በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

“ይሖዋ አጽናኜ ነው”

“ይሖዋ አጽናኜ ነው”

“ይሖዋ አጽናኜ ነው”

ከላይ ያሉት ከላቲን ቋንቋ የተተረጎሙ ቃላት የስዊድኑ ንጉሥ የቻርልስ ዘጠነኛ ንጉሠ ነገሥታዊ መርህ ነበሩ። በላቲን “ዬሆቫ ሶላቲዩም ሚዩም” ተብሎ ይነበባል። ንጉሥ ቻርልስ ከ1560-1697 ድረስ በስዊድን ከነገሡት ከአንድ የዘር ሐረግ የመጡ በርካታ ገዢዎች መካከል አንዱ ሲሆን እነዚህ ነገሥታት በዕብራይስጥ ወይም በላቲን የአምላክን ስም በሳንቲሞችና በሜዳልያዎች ላይ ያስቀርፁ እንዲሁም በግል መርሆቻቸው ውስጥ ይጠቀሙበት ነበር። ቻርልስ ዘጠነኛ የይሖዋ ንጉሣዊ ማኅበር ተብሎ የሚጠራውን ድርጅት አቋቁሟል። በ1607 ቻርልስ ዘውድ በደፋበት ዕለት የይሖዋ ሰንሰለት የተባለ ሐብል አድርጎ ነበር።

እነዚህ ነገሥታት እንዲህ ዓይነት ልማድ እንዲከተሉ ያነሳሳቸው ምንድን ነው? ምሑራን፣ ነገሥታቱ ለመጽሐፍ ቅዱስ የነበራቸው አክብሮትና በወቅቱ በአውሮፓ ተስፋፍቶ የነበረው የካልቪናውያን እንቅስቃሴ ተጽዕኖ አሳድሮባቸዋል የሚል እምነት አላቸው። ሥልጣኔ በጀመረበት ዘመን የኖሩ ከፍተኛ ትምህርት ያላቸው ልዑላን እንደመሆናቸው መጠን ይሖዋ የሚለው የአምላክ የግል ስም በላቲን እንዴት እንደሚጻፍ ያውቁ እንደነበር ከሁኔታው መረዳት ይቻላል። አንዳንዶቹም ይህ ስም በመጀመሪያው የዕብራይስጥ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በሺዎች ለሚቆጠሩ ጊዜያት መጠቀሱን እንደተገነዘቡ አያጠራጥርም።

በ16ኛውና በ17ኛው መቶ ዘመን በአውሮፓ የተለያዩ ክፍሎች ይሖዋ የሚለው ስም በሳንቲሞች፣ በሜዳልያዎችና በሕዝብ ሕንጻዎች እንዲሁም በቤተ ክርስቲያኖች ላይ ይጻፍ እንደነበር የሚያሳዩ በርካታ ማስረጃዎች አሉ። በዘጸአት 3:​15 ላይ አምላክ ራሱ የተናገረው “እግዚአብሔር [“ይሖዋ፣” NW ] . . . ለዘላለሙ ስሜ ነው” የሚለው ጥቅስ ሰፊ ተቀባይነት ያገኘና በአክብሮት የሚታይ እንደነበር ከሁኔታዎቹ መረዳት ይቻላል።

[በገጽ 13 ላይ የሚገኙ ሥዕሎች]

የይሖዋ ንጉሣዊ ማኅበር ሰንሰለትና አርማ በ1606 ከወርቅ፣ ከኢናሜልና ከከበረ ድንጋይ የተሠራ

ንጉሥ ኤሪክ አሥራ አራተኛ 1560-68

ንጉሥ ቻርልስ ዘጠነኛ 1599-1611 (የኤሪክ አሥራ አራተኛ ወንድም)

ዳግማዊ ጉስታቨስ አዶልፍ 1611-32 (የቻርልስ ዘጠነኛ ልጅ)

ንግሥት ክርስቲና 1644-54 (የዳግማዊ ጉስታቨስ አዶልፍ ልጅ)

[ምንጮች]

ሰንሰለት:- Livrustkammaren, Stockholm Sverige; ሳንቲሞች:- Kungl. Myntkabinettet, Sveriges Ekonomiska Museum