መጠበቂያ ግንብ—የጥናት እትም ግንቦት 2017

ይህ እትም ከሐምሌ 3-30, 2017 የሚጠኑ የጥናት ርዕሶችን ይዟል።

“የባዕድ አገር ሰዎች” ይሖዋን ‘በደስታ እንዲያገለግሉት’ መርዳት

ይሖዋን ለማያውቁ ስደተኞች ምሥራቹን ውጤታማ በሆነ መንገድ ማካፈል የምትችለው እንዴት ነው?

“የባዕድ አገር ሰዎችን” ልጆች መርዳት

ከአገራችሁ ውጭ የምትኖሩ ወላጆች ከሆናችሁ ልጆቻችሁ ስለ ይሖዋ ለመማር የተሻለ አጋጣሚ እንዲኖራቸው ማድረግ የምትችሉት እንዴት ነው? ሌሎችስ በዚህ ረገድ እርዳታ መስጠት የሚችሉት እንዴት ነው?

የሕይወት ታሪክ

መስማት የተሳነኝ መሆኔ ሌሎችን ከማስተማር አላገደኝም

ዋልተር ማርከን መስማት ባይችሉም በይሖዋ አምላክ አገልግሎት አስደሳችና የሚያረካ ሕይወት አሳልፈዋል።

ፍቅራችሁ እንዳይቀዘቅዝ ተጠንቀቁ

በመጀመሪያው መቶ ዘመን የነበሩ አንዳንድ ክርስቲያኖች መጀመሪያ ላይ የነበራቸውን ፍቅራቸውን ትተው ነበር። እኛስ ለይሖዋ ያለን ፍቅር ምንጊዜም ጠንካራ እንዲሆን ምን ይረዳናል?

“ከእነዚህ አስበልጠህ ትወደኛለህ?”

ኢየሱስ ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ነገሮች ቅድሚያ መስጠትን በተመለከተ ለስምዖን ጴጥሮስ ጠቃሚ ትምህርት ሰጥቶታል። በዛሬው ጊዜስ ይህን ምክር ተግባራዊ ማድረግ እንችላለን?

ጋይዮስ ወንድሞቹን የረዳበት መንገድ

ጋይዮስ ማን ነው? የእሱን ምሳሌ መከተል ያለብንስ ለምንድን ነው?

ኑሮን ማቅለል የሚያስገኘው ደስታ

አንድ ባልና ሚስት ኑሯቸውን እንዲያቀልሉ ያነሳሳቸው ምንድን ነው? ይህን ያደረጉትስ እንዴት ነው? ያደረጉት ውሳኔ ደስታ ያስገኘላቸው ለምንድን ነው?

ከታሪክ ማኅደራችን

“ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ ልባችን በቅንዓትና በፍቅር ተሞልቶ ነበር”

የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎቹ በ1922 ካደረጉት ትልቅ ስብሰባ በኋላ ‘ንጉሡንና መንግሥቱን አስታውቁ’ የሚለውን ምክር ተግባራዊ ያደረጉት እንዴት ነው?