ሁለተኛ ሳሙኤል 23:1-39

  • የዳዊት የመጨረሻ ቃላት (1-7)

  • የዳዊት ኃያላን ተዋጊዎች የፈጸሙት ጀብዱ (8-39)

23  የዳዊት የመጨረሻ ቃላት እነዚህ ናቸው፦+ “የእሴይ ልጅ የዳዊት ቃል፣+ከፍ ከፍ የተደረገው ሰው ቃል፣+የያዕቆብ አምላክ የቀባው፣+የእስራኤል መዝሙሮች ተወዳጅ ዘማሪ።*+   የይሖዋ መንፈስ በእኔ ተናገረ፤+ቃሉ በአንደበቴ ላይ ነበረ።+   የእስራኤል አምላክ ተናገረ፣የእስራኤል ዓለት+ እንዲህ አለኝ፦ ‘የሰው ልጆችን የሚገዛው ጻድቅ ሲሆን፣+አምላክን በመፍራት ሲገዛ፣+   ፀሐይ በምትፈነጥቅበት ጊዜ እንደሚኖረው የማለዳ ብርሃን፣+ደመና እንደሌለበት ማለዳ ይሆናል። ሣርን ከምድር እንደሚያበቅል፣+ዝናብ ካባራ በኋላ ፍንትው ብሎ እንደሚወጣ የፀሐይ ብርሃን ነው።’   የእኔስ ቤት በአምላክ ፊት እንዲሁ አይደለም? እሱ ከእኔ ጋር ዘላለማዊ ቃል ኪዳን ገብቷልና፤+ቃል ኪዳኑም የተስተካከለና አስተማማኝ ነው። ምክንያቱም ይህ ለእኔ የተሟላ መዳንና ፍጹም ደስታ ነው፤ደግሞስ ቤቴ እንዲለመልም የሚያደርገው ለዚህ አይደለም?+   የማይረቡ ሰዎች ሁሉ ልክ እንደ እሾህ ቁጥቋጦ ወዲያ ይጣላሉ፤+በእጅ ሊሰበሰቡ አይችሉምና።   የሚነካቸው ሰውየብረት መሣሪያ መታጠቅና የጦር ዘንግ መያዝ አለበት፤እነሱም ባሉበት ሙሉ በሙሉ በእሳት መቃጠል አለባቸው።”  የዳዊት ኃያላን ተዋጊዎች+ ስም ይህ ነው፦ የሦስቱ መሪ+ የሆነው ታህክሞናዊው ዮሼብባሼቤት። እሱም ጦሩን ሰብቆ በአንድ ጊዜ 800 ሰው ገደለ።  ከእሱ ቀጥሎ የአሆሐይ ልጅ የሆነው የዶዶ+ ልጅ አልዓዛር+ ነበር፤ እሱም ፍልስጤማውያንን በተገዳደሩበት ጊዜ ከዳዊት ጋር ከነበሩት ሦስት ኃያላን ተዋጊዎች አንዱ ነው። ፍልስጤማውያንም በዚያ ለጦርነት ተሰብስበው ነበር፤ የእስራኤል ሰዎች ባፈገፈጉ ጊዜ 10  እሱ ካለበት ንቅንቅ ሳይል እጁ እስኪዝልና ከጨበጠው ሰይፍ ላይ መላቀቅ እስኪያቅተው ድረስ ፍልስጤማውያንን ጨፈጨፋቸው።+ በመሆኑም ይሖዋ በዚያ ቀን ታላቅ ድል አጎናጸፈ፤*+ ሕዝቡም ከተገደሉት ሰዎች ላይ ለመግፈፍ ከእሱ ኋላ ተመልሶ መጣ። 11  ከእሱ ቀጥሎ የሃራራዊው የአጌ ልጅ ሻማህ ነበር። ፍልስጤማውያን ሊሃይ በተባለ ስፍራ ምስር በሞላበት አንድ ማሳ ውስጥ ተሰብስበው ነበር፤ ሕዝቡም በፍልስጤማውያን የተነሳ ሸሸ። 12  እሱ ግን በእርሻው መካከል ካለበት ንቅንቅ ሳይል መሬቱ እንዳይያዝ አደረገ፤ ፍልስጤማውያንንም መታቸው፤ በመሆኑም ይሖዋ ታላቅ ድል አጎናጸፈ።*+ 13  በመከር ወቅት ከ30ዎቹ መሪዎች መካከል ሦስቱ ዳዊት ወደሚገኝበት ወደ አዱላም+ ዋሻ ወረዱ፤ አንድ የፍልስጤማውያን ቡድንም* በረፋይም ሸለቆ*+ ሰፍሮ ነበር። 14  በዚህ ጊዜ ዳዊት በምሽጉ+ ውስጥ ነበር፤ የፍልስጤማውያንም የጦር ሰፈር በቤተልሔም ነበር። 15  ከዚያም ዳዊት “በቤተልሔም በር አቅራቢያ ካለው የውኃ ማጠራቀሚያ ጉድጓድ የምጠጣው ውኃ ባገኝ ምንኛ ደስ ባለኝ!” በማለት ምኞቱን ገለጸ። 16  በዚህ ጊዜ ሦስቱ ኃያላን ተዋጊዎች ወደ ፍልስጤማውያን ሰፈር ጥሰው በመግባት በቤተልሔም በር አቅራቢያ ከሚገኘው የውኃ ማጠራቀሚያ ጉድጓድ ውኃ ቀድተው ለዳዊት አመጡለት፤ እሱ ግን ለመጠጣት ፈቃደኛ አልሆነም፤ ከዚህ ይልቅ ውኃውን ለይሖዋ አፈሰሰው።