‘የዋሆች ምድርን ይወርሳሉ’
አብዛኞቻችን ፍትሕ ሲዛባና ክፉዎች ትክክል የሆነውን ማድረግ በሚፈልጉ ሰዎች ላይ ግፍ ሲፈጽሙ ተመልክተናል። የፍትሕ መዛባትና ክፋት የማይኖሩበት ጊዜ ይመጣ ይሆን?
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘው መዝሙር 37 የዚህን ጥያቄ መልስ የሚሰጠን ሲሆን ለዘመናችን የሚጠቅም መመሪያም ይዟል። መዝሙር 37 ቀጥሎ ለቀረቡት ጥያቄዎች የሚሰጠውን መልስ ልብ በል፦
በመንፈስ ቅዱስ መሪነት የተጻፈው መዝሙር 37 ‘ይሖዋን ተስፋ የሚያደርጉና መንገዱን የሚከተሉ’ ሰዎች ብሩሕ ተስፋ እንደሚጠብቃቸው ይናገራል። የይሖዋ ምሥክሮች መጽሐፍ ቅዱስን እንድታጠና ሊረዱ ይችላሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናትህ አንተም ሆንክ ቤተሰብህ አስተማማኝ የወደፊት ተስፋ እንዲኖራችሁ ይረዳችኋል።