አንደኛ ዜና መዋዕል 18:1-17

  • ዳዊት የተቀዳጃቸው ድሎች (1-13)

  • የዳዊት አስተዳደር (14-17)

18  ከጊዜ በኋላም ዳዊት ፍልስጤማውያንን ድል በማድረግ በቁጥጥር ሥር አዋላቸው፤ ጌትንና+ በሥሯ ያሉትን ከተሞችም ከፍልስጤማውያን እጅ ወሰደ።+  ከዚያም ሞዓብን ድል አደረገ፤+ ሞዓባውያንም የዳዊት አገልጋዮች ሆኑ፤ ግብርም ገበሩለት።+  የጾባህ+ ንጉሥ ሃዳድኤዜር+ በኤፍራጥስ ወንዝ+ ላይ ያለውን የበላይነት ለማጠናከር በሄደ ጊዜ ዳዊት በሃማት+ አቅራቢያ ድል አደረገው።  ዳዊት ከእሱ ላይ 1,000 ሠረገሎች፣ 7,000 ፈረሰኞችና 20,000 እግረኛ ወታደሮች ማረከ።+ ከዚያም ዳዊት 100 የሠረገላ ፈረሶችን ብቻ አስቀርቶ ሌሎቹን በሙሉ ቋንጃቸውን ቆረጠ።+  የደማስቆዎቹ ሶርያውያን፣ የጾባህን ንጉሥ ሃዳድኤዜርን ለመርዳት በመጡ ጊዜ ዳዊት ከሶርያውያን መካከል 22,000 ሰዎችን ገደለ።+  ከዚያም ዳዊት በደማስቆ ሶርያ የጦር ሰፈሮች አቋቋመ፤ ሶርያውያንም የዳዊት አገልጋዮች ሆኑ፤ ግብርም ገበሩለት። ይሖዋ ዳዊትን በሄደበት ሁሉ ድል አቀዳጀው።+  በተጨማሪም ዳዊት ከሃዳድኤዜር አገልጋዮች ላይ ከወርቅ የተሠሩ ክብ ጋሻዎችን ወሰደ፤ ወደ ኢየሩሳሌምም አመጣቸው።  ዳዊት የሃዳድኤዜር ከተሞች ከሆኑት ከጢብሃትና ከኩን እጅግ ብዙ መዳብ ወሰደ። ሰለሞን የመዳቡን ባሕር፣+ ዓምዶቹንና የመዳብ ዕቃዎቹን የሠራው በዚህ ነበር።+  የሃማት ንጉሥ ቶዑ፣ ዳዊት የጾባህን ንጉሥ የሃዳድኤዜርን ሠራዊት በሙሉ ድል እንዳደረገ በሰማ ጊዜ+ 10  ደህንነቱን እንዲጠይቅና ከሃዳድኤዜር ጋር ተዋግቶ ድል በማድረጉ የተሰማውን ደስታ እንዲገልጽለት ልጁን ሃዶራምን ወዲያውኑ ወደ ንጉሥ ዳዊት ላከው (ሃዳድኤዜር ከቶዑ ጋር ብዙ ጊዜ ይዋጋ ነበርና)፤ እሱም ከወርቅ፣ ከብርና ከመዳብ የተሠሩ ብዙ ዓይነት ዕቃዎችን ይዞ መጣ። 11  ንጉሥ ዳዊት እነዚህን ዕቃዎች ከሁሉም ብሔራት ይኸውም ከኤዶም፣ ከሞዓብ፣ ከአሞናውያን፣+ ከፍልስጤማውያንና+ ከአማሌቃውያን+ ከማረከው ብርና ወርቅ ጋር ለይሖዋ ቀደሰ።+ 12  የጽሩያ ልጅ+ አቢሳ+ በጨው ሸለቆ 18,000 ኤዶማውያንን ገደለ።+ 13  እሱም በኤዶም የጦር ሰፈሮች አቋቋመ፤ ኤዶማውያንም ሁሉ የዳዊት አገልጋዮች ሆኑ።+ ይሖዋ ዳዊትን በሄደበት ሁሉ ድል አቀዳጀው።+ 14  ዳዊት በመላው እስራኤል ላይ መግዛቱን ቀጠለ፤+ ለሕዝቡም ሁሉ ፍትሕንና ጽድቅን አሰፈነላቸው።+ 15  የጽሩያ ልጅ ኢዮዓብ የሠራዊቱ አዛዥ ነበር፤+ የአሂሉድ ልጅ ኢዮሳፍጥ+ ታሪክ ጸሐፊ ነበር፤ 16  የአኪጡብ ልጅ ሳዶቅና የአብያታር ልጅ አሂሜሌክ ካህናት ነበሩ፤ ሻውሻ ደግሞ ጸሐፊ ነበር። 17  የዮዳሄ ልጅ በናያህ የከሪታውያንና+ የጴሌታውያን+ አዛዥ ነበር። የዳዊት ወንዶች ልጆችም ከንጉሡ ቀጥሎ ዋና ባለሥልጣናት ነበሩ።

የግርጌ ማስታወሻዎች