መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምራል?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምራል?

አርማጌዶን ምንድን ነው?

አንዳንዶች ምን ብለው ያምናሉ?

አርማጌዶን በኑክሌር የጦር መሣሪያ ወይም በአካባቢ መበከል የተነሳ የሚመጣ ዓለም አቀፍ ጥፋት እንደሆነ የሚያምኑ ሰዎች አሉ። አንተስ ምን ይመስልሃል?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

አርማጌዶን “ሁሉን ቻይ በሆነው አምላክ ታላቅ ቀን” ጦርነት የሚካሄድበት ምሳሌያዊ ቦታ ነው፤ ይህ ጦርነት አምላክ ከክፉዎች ጋር የሚያደርገው ጦርነት ነው።—ራእይ 16:14, 16

መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረው ሌላስ ነገር አለ?

  • አምላክ የአርማጌዶን ጦርነትን የሚያካሂደው ምድርን ለማጥፋት ሳይሆን የሰው ልጆች ምድርን እንዳያጠፏት ለመከላከል ነው።—ራእይ 11:18

  • የአርማጌዶን ጦርነት ጦርነቶችን ሁሉ ያስወግዳል።—መዝሙር 46:8, 9

ከአርማጌዶን ጦርነት መትረፍ ይቻላል?

ምን ብለህ ትመልሳለህ?

  • ይቻላል

  • አይቻልም

  • ምናልባት

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

ከሁሉም ብሔራት የተውጣጡ “እጅግ ብዙ ሕዝብ” በአርማጌዶን ጦርነት ከሚደመደመው ‘ከታላቁ መከራ’ ይተርፋሉ።—ራእይ 7:9, 14

መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረው ሌላስ ነገር አለ?

  • አምላክ በተቻለ መጠን ብዙ ሰዎች ከአርማጌዶን ጦርነት እንዲተርፉ ይፈልጋል። በክፉዎች ላይ ጥፋት ማምጣትን የሚመለከተው እንደ መጨረሻ አማራጭ አድርጎ ነው።—ሕዝቅኤል 18:32

  • መጽሐፍ ቅዱስ ከአርማጌዶን መትረፍ ስለሚቻልበት መንገድ ይናገራል።—ሶፎንያስ 2:3