በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ | በቤት ውስጥ ሰላም እንዲሰፍን ማድረግ

በቤተሰብ መካከል ሰላም ማስፈን የሚቻልበት መንገድ

በቤተሰብ መካከል ሰላም ማስፈን የሚቻልበት መንገድ

መጽሐፍ ቅዱስ በቤት ውስጥ ሰላም ለማስፈን ሊረዳ ይችላል? መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረውን ነገር ቀጥሎ የተጠቀሱት ሰዎች ከተናገሩት ጠቃሚ ሐሳብ ጋር እንድታወዳድሩ እንጋብዛችኋለን። ግጭትን ለማስወገድ፣ ሰላም እንዲሰፍን ለማድረግ እንዲሁም ዘላቂ ትስስር ለመፍጠር የሚረዷችሁን ነጥቦች ለማግኘት ሞክሩ።

ሰላም ለማስፈን የሚረዱ የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያዎች

አንዳችሁ ለሌላው ጥሩ አመለካከት አዳብሩ።

“ሌሎች ከእናንተ እንደሚበልጡ በትሕትና አስቡ እንጂ በጠበኝነት መንፈስ ወይም በትምክህተኝነት ምንም ነገር አታድርጉ፤ ስለ ራሳችሁ ፍላጎት ብቻ ከማሰብ ይልቅ እያንዳንዳችሁ ለሌሎች ሰዎች ፍላጎትም ትኩረት ስጡ።”ፊልጵስዩስ 2:3, 4

“የትዳር ጓደኛችንን ከራሳችንም ሆነ ከሌሎች አስበልጠን መመልከት ጥሩ እንደሆነ ተገንዝበናል።”—ሲ. ፒ. ለ19 ዓመታት በትዳር የኖረች

አፍራሽ አስተሳሰብ ሳትይዙ በጥሞና አዳምጡ።

“ጠበኞች እንዳይሆኑ ከዚህ ይልቅ ምክንያታዊ እንዲሆኑና ለሰው ሁሉ ገርነትን በተሟላ ሁኔታ እንዲያንጸባርቁ አሳስባቸው።”ቲቶ 3:2

“የትዳር ጓደኛችንን በሚያበሳጭ መንገድ ከማናገር መቆጠባችን በመካከላችን ውጥረት እንዳይፈጠር ይረዳል። በተናገረው ሐሳብ ባንስማማም እንኳ ጭፍን ሳንሆን ማዳመጣችንና አመለካከቱን ማክበራችን አስፈላጊ ነው።”—ፒ. ፒ. ለ20 ዓመታት በትዳር የኖረች

ታጋሽና ገር ሁኑ።

“በትዕግሥት አዛዥን ማሸነፍ ይቻላል፤ ለስላሳም [“የገራም፣” የ1954 ትርጉም] አንደበት አጥንትን ይሰብራል።”ምሳሌ 25:15

“ግጭት መፈጠሩ አይቀርም፤ ሆኖም ውጤቱ የተመካው በምናሳየው ባሕርይ ላይ ነው። ምንጊዜም ታጋሾች መሆን አለብን። ምክንያቱም ታጋሽ ከሆንን ችግሮቹን መፍታት እንችላለን።”—ጂ. ኤ. ለ27 ዓመታት በትዳር የኖረች

ጎጂ ቃላትም ሆነ አካላዊ ጥቃት አትሰንዝሩ።

“ቁጣን፣ ንዴትን፣ ክፋትንና ስድብን ሁሉ ከእናንተ አስወግዱ፤ ጸያፍ ንግግርም ከአፋችሁ አይውጣ።”ቆላስይስ 3:8

“ባለቤቴ ራሱን የሚቆጣጠር በመሆኑ አደንቀዋለሁ። ሁልጊዜ የተረጋጋ ሲሆን ጮኾብኝም ሆነ ሰድቦኝ አያውቅም።”—ቢ. ዲ. ለ20 ዓመታት በትዳር የኖረች

ይቅርታ ለማድረግና አለመግባባቶችን ለመፍታት ፈጣን ሁኑ።

“አንዱ በሌላው ላይ ቅር የተሰኘበት ነገር ቢኖረው እንኳ እርስ በርስ መቻቻላችሁንና በነፃ ይቅር መባባላችሁን ቀጥሉ።”ቆላስይስ 3:13

“ውጥረት ውስጥ ስትሆኑ መረጋጋት ቀላል አይደለም፤ ሳታስቡት የትዳር ጓደኛችሁን የሚጎዳ ነገር ልትናገሩ ወይም ልታደርጉ ትችላላችሁ። እንዲህ ያለ ሁኔታ ሲገጥማችሁ ይቅር መባባል በጣም ጠቃሚ ነው። ይቅር የማትባባሉ ከሆነ ትዳራችሁ ሊሰምር አይችልም።”—ኤ. ቢ. ለ34 ዓመታት በትዳር የኖረች

በልግስና የመስጠትና ያላችሁን የማካፈል ልማድ ይኑራችሁ።

“ለሰዎች ስጡ፤ እነሱም ይሰጧችኋል። . . . በምትሰፍሩበት መስፈሪያ መልሰው ይሰፍሩላችኋልና።”—ሉቃስ 6:38

“ባለቤቴ ምን እንደሚያስደስተኝ ስለሚያውቅ ሁሌ ያልጠበቅኳቸውን ነገሮች ያደርግልኛል። እኔም እንዴት ላስደስተው እንደምችል አስባለሁ። በዚህም የተነሳ አሁንም ድረስ በጣም ደስተኞች ነን።”—ኤች. ኬ. ለ44 ዓመታት በትዳር የኖረች

ሰላም ለማስፈን የምታደርጉትን ጥረት አታቋርጡ

ንቁ! ቃለ መጠይቅ ያደረገላቸው ሰዎች፣ በመጽሐፍ ቅዱስ እርዳታ ተጠቅመው በቤተሰባቸው ውስጥ ሰላም እንዲሰፍን የሚረዱ ባሕርያትን ካዳበሩ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች መካከል ጥቂቶቹ ብቻ ናቸው። * እነዚህ ሰዎች፣ ከቤተሰባቸው አባላት መካከል አንዳንዶቹ ሰላማዊ ለመሆን ጥረት ባያደርጉም እንኳ ሰላም ፈጣሪ መሆን እንደሚክስ ተገንዝበዋል፤ ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ “ሰላምን የሚያራምዱ . . . ደስተኞች ናቸው” ይላል።—ምሳሌ 12:20

^ አን.24 የቤተሰብን ሕይወት አስደሳች ማድረግ የሚቻለው እንዴት እንደሆነ የሚገልጽ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጀውን ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? የተባለውን መጽሐፍ ምዕራፍ 14 ተመልከት፤ መጽሐፉ www.jw.org/am ላይም ይገኛል። በተጨማሪም የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች > ለቤተሰብ በሚለው ሥር የወጡ ርዕሶችን ተመልከት።