የወደፊት ሕይወትን አስተማማኝ ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው?

የወደፊት ሕይወትን አስተማማኝ ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው?

የወደፊት ሕይወትን አስተማማኝ ለማድረግ የሚረዳው ምን ይመስልሃል?

  • ከፍተኛ ትምህርት?

  • ሀብት?

  • ጥሩ ሰው መሆን?

  • ወይስ ሌላ ነገር?

የፈጣሪ ቃል እንዲህ ይላል፦

“ጥበብ ለአንተ መልካም እንደሆነ እወቅ። ጥበብን ብታገኝ የወደፊት ሕይወትህ የተሳካ ይሆናል።”—ምሳሌ 24:14

በፈጣሪ ቃል ውስጥ የወደፊት ሕይወትህን አስተማማኝ ለማድረግ የሚረዱ ጥበብ ያዘሉ ምክሮችን ታገኛለህ።