አንደኛ ዜና መዋዕል 9:1-44

  • ከግዞት የተመለሱት እስራኤላውያን የትውልድ ሐረግ (1-34)

  • የሳኦል የዘር ሐረግ በድጋሚ ተዘረዘረ (35-44)

9  እስራኤላውያን በሙሉ በየትውልድ ሐረጋቸው ተመዘገቡ፤ በእስራኤል ነገሥታት መጽሐፍም ላይ ተጻፉ። ይሁዳም ታማኝ ሆኖ ስላልተገኘ ወደ ባቢሎን በግዞት ተወሰደ።+  በከተሞቻቸው ወደሚገኙት ርስቶቻቸው የተመለሱት የመጀመሪያዎቹ ነዋሪዎች አንዳንድ እስራኤላውያን፣ ካህናቱ፣ ሌዋውያኑና የቤተ መቅደሱ አገልጋዮች ነበሩ።+  የተወሰኑ የይሁዳ፣+ የቢንያም፣+ የኤፍሬምና የምናሴ ዘሮች በኢየሩሳሌም ተቀመጡ፦  ከይሁዳ ልጅ፣ ከፋሬስ+ ዘሮች መካከል የባኒ ልጅ፣ የኢምሪ ልጅ፣ የኦምሪ ልጅ፣ የአሚሁድ ልጅ ዑታይ።  ከሴሎናውያንም የበኩር ልጅ የሆነው አሳያህ እና ወንዶች ልጆቹ።  ከዛራ ልጆች+ መካከል ደግሞ፣ የኡዔል እና 690 ወንድሞቻቸው ነበሩ።  በዚያ የተቀመጡት የቢንያም ዘሮችም የሚከተሉት ናቸው፦ የሃስኑአ ልጅ፣ የሆዳውያህ ልጅ፣ የመሹላም ልጅ ሳሉ፤  የየሮሃም ልጅ ይብኔያህ፣ የሚክሪ ልጅ፣ የዑዚ ልጅ ኤላህ፣ የይብኒያህ ልጅ፣ የረኡዔል ልጅ፣ የሰፋጥያህ ልጅ መሹላም።  በዘር ሐረጉ መዝገብ ላይ የሰፈሩት ወንድሞቻቸውም 956 ነበሩ። እነዚህ ሁሉ ወንዶች በየአባቶቻቸው ቤት መሪዎች ነበሩ። 10  ከካህናቱም የዳያህ፣ የሆያሪብ፣ ያኪን፣+ 11  የእውነተኛው አምላክ ቤት መሪ የሆነው የአኪጡብ ልጅ፣ የመራዮት ልጅ፣ የሳዶቅ ልጅ፣ የመሹላም ልጅ፣ የኬልቅያስ ልጅ አዛርያስ፣ 12  የማልኪያህ ልጅ፣ የጳስኮር ልጅ፣ የየሮሃም ልጅ አዳያህ፣ የኢሜር ልጅ፣ የመሺሌሚት ልጅ፣ የመሹላም ልጅ፣ የያህዜራ ልጅ፣ የአዲዔል ልጅ ማአሳይ፣ 13  እንዲሁም የየአባቶቻቸው ቤት መሪዎች የሆኑት ወንድሞቻቸው ነበሩ፤ እነሱም 1,760 ሲሆኑ ለእውነተኛው አምላክ ቤት አገልግሎት ዝግጁ የሆኑ ኃያላንና ብቁ ሰዎች ነበሩ። 14  ከሌዋውያኑም ከሜራሪ ዘሮች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፦ የሃሻብያህ ልጅ፣ የአዝሪቃም ልጅ፣ የሃሹብ ልጅ ሸማያህ፣+ 15  ባቅባቃር፣ ሄሬሽ፣ ጋላል፣ የአሳፍ ልጅ፣ የዚክሪ ልጅ፣ የሚካ ልጅ ማታንያህ፣ 16  የየዱቱን ልጅ፣ የጋላል ልጅ፣ የሸማያህ ልጅ አብድዩ እንዲሁም የሕልቃና ልጅ፣ የአሳ ልጅ ቤራክያህ። እሱም በነጦፋውያን+ ሰፈር ይኖር ነበር። 