በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ታስታውሳለህ?

ታስታውሳለህ?

 ታስታውሳለህ?

በቅርቡ የወጡትን የመጠበቂያ ግንብ እትሞች በማንበብ ተጠቅመሃል? እስቲ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

• ስለ አምላክና ስለ ዓላማዎቹ የሚናገረውን እውነት ማለትም ‘ንጹሑን ቋንቋ’ አጥርተን መናገር የምንችለው እንዴት ነው? (ሶፎ. 3:9 NW)

እንደማንኛውም ቋንቋ ሁሉ ‘ንጹሑን ቋንቋ’ አጥርተን ለመናገርም በጥሞና ማዳመጥ፣ ቋንቋውን አጥርተው የሚናገሩ ሰዎችን መኮረጅ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ መጻሕፍትን ስሞች እንዲሁም አንዳንድ ጥቅሶችን በቃላችን ማጥናት፣ የተማርናቸውን ነገሮች መደጋገም፣ ጮክ ብለን ማንበብ፣ የቋንቋውን ሰዋስው ወይም የእውነትን ንድፍ ማጥናት፣ እድገት ለማድረግ መጣር፣ የጥናት ጊዜ መመደብ እንዲሁም ንጹሑን ቋንቋ አዘውትረን ‘መናገር’ ያስፈልገናል።—8/15 ገጽ 21-25

• አምላክን ማወቅ ሲባል ምን ማለት ነው?

የአምላክ ስም “ይሖዋ” ሲሆን ይህንን ስሙን እንድናውቅ ይፈልጋል። (ዘፀ. 6:3 የ1879 ትርጉም) ይሖዋ ‘የፍቅርና የሰላም አምላክ’ ነው። (2 ቆሮ. 13:11) ‘ሁሉን የሚያውቅ’ ከመሆኑም ሌላ ‘አዳኝ’ የሆነ አምላክ ነው። (1 ሳሙ. 2:3 የ1980 ትርጉም፤ መዝ. 25:5) አምላክ እሱን ወደሚያውቁት ሰዎች ይቀርባል።—9/1 ገጽ 4-7

• “በሦስት የተገመደ ገመድ” የሚለው ሐሳብ ከትዳር ጋር በተያያዘ ሊሠራ የሚችለው እንዴት ነው?

“በሦስት የተገመደ ገመድ” የሚለው አገላለጽ ምሳሌያዊ ነው። (መክ. 4:12) ይህን አገላለጽ ወደ ትዳር ስናመጣው በሁለት ክሮች የተወከሉት ባልና ሚስት፣ መሃል ላይ በሚገኝ ሌላ ክር ማለትም በይሖዋ አምላክ አማካኝነት አንድ ላይ እንደተጣመሩ ወይም እንደተገመዱ ያሳያል። ባልና ሚስት ከአምላክ ጋር መጣመራቸው ችግሮችን ለመቋቋምና ደስተኛ ለመሆን የሚያስችል መንፈሳዊ ጥንካሬ ይሰጣቸዋል።—9/15 ገጽ 16

በዕብራውያን 6:2 ላይ የተገለጸው ‘እጆችን መጫን’ ምን ያመለክታል?

በዚህ ጥቅስ ላይ የተገለጸው እጆችን መጫን፣ ክርስቲያን ሽማግሌዎችን መሾምን ሳይሆን የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎችን ማስተላለፍን የሚያመለክት ይመስላል። (ሥራ 8:14-17፤ 19:6)—9/15 ገጽ 32

• አንድ ጥሩ አባት ልጆቹ ከእሱ የትኞቹን ነገሮች እንደሚፈልጉ መገንዘብ ይኖርበታል?

ልጆች ከሚያስፈልጓቸው ነገሮች መካከል (1) የአባታቸው ፍቅር፣ (2) ጥሩ ምሳሌ የሚሆናቸው ሰው፣ (3) ደስታ የሰፈነበት የቤተሰብ ሕይወት፣ (4) መንፈሳዊ ነገሮችን መማር፣ (5) ተግሣጽ እንዲሁም (6) ጥበቃ ይገኙበታል።—10/1 ገጽ 18-21

• የበላይ ተመልካቾች ለሌሎች አክብሮት ማሳየት የሚችሉት እንዴት ነው?

አንድ የጉባኤ ሽማግሌ ይህንን ማድረግ ከሚችልባቸው መንገዶች አንዱ፣ እሱ ራሱ ሊያደርገው የማይፈልገውን ነገር ሌሎች እንዲያደርጉ ፈጽሞ ባለመጠየቅ ነው። ከዚህም በተጨማሪ ሌሎች እንዲሠሩ ለሚጠይቃቸው ነገሮችም ሆነ ለሚሰጣቸው መመሪያዎች ምክንያቱን በመናገር እንደሚያከብራቸው ያሳያል።—10/15 ገጽ 22

• የጋብቻ ቃል ኪዳንን አክብሮ ለመኖር የሚረዱ አንዳንድ ነጥቦች የትኞቹ ናቸው?

የጋብቻ ቃል ኪዳንን አክብሮ ለመኖር ከሚረዱት ነጥቦች ሁለቱ፦ (1) ለትዳርህ ቅድሚያ መስጠት እና (2) ለትዳርህ ያለህን ታማኝነት እንድታጓድል ከሚያደርግ ከማንኛውም ነገር መራቅ ናቸው። ትዳርህ ሰላም የሰፈነበትም ይሁን ችግር ያለበት ባለቤትህ ትዳራችሁን የተሳካ ለማድረግ ጠንክረህ እንደምትሠራ ሊሰማት ይገባል፤ እነዚህ ሁለት ነጥቦች ይህን ለማድረግ ይረዱሃል።—11/1 ገጽ 18-21

• አንድ ክርስቲያን ሽማግሌ፣ በጥንቷ እስራኤል የሚኖር እረኛ በቆልማማ በትር ይጠቀም ከነበረበት መንገድ ምን ትምህርት ማግኘት ይችላል?

በጥንቷ እስራኤል የሚኖር አንድ እረኛ መንጋውን ለመምራት ረጅም ቆልማማ በትር ወይም ከዘራ ይጠቀም ነበር። በጎቹ ወደ ጉረኗቸው ሲገቡ ወይም ከዚያ ሲወጡ እረኛው ‘ከበትሩ በታች’ እንዲያልፉ በማድረግ ይቆጥራቸዋል። (ዘሌ. 27:32) አንድ ክርስቲያን እረኛም በተመሳሳይ በእሱ ጥበቃ ሥር ባለው የአምላክ መንጋ ውስጥ የሚገኘውን እያንዳንዱን በግ በሚገባ ሊያውቅና ያለበትን ሁኔታ ሊከታተል ይገባል።—11/15 ገጽ 9

• አንዲት እናት ለንጽሕና ከፍተኛ ቦታ እንደምትሰጥ የምታሳየው እንዴት ነው?

ምግብ በተለያዩ መንገዶች ሊበከል ስለሚችል ምግብ ከመንካቷ በፊት እጆቿን በሚገባ የምትታጠብ ከመሆኑም በላይ ሸፍና ታስቀምጠዋለች። ቤቱን በንጽሕና በመያዝ አይጦችና ነፍሳት እንዳይኖሩ ታደርጋለች። ልብስን ማጠብ እንዲሁም ሰውነትንና እጅን አዘውትሮ መታጠብም አስፈላጊ ነው። መጽሐፍ ቅዱስም እንዲህ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ያሳያል።—12/1 ገጽ 9-11