ንቁ! ኅዳር 2013 | የሥነ ምግባር እሴቶች—ለተሻለ ሕይወት

የምንመራባቸው የሥነ ምግባር እሴቶች በሕይወታችን ውስጥ ቅድሚያ በምንሰጣቸው ነገሮች ላይ እንዲሁም ከሌሎች ጋር ባለን ግንኙነትና ለልጆቻችን በምናስተላልፈው የሥነ ምግባር መመሪያ ላይ ተጽዕኖ ያሳድራሉ። የተሻለ ሕይወት እንዲኖረን ከሚረዱት የመጽሐፍ ቅዱስ የሥነ ምግባር እሴቶች መካከል 4ቱን እንድትመረምር እንጋብዝሃለን።

ከዓለም አካባቢ

ከርዕሰ ጉዳዮቹ መካከል፦ በጀርመን የቤተ ክርስቲያን ግብር፣ ማመስገን በአእምሮ ላይ የሚያመጣው ለውጥ እና “ከሃይማኖት ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት እንደሌላቸው” የሚናገሩ ሰዎች ቁጥር በዓለም ዙሪያ መጨመር።

ለቤተሰብ

ስለ ሴክስቲንግ ከልጃችሁ ጋር መነጋገር የምትችሉት እንዴት ነው?

ችግሩ በልጃችሁ ላይ እስኪደርስ ድረስ አትጠብቁ። ሴክስቲንግ ስላለው አደጋ ከልጃችሁ ጋር ተወያዩ።

የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ

የሥነ ምግባር እሴቶች—ለተሻለ ሕይወት

የብዙዎች አመለካከት “ትክክል መስሎ ከተሰማህ አድርገው። ልብህ የሚልህን አዳምጥ” የሚል ነው። እንዲህ ያለው አስተሳሰብ ጥበብ ነው? በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙ ልትተማመንባቸው የምትችላቸው የሥነ ምግባር እሴቶች የትኞቹ እንደሆነ ለማወቅ ይህን ርዕስ እንድታነብ እንጋብዝሃለን።

ቃለ ምልልስ

ታዋቂ የፒያኖ ተጫዋች ስለሚያምንበት ነገር ምን ይላል?

ቀደም ሲል አምላክ የለሽ የነበረው ይህ ሰው ሙዚቃ፣ በፈጣሪ መኖር እንዲያምን አድርጎታል። መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክ ቃል ነው ብሎ ሊያምን የቻለው እንዴት ነው?

ማረጥ የሚያስከትላቸውን አስቸጋሪ ሁኔታዎች መቋቋም

አንቺም ሆንሽ በዙሪያሽ ያሉ ሰዎች ስለ ማረጥ ይበልጥ ባወቃችሁ መጠን ከዚህ ሁኔታ ጋር ተያይዘው የሚመጡ አስቸጋሪ ሁኔታዎችን ለመቋቋም ይበልጥ ዝግጁ ትሆናላችሁ።

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

ጋብቻ

አንድ ባልና ሚስት አምላክ የሰጣቸውን ድርሻ መወጣታቸው ስኬታማና ደስተኛ እንዲሆኑ የሚረዳቸው እንዴት እንደሆነ ማወቅ ትፈልጋለህ?

‘ሁልጊዜ ግብዣ’ ላይ ነህ?

ችግሮች ቢያጋጥሙህም አዎንታዊ በሆኑ ነገሮች ላይ በማተኮር ደስታህን ጠብቀህ መኖር የምትችለው እንዴት እንደሆነ ከምንባቡ እንድትረዳህ እንጋብዝሃለን።

በተጨማሪም . . .

ስለ መልኬ ከልክ በላይ እየተጨነቅሁ ነው?

መልክሽን የማትወጂው ከሆነ፣ ሚዛናዊ አመለካከት ማዳበር የምትችዪው እንዴት ነው?

የጤና ችግር ቢኖርብኝ ምን ላድርግ? (ክፍል 1)

አራት ወጣቶች ያለባቸውን የጤና ችግር ለመቋቋምና አዎንታዊ አመለካከት ለመያዝ የረዳቸው ምን እንደሆነ ተናግረዋል።

ሰውነቴን የምቆርጠው ለምንድን ነው?

ብዙ ወጣቶች፣ በሰውነታቸው ላይ ጉዳት የማድረስ ችግር አለባቸው። አንቺም እንዲህ ዓይነት ችግር ካለብሽ፣ እርዳታ ማግኘት የምትችዪው እንዴት ነው?

ወጣቶች፣ ዛሬ ነገ ስለ ማለት ምን ይላሉ?

ዛሬ ነገ ማለት ስለሚያስከትላቸው ጉዳቶችና ጊዜን በአግባቡ መጠቀም ስላሉት ጥቅሞች አንዳንድ ወጣቶች የተናገሩትን እንድትመለከት እንጋብዝሃለን።

ዮሴፍ የሰዎችን ሕይወት አትርፏል

ይህንን ታሪክ በማውረድ አምላክ አንድን ብሔር ለማዳን ዮሴፍን እንዴት እንደተጠቀመበት ማንበብ ትችላለህ።