ንቁ! ቁጥር 6 2016 | በሽታን መከላከል የሚቻለው እንዴት ነው?
በዛሬው ጊዜ ሕይወትን አደጋ ላይ የሚጥሉ በሽታዎች በዓለማችን ላይ በዝተዋል። ታዲያ እንዲህ ያሉ በሽታዎችን መከላከል የምንችለው እንዴት ነው?
መጽሐፍ ቅዱስ “ብልህ ሰው አደጋ ሲያይ ይሸሸጋል” በማለት ጥበብ ያዘለ ምክር ይሰጣል።—ምሳሌ 22:3
ይህ “ንቁ!” መጽሔት፣ ከአደጋ መሸሸግ ማለትም በሽታን መከላከል የምንችለው እንዴት እንደሆነ ያብራራል።
የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ
በሽታን መከላከል የሚቻለው እንዴት ነው?
ሰውነትህ በዓይን ከማይታዩና ድምፅ ከሌላቸው ሆኖም ሞት ሊያስከትሉ ከሚችሉ ጠላቶች ጋር በየዕለቱ ይዋጋል።
ንድፍ አውጪ አለው?
የባሕር መስል ራሱን የሚያጣብቅበት መንገድ
የባሕር መስሎች በክሮች አማካኝነት ራሳቸውን ያጣብቃሉ። የእነዚህን ክሮች ንድፍ መረዳት በሕንፃዎች ላይ መሣሪያዎችን ለመግጠምና ጅማትን ከአጥንት ጋር ለማያያዝ ያስችላል።
ለቤተሰብ
አክብሮት ማሳየት የሚቻለው እንዴት ነው?
አክብሮት አንዳንድ ጊዜ ብቻ ልናሳየው የሚገባ ነገር አይደለም፤ ከዚህ ይልቅ ለትዳር ወሳኝ የሆነ ባሕርይ ነው። ለትዳር ጓደኛችሁ አክብሮት ማሳየት የምትችሉት እንዴት ነው?
አስደናቂው ክላውን ፊሽ
በቀለማት ያሸበረቀው ይህ ትንሽ ዓሣ ከአኔመኒ ጋር አስደናቂ ጥምረት አለው። ይህን ጥምረት ልዩ የሚያደርገው ምንድን ነው?
መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
ሰዓት ማክበር
ሰዓት አክባሪ መሆን አለመሆንህ በሰዎች ዘንድ የምታተርፈውን ስም ይነካዋል። መጽሐፍ ቅዱስ ስለዚህ አስፈላጊ ባሕርይ ምን ይላል? ሰዓት አክባሪ ለመሆን ምን ይረዳናል?
የ2016 ንቁ! ርዕስ ማውጫ
በ2016 ንቁ! ላይ የወጡ ርዕሰ ጉዳዮች ዝርዝር።
በተጨማሪም . . .
ዕቃዎችህን በሥርዓት አስቀምጥ
ይሖዋ ለሁሉም ነገር ቦታ አዘጋጅቷል። አንተም ዕቃዎችህን በሥርዓት ማስቀመጥና ንጹሕ መሆን የምትችልበትን መንገድ መማር ትችላለህ!
መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ገና ምን ይላል?
ከገና በዓል ጋር የተያያዙ አምስት አስገራሚ ነገሮችን እንድታነብ እንጋብዝሃለን።

