ዘኁልቁ 24:1-25

  • ሦስተኛው የበለዓም ምሳሌያዊ አነጋገር (1-11)

  • አራተኛው የበለዓም ምሳሌያዊ አነጋገር (12-25)

24  በለዓምም ይሖዋ እስራኤልን መባረክ እንደወደደ* ሲያይ ዳግመኛ ድግምት ፍለጋ አልሄደም፤+ ከዚህ ይልቅ ፊቱን ወደ ምድረ በዳ አቀና።  በለዓም አሻግሮ ሲመለከት እስራኤል በየነገዱ እንደሰፈረ አየ፤+ ከዚያም የአምላክ መንፈስ በእሱ ላይ ወረደ።+  በመሆኑም ይህን ምሳሌያዊ አባባል ተናገረ፦+ “የቢዖር ልጅ የበለዓም ቃል፣ዓይኑ የተከፈተው የዚያ ሰው ቃል፣   የአምላክን ቃል የሰማው፣ሁሉን ቻይ የሆነውን አምላክ ራእይ ያየውዓይኖቹ ሳይከደኑ የሰገደው ሰው ቃል ይህ ነው፦+   ያዕቆብ ሆይ፣ ድንኳኖችህ፣እስራኤል ሆይ፣ የማደሪያ ድንኳኖችህ እንዴት ያማሩ ናቸው!+   እንደ ሸለቆዎች፣*በወንዝም ዳር እንዳሉ የአትክልት ስፍራዎች በረጅሙ ተዘርግተዋል።+ይሖዋ እንደተከላቸው እሬቶች፣በውኃም ዳር እንዳሉ አርዘ ሊባኖሶች ሆነዋል።   ከሁለቱም አቁማዳዎቹ ውኃ ይንጠባጠባል፤ዘሩም በብዙ ውኃዎች አጠገብ ተዘርቷል።+ ንጉሡም+ ከአጋግ+ የላቀ ይሆናል፤መንግሥቱም ከፍ ከፍ ይላል።+   አምላክ ከግብፅ አወጣው፤ለእነሱ ልክ እንደ ጎሽ ቀንዶች ነው። የሚጨቁኑትን ብሔራት ይበላል፤+አጥንቶቻቸውንም ይቆረጣጥማል፤ በፍላጻዎቹም ያደቃቸዋል።   አድብቷል፤ እንደ አንበሳም ተጋድሟል፤እንደ አንበሳስ ማን ሊቀሰቅሰው ይደፍራል? አንተን የሚባርኩህ የተባረኩ ናቸው፤የሚረግሙህም የተረገሙ ናቸው።”+ 10  በዚህ ጊዜ ባላቅ በበለዓም ላይ በጣም ተቆጣ። ባላቅም በንቀት እጆቹን አጨብጭቦ በለዓምን እንዲህ አለው፦ “የጠራሁህ ጠላቶቼን እንድትረግምልኝ ነበር፤+ አንተ ግን ይኸው ሦስቱንም ጊዜ ባረክሃቸው እንጂ ምንም የፈየድከው ነገር የለም። 11  በል አሁን ቶሎ ብለህ ወደ ቤትህ ሂድ። እኔ እንኳ ታላቅ ክብር ላጎናጽፍህ አስቤ ነበር፤+ ይሖዋ ግን ክብር ነፈገህ።” 12  በለዓምም ለባላቅ እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “ወደ እኔ ለላክሃቸው መልእክተኞች እንዲህ ብዬ ነገሬአቸው አልነበረም? 13  ‘ባላቅ በብርና በወርቅ የተሞላውን ቤቱን ቢሰጠኝ እንኳ ከይሖዋ ትእዛዝ ውጭ በገዛ ፈቃዴ* መልካምም ሆነ መጥፎ ነገር ማድረግ አልችልም። እኔ የምናገረው ይሖዋ የሚነግረኝን ብቻ ነው።’+ 14  እንግዲህ አሁን ወደ ሕዝቤ ልሄድ ነው። ይልቅስ መጥተህ ወደፊት* ይህ ሕዝብ በሕዝብህ ላይ የሚያደርገውን ልንገርህ።” 15  ስለዚህ ይህን ምሳሌያዊ አባባል ተናገረ፦+ “የቢዖር ልጅ የበለዓም ቃል፣ዓይኑ የተከፈተው የዚያ ሰው ቃል፣+ 16  የአምላክን ቃል የሰማው፣የልዑሉን አምላክ እውቀት የሚያውቀው ሰው ቃል ይህ ነው፤ዓይኖቹ ሳይከደኑ እየሰገደ ሳለሁሉን ቻይ የሆነውን አምላክ ራእይ አየ፦ 17  አየዋለሁ፣ አሁን ግን አይደለም፤እመለከተዋለሁ፣ በቅርቡ ግን አይደለም። ኮከብ+ ከያዕቆብ ይወጣል፤በትረ መንግሥትም+ ከእስራኤል ይነሳል።+ የሞዓብን ግንባር፣*የሁከት ልጆችንም ሁሉ ራስ ቅል ይፈረካክሳል።+ 18  እስራኤል ጀግንነቱን ሲያሳይኤዶም ርስቱ ይሆናል፤+ሴይርም+ የጠላቶቹ ርስት ይሆናል።+ 19  ከያዕቆብም አንዱ ድል እያደረገ ይወጣል፤+የተረፉትንም የከተማዋን ነዋሪዎች ሁሉ ያጠፋል።” 20  አማሌቅንም ባየ ጊዜ እንዲህ ሲል ምሳሌያዊ አባባሉን መናገሩን ቀጠለ፦ “አማሌቅ ከብሔራት መካከል የመጀመሪያ ነበር፤+ሆኖም በመጨረሻ ይጠፋል።”+ 21  ቄናውያንንም+ ባየ ጊዜ እንዲህ ሲል ምሳሌያዊ አባባሉን መናገሩን ቀጠለ፦ “መኖሪያህ አስተማማኝ ነው፤ ጎጆህም በቋጥኝ ላይ የተሠራ ነው። 22  ሆኖም አንድ ሰው ቄይንን ያቃጥላታል። አሦር ማርኮ እስኪወስዳችሁ ድረስ ምን ያህል ትቆዩ ይሆን?” 23  እሱም እንዲህ ሲል ምሳሌያዊ አባባሉን መናገሩን ቀጠለ፦ “አቤት! አምላክ ይህን በሚያደርግበት ጊዜ ማን ይተርፍ ይሆን? 24  ከኪቲም+ የባሕር ዳርቻ መርከቦች ይመጣሉ፤አሦርንም ያጠቃሉ፤+ደግሞም ኤቤርን ያሠቃያሉ። ሆኖም እሱም ፈጽሞ ይጠፋል።” 25  ከዚያም በለዓም+ ተነስቶ ወደ ስፍራው ተመለሰ። ባላቅም መንገዱን ቀጠለ።

የግርጌ ማስታወሻዎች

ቃል በቃል “በይሖዋ ዓይን መልካም እንደሆነ።”
ወይም “ደረቅ ወንዞች።”
ቃል በቃል “ከልቤ አመንጭቼ።”
ወይም “በቀኖቹ መጨረሻ።”
ወይም “ሰሪሳራ።” በዓይንና በጆሮ መካከል ያለውን የአካል ክፍል ያመለክታል።