በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከኤሌክትሪክ ኃይል ማከፋፈያነት መንፈሳዊ ብርሃን ወደማንጸባረቅ ተለወጠ

ከኤሌክትሪክ ኃይል ማከፋፈያነት መንፈሳዊ ብርሃን ወደማንጸባረቅ ተለወጠ

ከኤሌክትሪክ ኃይል ማከፋፈያነት መንፈሳዊ ብርሃን ወደማንጸባረቅ ተለወጠ

ጣሊያን የሚገኘው የንቁ! ዘጋቢ እንደጻፈው

በ1900ዎቹ ዓመታት መጀመሪያ ላይ ጣሊያን ውስጥ በምትገኘው ፒስቶያ የምትባል ተራራማ አካባቢ የኢንዱስትሪ ተቋማት መስፋፋት ጀመሩ። ጥሬ ዕቃዎችንም ሆነ የኢንዱስትሪ ውጤቶችን ማጓጓዝ እንዲቻል በኤሌክትሪክ የሚሠራ አንድ የባቡር ሐዲድ ተዘርግቶ ነበር። ሰኔ 21, 1926 የተመረቀውና በጣም ጠባብ ሐዲዶች ያሉት ይህ የባቡር መስመር በኮረብቶችና በተራሮች ላይ እየተጥመለመለ የሚያልፍ ሲሆን 15 ኪሎ ሜትር ያህል ርዝመት አለው።

ባቡሩ የኤሌክትሪክ ኃይል የሚያገኘው ከአንድ የኤሌክትሪክ ማከፋፈያ ጣቢያ ነበር (በስተግራ ከላይ)። ይሁን እንጂ በአካባቢው የሚደረገው የንግድ እንቅስቃሴ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ በመምጣቱ የባቡር መስመሩ አገልግሎት መስጠት አቁሞ በ1965 ሙሉ በሙሉ ተዘጋ። ታዲያ በባቡር ሐዲዱ ግራና ቀኝ የተገነቡት ሕንፃዎችስ ምን ሆኑ? አንዳንዶቹ ዞር ብሎ የሚያያቸው ባለመገኘቱ ፈራርሰዋል፤ ሌሎቹ ደግሞ ከጊዜ በኋላ መጠጥ ቤቶችና የአውቶቡስ መናኸሪያ ሆነዋል።

የኤሌክትሪክ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያው ግን እድሳት ተደረገለት። በ1997 ሳን ማርቼሎ ፒስቶዬዜ የተባለው የይሖዋ ምሥክሮች ጉባኤ ሕንፃውን የገዛው ሲሆን በአሁኑ ጊዜ ተለውጦ በተስከኒ ከሚገኙት ውብ የመንግሥት አዳራሾች ውስጥ አንዱ ሆኗል (በስተግራ ከታች)። ቀደም ሲል በኃይል ማከፋፈያነት ያገለግል በነበረው በዚህ ሕንፃ ውስጥ የሚሰበሰበው ጉባኤ አባላት በዚህ ተራራማ አካባቢ የአምላክን መንግሥት ምሥራች በመስበኩ ሥራ በመጠመድ ‘እንደ ከዋክብት እያበሩ’ ነው። (ፊልጵስዩስ 2:15፤ ማቴዎስ 24:14) አዎን፣ ቀደም ሲል የኤሌክትሪክ ኃይል ማከፋፈያ ሆኖ ያገለግል የነበረው ሕንፃ በአሁኑ ጊዜ መንፈሳዊ ብርሃን ለማንጸባረቅ እያገለገለ ነው።—ማቴዎስ 5:14-16፤ 28:19, 20