በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

“አዲስና ደስ የሚል አቀራረብ ነው!”

“አዲስና ደስ የሚል አቀራረብ ነው!”

በደቡብ ኮሪያ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ የተማሪዎች አማካሪ የሆነችው ሱ ጆንግ jw.org ላይ የሚገኙ ቪዲዮዎችን ለተማሪዎቿ ታሳያቸዋለች። እንዲህ በማለት ተናግራለች፦ “ተማሪዎቹ እውነተኛ ጓደኛ የሚባለው ምን ዓይነት ጓደኛ ነው? የተባለውን ቪዲዮ በጣም ወደውታል! ቪዲዮውን ካዩ በኋላ ‘ስለ ጓደኝነት በዚህ መልኩ አስቤ አላውቅም። አዲስና ደስ የሚል አቀራረብ ነው!’ በማለት ተናግረዋል። አንዳንዶቹ ደግሞ ወደፊት ምክር ሲያስፈልጋቸው ይህን ድረ ገጽ እንደሚመለከቱ ተናግረዋል።” ሱ ጆንግ እንዲህ በማለት አክላ ተናግራለች፦ “ለብዙ የሙያ ባልደረቦቼም ይህን ቪዲዮ እንዲጠቀሙበት ሐሳብ አቅርቤላቸዋለሁ፤ ለተማሪዎች ሊያሳዩ የሚችሉት እንዲህ ዓይነት ግሩም መሣሪያ በማግኘታቸው በጣም ተደስተዋል።”

በደቡብ ኮሪያ የሚገኙ በርካታ ተማሪዎች የወደዱት ሌላው ቪዲዮ ደግሞ ቡጢ ሳትሰነዝር ጉልበተኞችን ማሸነፍ የሚለው የነጭ ሰሌዳ አኒሜሽን ነው። የወጣቶችን ዓመፅ ለመከላከል ከተቋቋመ ድርጅት ጋር የምትሠራ አንዲት መምህርት ይህንን ቪዲዮ ለተማሪዎች አሳይታ ነበር። እንዲህ ብላለች፦ “ቪዲዮው ማራኪ የሆኑ ሥዕሎች ስላሉት የብዙ ወጣቶችን ትኩረት ይስባል። በተጨማሪም ቪዲዮው የዓመፅ ድርጊቶችን መቋቋም ብቻ ሳይሆን መከላከል የሚቻልባቸውንም መንገዶች የሚያሳይ በመሆኑ ጠቃሚ ነው።” ይህ ድርጅት፣ ለብዙ የአንደኛና የመለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች በሚያዘጋጃቸው ንግግሮች ላይ ቪዲዮውን ለማሳየት ፈቃድ የጠየቀ ሲሆን ይህን ለማድረግ ተፈቅዶለታል። ፖሊሶችም ጭምር jw.org ላይ የሚገኙ ቪዲዮዎችን እየተጠቀሙ ነው።

ይህን ድረ ገጽ ተመልክተኸው የማታውቅ ከሆነ እንድትጎበኘው እንጋብዝሃለን። ድረ ገጹ ለመቃኘት ቀላል ነው፤ ከዚህ ድረ ገጽ ላይ የኦዲዮና የቪዲዮ ፕሮግራሞችን፣ መጽሐፍ ቅዱስንና ሌሎች ጽሑፎችን በነፃ ማውረድ ትችላለህ።