በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ንቁ! ቁጥር 1 2018 | ደስታ የሚያስገኝ መንገድ

ደስተኛ ሕይወት ለመምራት የሚያስችል አስተማማኝ መመሪያ ማግኘት የምንችለው ከየት ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ “በመንገዳቸው ነቀፋ የሌለባቸው፣ በይሖዋ ሕግ የሚመላለሱ ሰዎች ደስተኞች ናቸው” ይላል።—መዝሙር 119:1

በእነዚህ ሰባት ርዕሶች ላይ ለደስታ ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ አስተማማኝና ዘመን የማይሽራቸው ነጥቦች ይብራራሉ።

 

መንገዱን ማግኘት

ደስተኛ እንደሆንክ ይሰማሃል? አንድን ሰው ደስተኛ እንዲሆን የሚያደርገው ምንድን ነው?

ባለን መርካትና ለጋስ መሆን

ብዙዎች ደስታ የሚለካው በሀብት ወይም በንብረት ብዛት እንደሆነ ይሰማቸዋል። በእርግጥ ገንዘብ ወይም ቁሳዊ ንብረት ዘላቂ ደስታ ያስገኛል? ማስረጃዎቹ ምን ይጠቁማሉ?

ጥሩ ጤንነትና ችግርን ተቋቁሞ የመኖር ችሎታ

አንድ ሰው የጤና ችግር ካለበት በሐዘን ተቆራምዶ ከመኖር ውጭ ምንም አማራጭ የለውም?

ፍቅር

ፍቅር ለደስታ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል።

ይቅር ባይነት

ተበሳጭቶና ቂም ይዞ የሚቆይ ሰው በሕይወቱ ደስታ የሚያጣ ከመሆኑም ሌላ ጤንነቱ ይጎዳል።

ዓላማ ያለው ሕይወት

ሕይወትን በተመለከተ ለምናነሳቸው አንገብጋቢ ጥያቄዎች አጥጋቢ መልስ ማግኘታችን ለደስታችን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል።

ተስፋ

በርካታ ሰዎች ራሳቸውም ሆኑ የሚወዷቸው ሰዎች ወደፊት ምን እንደሚጠብቃቸው በእርግጠኝነት አያውቁም፤ ይህም ደስተኛ እንዳይሆኑ አድርጓቸዋል።

ተጨማሪ መረጃ

አንድ ሰው ደስተኛ እንዲሆን ወይም እንዳይሆን የሚያደርጉት የተለያዩ ምክንያቶች አሉ። በሕይወትህ ውስጥ አስፈላጊ በሆኑ መስኮች ለምታነሳቸው ጥያቄዎች መልስ የምታገኝበት አንድ ምንጭ አለ፤ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ጥረት እንድታደርግ እንጋብዝሃለን።