አንደኛ ዜና መዋዕል 3:1-24

  • የዳዊት ዘሮች (1-9)

  • የዳዊት የንግሥና መስመር (10-24)

3  ዳዊት በኬብሮን ሳለ የተወለዱለት ወንዶች ልጆች እነዚህ ናቸው፦+ የበኩር ልጁ አምኖን፤+ እናቱ ኢይዝራኤላዊቷ አኪኖዓም+ ነበረች፤ ሁለተኛው ልጁ ዳንኤል፤ እናቱ ቀርሜሎሳዊቷ አቢጋኤል+ ነበረች፤  የገሹር ንጉሥ የታልማይ ልጅ ከሆነችው ከማአካ የወለደው ሦስተኛው ልጁ አቢሴሎም፤+ ከሃጊት የወለደው አራተኛው ልጁ አዶንያስ፤+  አምስተኛው ልጁ ሰፋጥያህ፤ እናቱ አቢጣል ነበረች፤ ስድስተኛው ልጁ ይትረአም፤ እናቱ የዳዊት ሚስት ኤግላ ነበረች።  እነዚህ ስድስቱ በኬብሮን ሳለ የተወለዱለት ናቸው፤ በዚያም ለ7 ዓመት ከ6 ወር ነገሠ፤ በኢየሩሳሌም ደግሞ 33 ዓመት ነገሠ።+  በኢየሩሳሌም የተወለዱለት እነዚህ ናቸው፦+ ሺምአ፣ ሾባብ፣ ናታን+ እና ሰለሞን፤+ የእነዚህ የአራቱ ልጆች እናት የአሚዔል ልጅ ቤርሳቤህ+ ነበረች።  ሌሎቹ ዘጠኝ ወንዶች ልጆች ደግሞ ይብሃር፣ ኤሊሻማ፣ ኤሊፌሌት፣  ኖጋ፣ ኔፌግ፣ ያፊአ፣  ኤሊሻማ፣ ኤሊያዳ እና ኤሊፌሌት ናቸው።  ከቁባቶቹ ከወለዳቸው ወንዶች ልጆች ሌላ እነዚህ ሁሉ የዳዊት ወንዶች ልጆች ነበሩ፤ እህታቸውም ትዕማር+ ትባል ነበር። 10  የሰለሞን ልጅ ሮብዓም፣+ የሮብዓም ልጅ አቢያህ፣+ የአቢያህ ልጅ አሳ፣+ የአሳ ልጅ ኢዮሳፍጥ፣+ 11  የኢዮሳፍጥ ልጅ ኢዮራም፣+ የኢዮራም ልጅ አካዝያስ፣+ የአካዝያስ ልጅ ኢዮዓስ፣+ 12  የኢዮዓስ ልጅ አሜስያስ፣+ የአሜስያስ ልጅ አዛርያስ፣+ የአዛርያስ ልጅ ኢዮዓታም፣+ 13  የኢዮዓታም ልጅ አካዝ፣+ የአካዝ ልጅ ሕዝቅያስ፣+ የሕዝቅያስ ልጅ ምናሴ፣+ 14  የምናሴ ልጅ አምዖን፣+ የአምዖን ልጅ ኢዮስያስ።+ 15  የኢዮስያስ ወንዶች ልጆች የበኩር ልጁ ዮሃናን፣ ሁለተኛው ልጁ ኢዮዓቄም፣+ ሦስተኛው ልጁ ሴዴቅያስ+ እና አራተኛው ልጁ ሻሉም ነበሩ። 16  የኢዮዓቄም ወንዶች ልጆች ልጁ ኢኮንያን+ እና ልጁ ሴዴቅያስ ነበሩ። 17  የእስረኛው የኢኮንያን ወንዶች ልጆች ሰላትያል፣ 18  ማልኪራም፣ ፐዳያህ፣ ሸናጻር፣ የቃምያህ፣ ሆሻማ እና ነዳብያህ ነበሩ። 19  የፐዳያህ ወንዶች ልጆች ዘሩባቤል+ እና ሺምአይ ነበሩ፤ የዘሩባቤል ወንዶች ልጆችም መሹላም እና ሃናንያህ ነበሩ (ሸሎሚትም እህታቸው ነበረች)፤ 20  ሌሎቹ አምስት ወንዶች ልጆች ደግሞ ሃሹባ፣ ኦሄል፣ ቤራክያህ፣ ሃሳድያህ እና ዮሻብሄሴድ ነበሩ። 21  የሃናንያህ ወንዶች ልጆች ደግሞ ጰላጥያህ እና የሻያህ ነበሩ፤ የየሻያህ ልጅ ረፋያህ ነበር፤ የረፋያህ ልጅ አርናን ነበር፤ የአርናን ልጅ አብድዩ ነበር፤ የአብድዩ ልጅ ሸካንያህ ነበር፤ 22  የሸካንያህ ዘሮች ሸማያህና የሸማያህ ልጆች ናቸው፤ እነሱም ሃጡሽ፣ ይግዓል፣ ባሪያህ፣ ነአርያህ እና ሻፋጥ ሲሆኑ በአጠቃላይ ስድስት ነበሩ። 23  የነአርያህ ወንዶች ልጆች ኤሊዮዔናይ፣ ሂዝቅያህ እና አዝሪቃም ሲሆኑ በአጠቃላይ ሦስት ነበሩ። 24  የኤሊዮዔናይ ወንዶች ልጆች ደግሞ ሆዳውያህ፣ ኤልያሺብ፣ ፐላያህ፣ አቁብ፣ ዮሃናን፣ ደላያህ እና አናኒ ሲሆኑ በአጠቃላይ ሰባት ነበሩ።

የግርጌ ማስታወሻዎች