በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የአምላክ ስም (ጎላ ያለው) በእጅ በተገለበጠ አንድ ጥንታዊ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምራል?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምራል?

አምላክ ስም አለው?

አንዳንዶች ምን ይላሉ? አንዳንድ ሰዎች አምላክ ስም የለውም ሲሉ ሌሎች ደግሞ ስሙ “እግዚአብሔር” ወይም “ጌታ” ነው ይላሉ፤ የተለያዩ ስሞች አሉት የሚሉም አሉ። አንተስ ምን ብለህ ታምናለህ?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

“ስምህ ይሖዋ የሆነው አንተ፣ አዎ፣ አንተ ብቻ በመላው ምድር ላይ ልዑል እንደሆንክ ሰዎች ይወቁ።”—መዝሙር 83:18

መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረው ሌላስ ነገር አለ?

  • አምላክ በርካታ የማዕረግ ስሞች ቢኖሩትም ሊጠራበት የሚገባ አንድ ስም እንዳለ ገልጿል።—ዘፀአት 3:15

  • አምላክ ሚስጥር አይደለም፤ እንዲያውም በሚገባ እንድናውቀው ይፈልጋል።—የሐዋርያት ሥራ 17:27

  • የአምላክ ወዳጅ ለመሆን የሚረዳን የመጀመሪያው ነገር ስሙን ማወቅ ነው።—ያዕቆብ 4:8

የአምላክን ስም መጥራት ስህተት ነው?

ምን ትላለህ?

  • ነው

  • አይደለም

  • እኔ እንጃ

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

“የአምላክህን የይሖዋን ስም በከንቱ አታንሳ።” (ዘፀአት 20:7) በአምላክ ስም መጠቀም ስህተት የሚሆነው አክብሮት በጎደለው መንገድ ከተጠቀምንበት ብቻ ነው።—ኤርምያስ 29:9

መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረው ሌላስ ነገር አለ?

  • ኢየሱስ የአምላክን ስም ያውቃል፤ በስሙም ይጠቀም ነበር።—ዮሐንስ 17:25, 26

  • አምላክ በስሙ እንድንጠራው ይፈልጋል።—መዝሙር 105:1

  • የአምላክ ጠላቶች ሰዎች ስሙን እንዲረሱ ለማድረግ ጥረት ያደርጋሉ።—ኤርምያስ 23:27