በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

አምላክ ጸሎትህን ይሰማል?

አምላክ ጸሎትህን ይሰማል?

አምላክ የምታቀርበውን ጸሎት የሚሰማ ይመስልሃል?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምራል?

  • አምላክ ጸሎትህን ይሰማል። መጽሐፍ ቅዱስ “ይሖዋ ለሚጠሩት ሁሉ፣ በእውነት ለሚጠሩት ሁሉ ቅርብ ነው። . . . እርዳታ ለማግኘት የሚያሰሙትንም ጩኸት ይሰማል” የሚል ማረጋገጫ ይሰጠናል።—መዝሙር 145:18, 19

  • አምላክ ወደ እሱ እንድትጸልይ ይፈልጋል። መጽሐፍ ቅዱስ “ስለ ሁሉም ነገር በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር ልመናችሁን ለአምላክ አቅርቡ” በማለት ጋብዞናል።—ፊልጵስዩስ 4:6

  • አምላክ ያስብልሃል። አምላክ የሚያሳስበንንና የሚያስጨንቀንን ነገር ጠንቅቆ የሚያውቅ ከመሆኑም በላይ ሊረዳን ይፈልጋል። መጽሐፍ ቅዱስ “የሚያስጨንቃችሁንም ነገር ሁሉ በእሱ ላይ ጣሉ፤ ምክንያቱም እሱ ስለ እናንተ ያስባል” ይላል።—1 ጴጥሮስ 5:7