+ 17  ከዚያም “ይሖዋ ሆይ፣ ይህን ማድረግ ፈጽሞ የማላስበው ነገር ነው! ሕይወታቸውን* አደጋ ላይ ጥለው የሄዱትን የእነዚህን ሰዎች ደም ልጠጣ ይገባል?”+ አለ። በመሆኑም ውኃውን ለመጠጣት ፈቃደኛ አልሆነም። ሦስቱ ኃያላን ተዋጊዎቹ ያደረጓቸው ነገሮች እነዚህ ነበሩ። 18  የጽሩያ+ ልጅ የኢዮዓብ ወንድም አቢሳ+ የሌሎች ሦስት ሰዎች መሪ ነበር፤ እሱም ጦሩን ሰብቆ 300 ሰው ገደለ፤ እንደ ሦስቱም ሰዎች ዝነኛ ነበር።+ 19  ምንም እንኳ ከሌሎቹ ሦስት ሰዎች ይበልጥ ታዋቂና የእነሱ አለቃ የነበረ ቢሆንም የመጀመሪያዎቹን ሦስት ሰዎች ያህል ማዕረግ አላገኘም። 20  የዮዳሄ ልጅ በናያህ+ በቃብጽኤል+ ብዙ ጀብዱ የፈጸመ ደፋር ሰው* ነበር። እሱም የሞዓቡን የአርዔልን ሁለት ወንዶች ልጆች ገደለ፤ እንዲሁም በረዶ በሚጥልበት ዕለት ወደ አንድ የውኃ ማጠራቀሚያ ጉድጓድ ወርዶ አንበሳ ገደለ።+ 21  በተጨማሪም እጅግ ግዙፍ የሆነ ግብፃዊ ገደለ። ግብፃዊው በእጁ ጦር ይዞ የነበረ ቢሆንም እሱ ግን በትር ብቻ ይዞ በመሄድ ገጠመው፤ የግብፃዊውንም ጦር ከእጁ ቀምቶ በገዛ ጦሩ ገደለው። 22  የዮዳሄ ልጅ በናያህ ያደረጋቸው ነገሮች እነዚህ ነበሩ፤ እሱም እንደ ሦስቱ ኃያላን ተዋጊዎች ዝነኛ ነበር። 23  ከሠላሳዎቹ ይበልጥ ታዋቂ የነበረ ቢሆንም የሦስቱን ሰዎች ያህል ማዕረግ አላገኘም። ይሁን እንጂ ዳዊት የራሱ የክብር ዘብ አለቃ አድርጎ ሾመው። 24  የኢዮዓብ ወንድም አሳሄል+ ከሠላሳዎቹ አንዱ ነበር፤ ከኃያላኑ ሰዎች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፦ የቤተልሔሙ+ የዶዶ ልጅ ኤልሃናን፣ 25  ሃሮዳዊው ሻማህ፣ ሃሮዳዊው ኤሊቃ፣ 26  ጳሌጣዊው ሄሌጽ፣+ የተቆአዊው የኢቄሽ ልጅ ኢራ፣+ 27  አናቶታዊው+ አቢዔዜር፣+ ሁሻዊው መቡናይ፣ 28  አሆሐያዊው ጻልሞን፣ ነጦፋዊው ማህራይ፣+ 29  የነጦፋዊው የባአናህ ልጅ ሄሌብ፣ ከቢንያማውያን የጊብዓው የሪባይ ልጅ ኢታይ፣ 30  ጲራቶናዊው በናያህ፣+ የጋአሽ+ ደረቅ ወንዞች* ሰው የሆነው ሂዳይ፣ 31  አርባዊው አቢዓልቦን፣ ባርሁማዊው አዝማዌት፣ 32  ሻአልቢማዊው ኤሊያህባ፣ የያሼን ልጆች፣ ዮናታን፣ 33  ሃራራዊው ሻማህ፣ የሃራራዊው የሻራር ልጅ አሂዓም፣ 34  የማአካታዊው ልጅ፣ የአሃስባይ ልጅ ኤሊፌሌት፣ የጊሎአዊው የአኪጦፌል+ ልጅ ኤሊያም፣ 35  ቀርሜሎሳዊው ሄጽሮ፣ ዓረባዊው ፓአራይ፣ 36  የጾባህዊው የናታን ልጅ ይግዓል፣ ጋዳዊው ባኒ፣ 37  አሞናዊው ጼሌቅ፣ የጽሩያ ልጅ የኢዮዓብ ጋሻ ጃግሬ በኤሮታዊው ናሃራይ፣ 38  ይትራዊው ኢራ፣ ይትራዊው+ ጋሬብ 39  እንዲሁም ሂታዊው ኦርዮ፤+ በአጠቃላይ 37 ነበሩ።

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “ተወዳጅ የሆነው።”
ወይም “መዳን አስገኘ።”
ወይም “መዳን አስገኘ።”
ወይም “ረባዳማ ሜዳ።”
ወይም “የድንኳን መንደርም።”
ወይም “ነፍሳቸውን።”
ቃል በቃል “የጀግና ልጅ።”