17  በር ጠባቂዎቹ+ ሻሉም፣ አቁብ፣ ታልሞን እና አሂማን ነበሩ፤ ወንድማቸው ሻሉምም መሪ ነበር፤ 18  እሱም እስከዚያን ጊዜ ድረስ በስተ ምሥራቅ በኩል በሚገኘው በንጉሡ በር ላይ ነበር።+ እነዚህ የሌዋውያንን ሰፈሮች የሚጠብቁ በር ጠባቂዎች ነበሩ። 19  የቆሬ ልጅ፣ የኤቢያሳፍ ልጅ፣ የቆረ ልጅ ሻሉም እና የአባቱ ቤት ወገን የሆኑት ወንድሞቹ ቆሬያውያን የድንኳኑ በር ጠባቂዎች በመሆን በዚያ የሚከናወነውን አገልግሎት በበላይነት ይቆጣጠሩ ነበር፤ አባቶቻቸው ደግሞ የመግቢያው ጠባቂዎች በመሆን የይሖዋን ሰፈር በበላይነት ይቆጣጠሩ ነበር። 20  ከዚህ በፊት የእነሱ መሪ የነበረው የአልዓዛር+ ልጅ ፊንሃስ+ ሲሆን ይሖዋም ከእሱ ጋር ነበር። 21  የመሺሌሚያህ ልጅ ዘካርያስ+ የመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ በር ጠባቂ ነበር። 22  በደጆቹ ላይ ቆመው እንዲጠብቁ የተመረጡት በአጠቃላይ 212 ነበሩ። እነሱም በትውልድ ሐረግ መዝገቡ ላይ ተጽፎ በሚገኘው መሠረት+ በሰፈሮቻቸው ውስጥ ይኖሩ ነበር። ዳዊትና ባለ ራእዩ+ ሳሙኤል እነዚህን ሰዎች ታማኝነት በሚጠይቀው ቦታ ላይ ሾሟቸው። 23  እነሱና ወንዶች ልጆቻቸው የይሖዋን ቤት ይኸውም የማደሪያ ድንኳኑን በሮች የመጠበቅ ኃላፊነት ተሰጥቷቸው ነበር።+ 24  በር ጠባቂዎቹ በአራቱም አቅጣጫዎች ማለትም በምሥራቅ፣ በምዕራብ፣ በሰሜንና በደቡብ በኩል ነበሩ።+ 25  በየሰፈሮቻቸው የሚኖሩት ወንድሞቻቸው ለሰባት ቀናት አብረዋቸው ለማገልገል አልፎ አልፎ ይመጡ ነበር። 26  ታማኝነት በሚጠይቀው ቦታ ላይ የሚያገለግሉ አራት የበር ጠባቂ አለቆች ነበሩ። እነሱም ሌዋውያን ሲሆኑ በእውነተኛው አምላክ ቤት የሚገኙትን ክፍሎችና ግምጃ ቤቶች የመጠበቅ ኃላፊነት ተሰጥቷቸው ነበር።+ 27  በእውነተኛው አምላክ ቤት ዙሪያ በተመደቡበት ቦታ ላይ ሆነው ያድሩ ነበር፤ የጥበቃውን ሥራ የሚያከናውኑት እንዲሁም ቁልፉ የተሰጣቸውና ቤቱን በየጠዋቱ የሚከፍቱት እነሱ ነበሩ። 28  ከእነሱ መካከል የተወሰኑት ለአገልግሎት የሚውሉትን ዕቃዎች የመቆጣጠር ኃላፊነት ነበረባቸው፤+ እነሱም ዕቃዎቹን በሚያስገቡበትም ሆነ በሚያወጡበት ጊዜ ይቆጥሯቸው ነበር። 