በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ንድፍ አውጪ አለው?

የፎቱርየስ አብሪ ጥንዚዛ መብራት

የፎቱርየስ አብሪ ጥንዚዛ መብራት

ፎቱርየስ የምትባለው አብሪ ጥንዚዛ ዝርያ መብራት ወይም ብርሃን የሚያመነጨው የሰውነቷ ክፍል፣ ተደራርበው በተቀመጡ ቅርፊቶች የተሸፈነ ነው፤ ይህ ሽፋን ጥንዚዛዋ የምታመነጨው ብርሃን ይበልጥ ደምቆ እንዲታይ ያደርጋል። *

ተደራርበው የተቀመጡ ቅርፊቶች

እስቲ የሚከተለውን አስብ፦ ተመራማሪዎች በአንዳንድ የአብሪ ጥንዚዛዎች መብራት ላይ የሚገኙት ትናንሽ ቅርፊቶች ተደራርበው የተቀመጡ እንደሆኑ አስተውለዋል፤ እነዚህ ቅርፊቶች ልክ ጣሪያ ሲሠራ እንደሚደረገው አንዱ በአንዱ ላይ የተደራረቡ ናቸው። ቅርፊቶቹ በአንደኛው ጫፍ በኩል 3 ማይክሮ ሜትር (ከሰው ፀጉር ውፍረት አንድ ሃያኛ ያህል ያነሰ) ያህል ቀና ይላሉ። ቅርፊቶቹ በዚህ መጠን ቀና ያሉ መሆናቸው መብራቱ ይበልጥ ደምቆ እንዲታይ ያደርጋል፤ ቅርፊቶቹ በዚህ መንገድ መቀመጣቸው፣ የመብራቱ ድምቀት ይህ ባይሆን ኖሮ ከሚኖረው ድምቀት በ50 በመቶ ገደማ እንዲጨምር አድርጓል!

ይህ ሐሳብ በኤሌክትሮኒክ መሣሪያዎች ላይ የሚገጠሙት ብርሃን አመንጪ ዳዮዶች ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆኑ ለማድረግ ያስችል ይሆን? ይህን ለማወቅ የሳይንስ ሊቃውንት፣ ብርሃን አመንጪ ዳዮዶችን የአብሪ ጥንዚዛ መብራት ላይ ያለውን ቅርፊት በሚመስል የተደራረበ ነገር ሸፈኗቸው። ውጤቱስ? ከብርሃን አመንጪ ዳዮዶቹ የሚወጣው ብርሃን ከበፊቱ በ55 በመቶ የሚበልጥ ሆነ! አኒክ ቤይ የተባሉ የፊዚክስ ሊቅ “ከዚህ ሙከራ የተገኘው ትልቅ ውጤት፣ ተፈጥሮን በጥንቃቄ በመመልከት ምን ያህል ትምህርት ልናገኝ የምንችል መሆኑን ማሳየቱ ነው” ብለዋል።

ታዲያ ምን ይመስልሃል? የፎቱርየስ አብሪ ጥንዚዛ መብራት በዝግመተ ለውጥ የተገኘ ነው? ወይስ ንድፍ አውጪ አለው?

^ አን.3 የሳይንስ ሊቃውንት የዚህችን ጥንዚዛ ዝርያዎች በሙሉ አጥንተው አልጨረሱም።