በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

 አገሮችና ሕዝቦች

ካሜሩንን እንጎብኝ

ካሜሩንን እንጎብኝ

ፒግሚዎች በመባልም የሚታወቁት የባካ ሕዝቦች የመጀመሪዎቹ የካሜሩን ነዋሪዎች ሳይሆኑ አይቀሩም። ከዚያም በ1500ዎቹ ዓመታት ፖርቱጋሎች ወደዚህ አካባቢ መጡ። ይህ ከሆነ ከበርካታ መቶ ዓመታት በኋላ፣ ፉላሚ የተባሉ ሙስሊም ሕዝቦች የካሜሩንን ሰሜናዊ ክፍል ተቆጣጠሩ። በዛሬው ጊዜ 40 በመቶ የሚሆነው የካሜሩን ሕዝብ ክርስቲያን እንደሆነ ሲነገር 20 በመቶው ደግሞ ሙስሊም ነው፤ የቀሩት 40 በመቶ የሚያህሉ ሰዎች ሲወርድ ሲዋረድ የመጡ የአፍሪካ ሃይማኖቶችን ይከተላሉ።

የይሖዋ ምሥክሮች በካሜሩን በሚነገረው በባሳ ቋንቋ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎችን ያዘጋጃሉ

በተለይ በካሜሩን ገጠራማ አካባቢዎች የሚኖሩ ሰዎች እንግዳ ተቀባይ በመሆናቸው ይታወቃሉ። እንግዶች ሲመጡ ሞቅ ያለ አቀባበል የሚደረግላቸው ሲሆን ወደ ቤት ገብተውም እህል ውኃ እንዲሉ ይጋበዛሉ። ይህን ግብዣ አለመቀበል እንደ ነውር ይቆጠራል፤ በሌላ በኩል ደግሞ አንድ ሰው እንዲህ ያለውን መስተንግዶ በመቀበል ለቤቱ ባለቤት ያለውን አክብሮት ይገልጻል።

ጨዋታ የሚጀመረው ለቤተሰቡ አባላት ሰላምታ በመስጠትና ስለ ደኅንነታቸው በመጠየቅ ነው። ስለ ከብቶች ሁኔታ እንኳ መጠየቅ  የተለመደ ነው! የካሜሩን ተወላጅ የሆነው ጆሴፍ እንዲህ ብሏል፦ “እንግዳ ሲወጣ ‘ደህና ሁን’ ብሎ መሰናበት ብቻ በቂ አይደለም። አብዛኛውን ጊዜ የቤቱ ባለቤት እንግዳውን እያጫወተ ይሸኘዋል። የተወሰነ መንገድ ከተጓዙ በኋላ እንግዳውን ተሰናብቶት ወደ ቤቱ ይመለሳል። አንድ ሰው እንዲህ ያለ አቀባበል ካልተደረገለት ቅር ሊለው ይችላል።”

በሳናጋ ወንዝ ላይ፣ ከግንድ ተፈልፍለው የሚሠሩ ታንኳዎችን ማየት የተለመደ ነው። ሸራዎቹ የሚሠሩት በቀላሉ ከሚገኙ ነገሮች ነው

አንዳንድ ጊዜ ወዳጅ የሆኑ ሰዎች በአንድ ገበታ ዙሪያ ሆነው በእጃቸው ይመገባሉ። በካሜሩን ይህ ልማድ የአንድነት ተምሳሌት ነው። እንዲያውም አንዳንድ ጊዜ በሆነ ምክንያት ወዳጅነታቸው የቀዘቀዘ ሰዎችን እንደገና ለማቀራረብ ይህን ልማድ ይጠቀሙበታል። ከአንድ ገበታ መመገብ “አሁን በመካከላችን ሰላም ሰፍኗል” እንደ ማለት ነው።

የዚህ መጽሔት አዘጋጆች የሆኑት የይሖዋ ምሥክሮች በካሜሩን ከ300 የሚበልጡ ጉባኤዎችን ያደራጁ ሲሆን በዚያ አገር 65,000 የሚሆኑ ሰዎችን መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምራሉ