የዮሐንስ የመጀመሪያው ደብዳቤ 1:1-10

  • የሕይወት ቃል (1-4)

  • በብርሃን መመላለስ (5-7)

  • ኃጢአትን የመናዘዝ አስፈላጊነት (8-10)

1  ከመጀመሪያ የነበረውን፣ የሰማነውን፣ በዓይናችን ያየነውን፣ በትኩረት የተመለከትነውንና በእጃችን የዳሰስነውን የሕይወትን ቃል በተመለከተ እንጽፍላችኋለን፤+  (አዎ፣ ይህ ሕይወት ተገልጧል፤ እኛም አይተናል፤ ደግሞም እየመሠከርን ነው፤+ እንዲሁም በአብ ዘንድ የነበረውንና ለእኛ የተገለጠውን የዘላለም ሕይወት+ ለእናንተ እየነገርናችሁ ነው፤)  እናንተም ከእኛ ጋር ኅብረት እንዲኖራችሁ* ያየነውንና የሰማነውን ለእናንተም እየነገርናችሁ ነው።+ ደግሞም ይህ ኅብረታችን ከአብና ከልጁ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው።+  እነዚህን ነገሮች የምንጽፍላችሁ ደስታችን የተሟላ እንዲሆን ነው።  ከእሱ የሰማነውና ለእናንተ የምናሳውቀው መልእክት ይህ ነው፦ አምላክ ብርሃን ነው፤+ በእሱም ዘንድ* ጨለማ ፈጽሞ የለም።  “ከእሱ ጋር ኅብረት አለን” ብለን እየተናገርን በጨለማ የምንመላለስ ከሆነ እየዋሸን ነው፤ እውነትንም ሥራ ላይ እያዋልን አይደለም።+  ይሁን እንጂ እሱ ራሱ በብርሃን እንዳለ ሁሉ እኛም በብርሃን የምንመላለስ ከሆነ እርስ በርሳችን ኅብረት ይኖረናል፤ እንዲሁም የልጁ የኢየሱስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል።+  “ኃጢአት የለብንም” ብለን የምንናገር ከሆነ ራሳችንን እያታለልን ነው፤+ እውነትም በእኛ ውስጥ የለም።  ኃጢአታችንን የምንናዘዝ ከሆነ እሱ ታማኝና ጻድቅ ስለሆነ ኃጢአታችንን ይቅር ይለናል፤ እንዲሁም ከክፋት ሁሉ ያነጻናል።+ 10  “ኃጢአት አልሠራንም” ብለን የምንናገር ከሆነ እሱን ውሸታም እያደረግነው ነው፤ ቃሉም በውስጣችን የለም።

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “ተካፋይ እንድትሆኑ።”
ወይም “ከእሱም ጋር በተያያዘ።”