በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የወጣቶች ጥያቄ

አንድን ግብዣ አስደሳች የሚያስብለው ምንድን ነው?

አንድን ግብዣ አስደሳች የሚያስብለው ምንድን ነው?

አንድ ቦታ ስትጋበዝ በጉጉት የምትጠብቀው ነገር ላይ ✔ አድርግ።

  • ምግቡ

  • ጭፈራው

  • የተለያዩ ጨዋታዎች

  • አዳዲስ ጓደኞች ማፍራት

  • ከቀድሞ ጓደኞችህ ጋር መገናኘት

  • ሌላ ․․․․․

አብዛኞቹ ወጣቶች አንድ ላይ ተሰባስቦ መጫወት ይወዳሉ፤ ደግሞም ይህ ምንም ስህተት የለውም። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደዚህ ዓይነት ግብዣዎች በጥሩ ጎናቸው ተጠቅሰዋል።

ይህን ታውቅ ነበር?

  • የኢዮብ ወንዶች ልጆች የቤተሰባቸውን አባላት ቤታቸው ይጋብዙ ነበር።​—ኢዮብ 1:4

  • ኢየሱስ በአንድ የሠርግ ድግስ ላይ ተገኝቶ ነበር።​—ዮሐንስ 2:1-11

  • በመጀመሪያው መቶ ዘመን የነበሩ ክርስቲያኖች በቤታቸው ውስጥ ይገባበዙ ነበር።​—የሐዋርያት ሥራ 2:46, 47

ከጓደኞቻችን ጋር አብሮ ጊዜ ማሳለፍ አስደሳች እንደሆነ አይካድም። የሚያሳዝነው ግን፣ አስደሳች የሆኑት ሁሉም ግብዣዎች አይደሉም።

እውነተኛ ታሪክ “የሚፈልግ ሁሉ ሊመጣበት የሚችል ግብዣ ላይ ተጠርቼ ነበር፤ ግብዣው የሚደረገው አንድ ልጅ ቤት ሲሆን ወላጆቹ ከከተማ ወጥተው ነበር። እኔ ግን ወደ ግብዣው ላለመሄድ ወሰንኩ፤ ደግሞም እንኳን አልሄድኩ! በግብዣው ላይ የአልኮል መጠጥ በገፍ ቀርቦ እንደነበረና አንዳንዶችም ጥንብዝ ብለው እንደሰከሩ በማግስቱ ሰማሁ። እንዲያውም ሦስት ልጆች ራሳቸውን ስተው ነበር። በተጨማሪም ድብድብ በመነሳቱ ፖሊሶች መጥተው ግብዣውን በተኑት።”​—ጀኔል

የምታገኘው ትምህርት ከግብዣ ጋር በተያያዘ ነገሮችን አስቀድመህ አመዛዝን። ጋባዥም ሆንክ ተጋባዥ በቀጣዮቹ ገጾች ላይ የቀረቡትን ጥያቄዎች አስብባቸው። እንዲህ ካደረግህ ግብዣው ካበቃ በኋላ አስደሳች ትዝታዎች ይኖሩሃል እንጂ አትቆጭም።

ጥሩ ውሳኔ አድርገዋል

“ጓደኛዬ ቤት ግብዣ የነበረ ጊዜ እናቷ የእያንዳንዱን ሰው ሁኔታ ትቃኝ ነበር። ጃኬቴን ለማምጣት ወደ መኪናው በሄድኩ ጊዜ እንኳ የት እንደምሄድ ጠየቀችኝ። ጥንቃቄዋ ከመጠን ያለፈ ነበር? ሊሆን ይችላል። እኔ ግን በዚህ ቅር አላለኝም፤ ምክንያቱም ኋላ ከመቆጨት አስቀድሞ መጠንቀቅ እንደሚሻል አውቃለሁ።”​—ኪም

“ጥሩ ግብዣዎች ላይ ተገኝቼ አውቃለሁ፤ እነዚህ ግብዣዎች ስኬታማ ሊሆኑ የቻሉት በተለያየ የዕድሜ ክልል የሚገኙ ሰዎች ስለተጋበዙ ይመስለኛል። በተጨማሪም ጋባዦቹ ሁሉንም የሚያሳትፉ አስደሳች ጨዋታዎች አዘጋጅተው ስለነበር ብቻውን ነጠል ብሎ ሌላ ነገር የሚያደርግ ማንም ሰው አልነበረም።”​—አንድሪኣ