ለቆሮንቶስ ሰዎች የተጻፈ የመጀመሪያው ደብዳቤ 5:1-13
5 በመካከላችሁ የፆታ ብልግና*+ እንደተፈጸመ ይወራል፤ እንዲህ ዓይነቱ ብልግና* ደግሞ በአሕዛብ መካከል እንኳ ታይቶ አይታወቅም፤ ከአባቱ ሚስት ጋር የሚኖር ሰው አለ ተብሏል።+
2 ታዲያ በዚህ ትኩራራላችሁ? ይልቁንም በዚህ ማዘንና+ ድርጊቱን የፈጸመውን ሰው ከመካከላችሁ ማስወጣት አይገባችሁም?+
3 ምንም እንኳ እኔ በአካል ከእናንተ ጋር ባልሆንም በመንፈስ ከእናንተ ጋር ነኝ፤ ደግሞም እንዲህ ያለ ድርጊት በፈጸመው ሰው ላይ አብሬያችሁ ያለሁ ያህል ሆኜ ፈርጄበታለሁ።
4 በጌታችን በኢየሱስ ስም አንድ ላይ በምትሰበሰቡበት ጊዜ እኔም በጌታችን በኢየሱስ ኃይል በመንፈስ ከእናንተ ጋር እንደምሆን በመገንዘብ
5 እንዲህ ያለውን ሰው ለሰይጣን አሳልፋችሁ ልትሰጡት ይገባል፤+ ይህም እሱ በጉባኤው ላይ ያሳደረው መጥፎ ተጽዕኖ እንዲወገድና* የጉባኤው መንፈስ በጌታ ቀን ባለበት ሁኔታ እንዲቀጥል ነው።+
6 መመካታችሁ መልካም አይደለም። ጥቂት እርሾ ሊጡን ሁሉ እንደሚያቦካው አታውቁም?+
7 አዲስ ሊጥ እንድትሆኑ አሮጌውን እርሾ አስወግዱ፤ ምክንያቱም የፋሲካችን በግ+ የሆነው ክርስቶስ ስለተሠዋ+ ከእርሾ ነፃ ናችሁ።
8 ስለዚህ በዓሉን+ በአሮጌ እርሾ እንዲሁም በክፋትና በኃጢአት እርሾ ሳይሆን እርሾ በሌለበት በቅንነትና በእውነት ቂጣ እናክብር።
9 ከሴሰኞች* ጋር መግጠማችሁን እንድትተዉ* በደብዳቤዬ ላይ ጽፌላችሁ ነበር፤
10 እንዲህ ስል ግን በአጠቃላይ ከዚህ ዓለም+ ሴሰኞች፣* ስግብግብ ሰዎች፣ ቀማኞች ወይም ጣዖት አምላኪዎች ጋር አትገናኙ ማለቴ አይደለም። እንዲህ ቢሆንማ ኖሮ ጨርሶ ከዓለም መውጣት ያስፈልጋችሁ ነበር።+
11 አሁን ግን የጻፍኩላችሁ፣ ወንድም ተብሎ እየተጠራ ሴሰኛ* ወይም ስግብግብ+ ወይም ጣዖት አምላኪ ወይም ተሳዳቢ ወይም ሰካራም+ ወይም ቀማኛ+ ከሆነ ማንኛውም ሰው ጋር መግጠማችሁን እንድትተዉ*+ አልፎ ተርፎም እንዲህ ካለው ሰው ጋር ምግብ እንኳ እንዳትበሉ ነው።
12 በውጭ ባሉ* ሰዎች ላይ የምፈርደው እኔ ምን አግብቶኝ ነው? በውስጥ ባሉት ሰዎች ላይ እናንተ አትፈርዱም?
13 በውጭ ባሉት ላይ አምላክ ይፈርዳል።+ “ክፉውን ሰው ከመካከላችሁ አስወግዱት።”+
የግርጌ ማስታወሻዎች
^ ቃል በቃል “ሥጋው እንዲጠፋና።”
^ ወይም “እንዳትቀራረቡ።”
^ ወይም “እንዳትቀራረቡ።”
^ ወይም “የክርስቲያን ጉባኤ አባል ባልሆኑ።”