በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ስለወደፊቱ ጊዜ አስተማማኝ መመሪያ ማግኘት

ስለወደፊቱ ጊዜ አስተማማኝ መመሪያ ማግኘት

ስለወደፊቱ ጊዜ አስተማማኝ መመሪያ ማግኘት

የአውደ ነገሥት ትንበያም ሆነ ሌላ ዓይነት የጥንቆላ ዘዴዎች አስተማማኝ ካልሆኑ ስለወደፊቱ ጊዜ ልናውቅ የምንችልበት ምንም መንገድ የለም ማለት ነውን? እንደዚያ ማለት አይደለም።

ረቂቅ የሆኑ ቁጥሮች ወደፊት የሚሆነውን ነገር ሊነግሩን አይችሉም። “በመጀመሪያ መጨረሻውን” የሚናገረው “ሕያው አምላክ” ግን ወደፊት የሚሆነውን ነገር ቃሉ በሆነው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ገልጾልናል። (1 ጢሞቴዎስ 4:10፤ ኢሳይያስ 46:10) በተጨማሪም ‘የልብን ስሜትና አሳብ በመመርመር’ ውስጣዊ ዝንባሌህን እንድታውቅ ሊረዳህና የተሳካ ውጤት የምታገኝበትን መንገድ ሊመራህ የሚችለው የሕያው አምላክ ቃል እንጂ የመጽሐፍ ገላጮች ቃል አይደለም።—ዕብራውያን 4:12

ወደፊት የሚሆነውን ነገር በትክክል ሊተነብይ የሚችለው የመጽሐፍ ቅዱስ ደራሲ የሆነው ፈጣሪያችን ነው። ይህም የሆነው አምላክ ሁሉን ማድረግ ስለሚችልና ምንጊዜም ከተናገረው ቃል ዝንፍ ስለማይል ነው። ይሖዋ አምላክ “ተናግሬአለሁ እፈጽምማለሁ” ብሏል። (ኢሳይያስ 46:11) ኢያሱ እስራኤላውያን ወደ ተስፋይቱ ምድር ከገቡ በኋላ በእርግጠኝነት “እግዚአብሔር ለእስራኤል ቤት ከተናገረው መልካም ነገር ሁሉ ተፈጸመ እንጂ ምንም አልቀረም” ለማለት ችሏል።—ኢያሱ 21:45፤ 23:14

መጽሐፍ ቅዱስ ገና ወደፊት የሚፈጸሙ በርካታ ትንቢቶችንም ይዟል። ከእነዚህ መካከል ምድር ከክፋት ሁሉ ጸድታ ገነት ስለምትሆንበት ጊዜ የሚናገረው ትንቢት ይገኛል። (መዝሙር 37:10, 11፤ ምሳሌ 2:21, 22) እንዲህ ባለው ጊዜ ለመኖር ትጓጓለህ? ፈጣሪያችን በዚህች ዓለም ላይ ያለውን ሁኔታ ለመለወጥ የሚያስችል ኃይልም ሆነ ጥበብ እንዳለው ታምናለህ? የምታምን ከሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ምድር የወደፊት ዕጣ የሚናገረውን መመርመር ይኖርብሃል። *

እንግዲያው በቁጥሮች ስሌት አማካኝነት ስለ ወደፊት ዕጣህ ለማወቅ ከመጣር ይልቅ መጽሐፍ ቅዱስንና በውስጡ ያሉትን ትንቢቶች በትክክል ለመረዳት በመጣር ጊዜህን በጥበብ ተጠቀምበት። የይሖዋ ምሥክሮች በአምላክ ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለተገለጸው የወደፊት ሁኔታ ተጨማሪ እውቀት እንድታገኝ ሊረዱህ ዝግጁ ናቸው።

[የግርጌ ማስታወሻ]