29  የተወሰኑት ደግሞ ሌሎቹን ዕቃዎች፣ ቅዱስ የሆኑትን ዕቃዎች በሙሉ፣+ የላመውን ዱቄት፣+ የወይን ጠጁን፣+ ዘይቱን፣+ ነጭ ዕጣኑንና+ የበለሳን ዘይቱን+ እንዲቆጣጠሩ ተሹመው ነበር። 30  ከካህናቱ ልጆች መካከል አንዳንዶቹ የበለሳን ዘይት የተቀላቀለበት ቅባት ያዘጋጁ ነበር። 31  የቆሬያዊው የሻሉም የበኩር ልጅ የሆነው ሌዋዊው ማቲትያህ በምጣድ ላይ ከሚጋገሩት ነገሮች+ ጋር በተያያዘ ታማኝነት በሚጠይቀው ቦታ ላይ ተመድቦ ነበር። 32  ወንድሞቻቸው ከሆኑት ከቀዓታውያን አንዳንዶቹ የሚነባበረውን ዳቦ+ በየሰንበቱ የማዘጋጀት+ ኃላፊነት ነበራቸው። 33  እነዚህ የሌዋውያን አባቶች ቤት መሪዎች የሆኑ ዘማሪዎች ነበሩ፤ ከሌሎች ሥራዎች ነፃ እንዲሆኑ የተደረጉት እነዚህ ሰዎች በክፍሎቹ ውስጥ ይቀመጡ ነበር። ምክንያቱም ቀንም ሆነ ሌሊት በሥራቸው ላይ የመገኘት ኃላፊነት ነበረባቸው። 34  እነዚህ በትውልድ ሐረጉ መዝገብ ላይ እንደሰፈረው የሌዋውያን ቤተሰቦች መሪዎች ነበሩ። የሚኖሩትም በኢየሩሳሌም ነበር። 35  የገባኦን አባት የኢዔል በገባኦን+ ይኖር ነበር። የሚስቱ ስም ማአካ ይባል ነበር። 36  የበኩር ልጁ አብዶን ሲሆን ሌሎቹ ልጆቹ ደግሞ ጹር፣ ቂስ፣ ባአል፣ ኔር፣ ናዳብ፣ 37  ጌዶር፣ አሂዮ፣ ዘካርያስ እና ሚቅሎት ነበሩ። 38  ሚቅሎት ሺምአምን ወለደ። እነዚህ ሁሉ ከሌሎች ወንድሞቻቸው ጋር ሆነው በወንድሞቻቸው አቅራቢያ በኢየሩሳሌም ይኖሩ ነበር። 39  ኔር+ ቂስን ወለደ፤ ቂስ ሳኦልን+ ወለደ፤ ሳኦል ዮናታንን፣+ ሜልኪሳን፣+ አቢናዳብን+ እና ኤሽባዓልን ወለደ። 40  የዮናታን ልጅ መሪበኣል+ ነበር። መሪበኣል ሚክያስን ወለደ።+ 41  የሚክያስ ወንዶች ልጆች ፒቶን፣ ሜሌክ፣ ታህሬአ እና አካዝ ነበሩ። 42  አካዝ ያራን ወለደ፤ ያራ አለሜትን፣ አዝማዌትንና ዚምሪን ወለደ። ዚምሪ ሞጻን ወለደ። 43  ሞጻ ቢንአን ወለደ፤ ቢንአ ረፋያህን ወለደ፤ ረፋያህ ኤልዓሳን ወለደ፤ ኤልዓሳ አዜልን ወለደ። 44  አዜል ስድስት ወንዶች ልጆች የነበሩት ሲሆን ስማቸውም አዝሪቃም፣ ቦከሩ፣ እስማኤል፣ ሸአርያህ፣ አብድዩ እና ሃናን ነበር። እነዚህ የአዜል ወንዶች ልጆች ነበሩ።

የግርጌ ማስታወሻዎች