በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ቶሌዶ የስፔንን ታሪካዊና ባሕላዊ ገጽታ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ከተማ ነው። በ1986 የዓለም ቅርስ ሆኖ የተመዘገበ ሲሆን ታዋቂ የቱሪስት መዳረሻ ነውs

 አገሮችና ሕዝቦች

ስፔንን እንጎብኝ

ስፔንን እንጎብኝ

ስፔን የተለያየ መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ ያላትና ልዩ ልዩ ሕዝቦች የሚኖሩባት አገር ናት። አብዛኛው የስፔን መሬት በስንዴና በወይን እርሻ እንዲሁም በወይራ ዛፎች የተሸፈነ ነው። በደቡብ በኩል ስፔንን ከአፍሪካ አህጉር የሚለያት 14 ኪሎ ሜትር ስፋት ያለው ውኃ ብቻ ነው።

ፊንቄያውያንን፣ ግሪካውያንንና የካርቴጅ ሰዎችን ጨምሮ በርካታ ሕዝቦች በአውሮፓ ደቡባዊ ምዕራብ ጫፍ ወደምትገኘው ወደዚች አገር ፈልሰዋል። ሮማውያን በሦስተኛው መቶ ዘመን ዓ.ዓ. ይህን አካባቢ ከተቆጣጠሩ በኋላ ሂስፓኒያ ብለው ጠሩት። ከጊዜ በኋላ ደግሞ ቪሲጎቶችና ሙሮች በዚህ አካባቢ መኖር የጀመሩ ሲሆን ሁሉም ባሕላዊ ቅርሳቸውን ትተው አልፈዋል።

በ2015 ብቻ ከ68 ሚሊዮን የሚበልጡ ሰዎች ስፔንን ጎብኝተዋል። ሞቃታማ የሆነው የስፔን ፀሐይና ወርቃማ የሆኑት የባሕር ዳርቻዎቿ  እንዲሁም በአገሪቱ ውስጥ የሚገኙት ጥንታዊ የሥነ ጥበብና የምሕንድስና ውጤቶች ዋና ዋናዎቹ የቱሪስት መስህቦች ናቸው። የስፔንን ምግብ ለማጣጣም ብለው የሚመጡ በርካታ ጎብኚዎችም አሉ። በብዛት ከሚገኙት ምግቦች መካከል የባሕር ምግቦች፣ በጭስ ወይም በጨው የደረቀ የአሳማ ሥጋ፣ የተለያዩ ዓይነት ወጦች፣ ሰላጣ እንዲሁም በወይራ ዘይት የተቀመሙ ወይም የበሰሉ አትክልቶች ይገኙበታል። የስፔን ኦምሌት፣ ፓኤላ እንዲሁም ታፓ በመላው ዓለም ተወዳጅነት ያተረፉ ምግቦች ናቸው።

ማሪስካዳ የሚባለው በስፋት የሚታወቅ የባሕር ምግብ

የፍላሜንኮ ዳንስ

ስፔናውያን ሰው ወዳድና ተግባቢ ናቸው። አብዛኞቹ ስፔናውያን የሮም ካቶሊክ እምነት ተከታዮች እንደሆኑ ቢናገሩም ብዙዎቹ ቤተ ክርስቲያን አይሄዱም። ባለፉት ዓመታት ውስጥ ብዙ ሰዎች ከአፍሪካ፣ ከእስያና ከላቲን አሜሪካ ወደ ስፔን ፈልሰዋል። ከእነዚህ መካከል አብዛኞቹ ስለ እምነታቸውና ስለ ባሕላቸው ከሌሎች ጋር መወያየት ያስደስታቸዋል። የይሖዋ ምሥክሮች ከእነዚህ ሰዎች ጋር ጥሩ ውይይት ያደረጉ ሲሆን መጽሐፍ ቅዱስ ስለተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ምን እንደሚያስተምር እንዲገነዘቡ እነዚህን ሰዎች መርዳት ችለዋል።

በ2015 ከ10,500 የሚበልጡ የይሖዋ ምሥክሮች፣ የመንግሥት አዳራሽ ተብለው የሚጠሩትን 70 የይሖዋ ምሥክሮች መሰብሰቢያ አዳራሾች ለመገንባት ወይም ለማደስ ራሳቸውን በፈቃደኝነት አቅርበዋል። ማዘጋጃ ቤቶቹ ለአንዳንዶቹ ፕሮጀክቶች የሚሆን መሬት በነፃ ሰጥተዋል። የይሖዋ ምሥክሮች ከተለያዩ አገሮች የመጡ ስደተኞችን ለመርዳት ሲሉ ከስፓንኛ ሌላ ከ30 በላይ በሚሆኑ ቋንቋዎች ስብሰባዎችን ያደርጋሉ። በ2016 ከ186,000 በላይ የሚሆኑ ሰዎች የይሖዋ ምሥክሮች የኢየሱስ ክርስቶስን ሞት መታሰቢያ ለማክበር ባደረጉት ልዩ ስብሰባ ላይ ተገኝተዋል።