በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የወደፊት ሕይወትህ የተመካው በአንተ ምርጫ ላይ ነው

የወደፊት ሕይወትህ የተመካው በአንተ ምርጫ ላይ ነው

ከ3,500 ዓመታት ገደማ በፊት ይሖዋ አምላክ ለአገልጋዮቹ የወደፊት ሕይወታቸውን አስተማማኝ ለማድረግ ከእነሱ ምን እንደሚጠበቅ ነግሯቸዋል። እንዲህ ብሏቸዋል፦ “ሕይወትንና ሞትን፣ በረከትንና እርግማንን በፊታችሁ [አስቀምጫለሁ]፤ እንግዲህ አንተም ሆንክ ዘሮችህ በሕይወት እንድትኖሩ ሕይወትን ምረጥ።”—ዘዳግም 30:19

እነዚህ ሰዎች የወደፊት ተስፋቸው ብሩህ እንዲሆን ከፈለጉ ትክክለኛ ምርጫ ማድረግ ነበረባቸው። እኛም ተመሳሳይ ምርጫ ቀርቦልናል። መጽሐፍ ቅዱስ የወደፊቱን ጊዜ በተመለከተ ጥሩ ምርጫ ማድረግ የሚቻለው እንዴት እንደሆነ ይናገራል፤ ‘አምላክህን ይሖዋን በመውደድ እና ቃሉን በመስማት ነው’ ይላል።—ዘዳግም 30:20

ይሖዋን መውደድና ቃሉን መስማት የምንችለው እንዴት ነው?

መጽሐፍ ቅዱስን ተማር፦ ይሖዋን ለመውደድ በቅድሚያ ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ስለ እሱ መማር ያስፈልግሃል። እንዲህ ስታደርግ ይሖዋ ለአንተ ከሁሉ የተሻለውን ነገር የሚመኝ አፍቃሪ አምላክ እንደሆነ ትገነዘባለህ። ወደ እሱ እንድትጸልይ ግብዣ አቅርቦልሃል፤ ‘ምክንያቱም እሱ ስለ አንተ ያስባል።’ (1 ጴጥሮስ 5:7) ወደ አምላክ ለመቅረብ ጥረት ካደረግክ ‘እሱም ወደ አንተ እንደሚቀርብ’ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል።—ያዕቆብ 4:8

የተማርከውን ተግባራዊ አድርግ፦ አምላክን መስማት ማለት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘውን ጥበብ ያዘለ መመሪያ መከተል ማለት ነው። “እንዲህ ካደረግክ መንገድህ ይቃናልሃል፤ እንዲሁም ማንኛውንም ነገር በጥበብ ማከናወን ትችላለህ።”—ኢያሱ 1:8