተና ሰዓት’ በአቋማቸው ጸንተዋል

አንደኛው የዓለም ጦርነት በ1914 ሲፈነዳ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች የሚከተሉት የገለልተኝነት አቋም በይፋ የታወቀው እንዴት እንደሆነ እንድታነብ እንጋብዝሃለን።