ዘካርያስ 9:1-17

  • በአጎራባች ብሔራት ላይ የተላለፈ የአምላክ ፍርድ (1-8)

  • የጽዮን ንጉሥ ይመጣል (9, 10)

    • ትሑት የሆነው ንጉሥ አህያ ላይ ተቀምጦ ይመጣል (9)

  • የይሖዋ ሕዝብ ነፃ ይወጣል (11-17)

9  የፍርድ መልእክት፦ “የይሖዋ ቃል በሃድራክ ምድር ላይ ነው፤ደማስቆንም ዒላማው* አድርጓል፤+የይሖዋ ዓይን በሰው ዘርናበእስራኤል ነገዶች ሁሉ ላይ ነውና፤+   አዋሳኟ የሆነችውን ሃማትንም+ ዒላማው አድርጓል፤ደግሞም እጅግ ጥበበኛ ቢሆኑም+ እንኳ ጢሮስንና+ ሲዶናን+ ዒላማው አድርጓል።   ጢሮስ የመከላከያ ግንብ* ገንብታለች። ብርን እንደ አቧራ፣ወርቅንም በመንገድ ላይ እንዳለ አፈር ቆልላለች።+  እነሆ፣ ይሖዋ ንብረቷን ይወስዳል፤ሠራዊቷንም ባሕሩ ውስጥ* ይደመስሳል፤+እሷም በእሳት ትበላለች።+   አስቀሎን ይህን አይታ ትፈራለች፤ጋዛ በጣም ትጨነቃለች፤ኤቅሮንም እንዲሁ ትሆናለች፤ ምክንያቱም ተስፋ የምታደርግባት ለኀፍረት ትዳረጋለች። ከጋዛ ንጉሥ ይጠፋል፤አስቀሎንም ሰው አልባ ትሆናለች።+   ዲቃላም በአሽዶድ ይቀመጣል፤እኔም የፍልስጤምን ኩራት አስወግዳለሁ።+   በደም የተበከሉትን ነገሮች ከአፉ፣አስጸያፊ የሆኑትንም ነገሮች ከጥርሱ መካከል አስወግዳለሁ፤ከእሱም የሚተርፈው ማንኛውም ሰው የአምላካችን ይሆናል፤እሱም በይሁዳ እንደ አለቃ፣*+ኤቅሮንም እንደ ኢያቡሳዊ ይሆናል።+   የሚገባም ሆነ የሚወጣ እንዳይኖር፣ቤቴን ለመጠበቅ በውጭ በኩል ድንኳን እተክላለሁ፤*+ከእንግዲህም ወዲህ በመካከላቸው የሚያልፍ አሠሪ* አይኖርም፤+አሁን በገዛ ዓይኔ አይቼዋለሁና።*   የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ፣ እጅግ ሐሴት አድርጊ። የኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ሆይ፣ በድል አድራጊነት ጩኺ። እነሆ፣ ንጉሥሽ ወደ አንቺ ይመጣል።+ እሱ ጻድቅ ነው፤ መዳንንም ያመጣል፤*ትሑት ነው፤+ ደግሞም በአህያ፣በአህያዪቱ ልጅ፣ በውርንጭላ* ላይ ይቀመጣል።+ 10  የጦር ሠረገላውን ከኤፍሬም፣ፈረሱንም ከኢየሩሳሌም እወስዳለሁ። የጦርነቱ ቀስት ይወሰዳል። እሱም ለብሔራት ሰላምን ያውጃል፤+ግዛቱም ከባሕር እስከ ባሕርእንዲሁም ከወንዙ* እስከ ምድር ዳርቻ ይሆናል።+ 11  አንቺ ሴት፣ በእኔና በአንቺ መካከል ካለው የደም ቃል ኪዳን የተነሳእስረኞችሽን ውኃ ከሌለበት ጉድጓድ አውጥቼ እልካቸዋለሁ።+ 12  እናንተ ተስፋ ያላችሁ እስረኞች ወደ ምሽጉ ተመለሱ።+ ዛሬ እንዲህ እልሻለሁ፦‘ድርሻሽን እጥፍ አድርጌ እከፍልሻለሁ።+ 13  ይሁዳን በእጄ እንዳለ ደጋን እወጥረዋለሁና።* ደጋኑን በኤፍሬም እሞላዋለሁ፤*ጽዮን ሆይ፣ ወንዶች ልጆችሽን እቀሰቅሳለሁ፤ግሪክ ሆይ፣ በወንዶች ልጆችሽ ላይ ይነሳሉ፤ጽዮን ሆይ፣ እንደ ተዋጊ ሰይፍም አደርግሻለሁ።’ 14  ይሖዋ በእነሱ ላይ ይገለጣል፤ፍላጻውም እንደ መብረቅ ይወነጨፋል። ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ቀንደ መለከት ይነፋል፤+እሱም ከደቡብ አውሎ ነፋሳት ጋር ይሄዳል። 15  የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ይከላከልላቸዋል፤እነሱም የሚወነጨፍባቸውን ድንጋይ ውጠው ያስቀራሉ፤ ደግሞም ያመክናሉ።+ ይጠጣሉ፤ የወይን ጠጅ እንደጠጣም ሰው ይንጫጫሉ፤እንዲሁም እንደ ሳህኖቹናእንደ መሠዊያው ማዕዘኖች የተሞሉ ይሆናሉ።+ 16  በዚያ ቀን አምላካቸው ይሖዋ፣እንደ ሕዝቡ መንጋ ያድናቸዋል፤+በአክሊል* ላይ እንዳሉ ፈርጦች በምድሩ ላይ ያብረቀርቃሉና።+ 17  ጥሩነቱ ምንኛ ታላቅ ነው!+ ውበቱስ እንዴት ያማረ ነው! እህል ወጣት ወንዶችን፣አዲስ የወይን ጠጅም ደናግሉን ያለመልማል።”+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ቃል በቃል “ማረፊያ ቦታው።”
ወይም “ምሽግ።”
“ባሕሩ ላይ” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ቃል በቃል “ሺክ።” የነገድ አለቃ የሆነ ሰው “ሺክ” ተብሎ ይጠራ ነበር።
ወይም “እንደ ጠባቂ ጦር እሰፍራለሁ።”
ወይም “ጨቋኝ።”
የሕዝቡን ጉስቁልና እንደተመለከተ መግለጹ ሳይሆን አይቀርም።
ወይም “ድል አድራጊም ነው፤ ደግሞም ድኗል።”
ወይም “በተባዕት አህያ።”
ኤፍራጥስን ያመለክታል።
ቃል በቃል “እረግጠዋለሁና።”
እንደ ፍላጻ አደርገዋለሁ ማለት ነው።
ወይም “በዘውድ።”