በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የጉርምስና ዕድሜ ያለው ደስታና ፈተና

የጉርምስና ዕድሜ ያለው ደስታና ፈተና

 የጉርምስና ዕድሜ ያለው ደስታና ፈተና

ጉርምስና በጣም ግሩም የሆነ የዕድሜ ክፍል ሊሆን ይችላል። በእርግጥም ለብዙዎች አስደሳች ጊዜ ነው። ብዙ ትላልቅ ሰዎች የጉርምስና ዕድሜያቸውን ማስታወስ ያስደስታቸዋል።

ይሁን እንጂ የምንኖረው ‘በአስጨናቂ ዘመን’ ውስጥ መሆኑን መካድ አንችልም። (2 ጢሞቴዎስ 3:1) በዚህ ምክንያት ባሁኑ ዘመን የሚኖሩ ወጣቶች የቀደሙት ትውልዶች ያላጋጠሟቸው ዓይነት ተጨማሪ ተጽዕኖዎች ይደርሱባቸዋል። ለወጣቶች የሚታተም አንድ መጽሔት ዋና አዘጋጅ የሆኑት ሳብሪና ሶሊን ዋይል የጉርምስና ዕድሜን በተወጠረ ገመድ ላይ ያለምንም ድጋፍ ከመሄድ ጋር ያመሳሰሉት በዚህ ምክንያት ሳይሆን አይቀርም። በእርግጥም ይህ ተነዋዋጭ የሆነ የዕድሜ ክፍል ግራ መጋባትና ጭንቀት የበዛበት ሊሆን ይችላል። ዋይል “ጎረምሶች የሚገኙበት ዕድሜ በልጅነትና በጉልምስና መካከል ያለ በመሆኑ የሁለቱም የዕድሜ ክፍሎች ችግር ይጫናቸዋል” ሲሉ ጽፈዋል።

በጉርምስና ዕድሜ የምትገኝ ከሆነ የሚያጋጥሙህን ተፈታታኝ ሁኔታዎች እንዴት መቋቋም ትችላለህ? በጉርምስና ዕድሜ ላይ የሚገኝ ልጅ ያለህ ወላጅ ከሆንክ ደግሞ እነዚህ ነውጥ የበዛባቸው ዓመታት ምን ይመስሉ እንደነበረ እንድታስታውስና ልጅህ እንዴት ያለ ሁኔታ እያሳለፈ እንዳለ ይበልጥ እንድትገነዘብ ምን ሊረዳህ ይችላል? ወጣቶችንም ሆነ ጎልማሶችን ተከታታይ በሆኑት በእነዚህ ርዕሶች አማካኝነት የጉርምስናን ዕድሜ በቅርበት እንዲመረምሩ እንጋብዛለን። እንዲህ ያለው ጠለቅ ያለ ጥናት ወጣቶች የጉርምስና ዕድሜ የሚያስከትላቸውን ችግሮች ተወጥተው የተሳካላቸው ጎልማሶች እንዲሆኑ ይረዳቸዋል።