ዘኁልቁ 17:1-13

  • የአሮን በትር አበበች (1-13)

17  ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦  “እስራኤላውያንን አናግራቸው፤ ለእያንዳንዱ የአባቶች ቤት ከእያንዳንዱ የአባቶች ቤት አለቃ+ ላይ አንድ አንድ በትር ይኸውም በአጠቃላይ 12 በትሮችን ከእነሱ ላይ ውሰድ። የእያንዳንዳቸውንም ስም በየበትራቸው ላይ ጻፍ።  ለእያንዳንዱ የአባቶች ቤት መሪ የሚኖረው አንድ በትር ስለሆነ የአሮንን ስም በሌዊ በትር ላይ ጻፍ።  በትሮቹን ራሴን ዘወትር ለእናንተ በምገልጥበት+ በመገናኛ ድንኳኑ ውስጥ በምሥክሩ+ ፊት ለፊት አስቀምጣቸው።  ከዚያም እኔ የምመርጠው+ ሰው በትር ያቆጠቁጣል፤ እኔም እስራኤላውያን በእናንተ ላይ በማጉረምረም+ በእኔ ላይ እያሰሙ ያሉት ማጉረምረም+ እንዲያበቃ አደርጋለሁ።”  በመሆኑም ሙሴ እስራኤላውያንን አነጋገራቸው፤ አለቆቻቸውም በሙሉ በትሮቹን ይኸውም ለእያንዳንዱ የአባቶች ቤት አለቃ አንድ በትር ማለትም 12 በትሮችን ሰጡት፤ የአሮንም በትር ከእነሱ በትሮች ጋር ነበር።  ከዚያም ሙሴ በትሮቹን በምሥክሩ ድንኳን ውስጥ በይሖዋ ፊት አስቀመጣቸው።  በማግስቱም ሙሴ ወደ ምሥክሩ ድንኳን ሲገባ የሌዊን ቤት የሚወክለውን የአሮንን በትር አቆጥቁጦ፣ እንቡጥ አውጥቶ፣ አበባ አብቦና የደረሰ የአልሞንድ ፍሬ አፍርቶ አገኘው።  ከዚያም ሙሴ በትሮቹን በሙሉ ከይሖዋ ፊት አውጥቶ ወደ እስራኤል ሕዝብ ሁሉ አመጣቸው። እነሱም በትሮቹን አዩ፤ እያንዳንዱም ሰው የራሱን በትር ወሰደ። 10  ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ለዓመፀኞቹ ልጆች+ ምልክት ሆኖ እንዲያገለግል+ የአሮንን በትር+ መልሰህ ምሥክሩ ፊት አስቀምጠው፤ ይህም የሚሆነው በእኔ ላይ ማጉረምረማቸውን እንዲተዉና እንዳይሞቱ ነው።” 11  ሙሴም ወዲያውኑ ይሖዋ እንዳዘዘው አደረገ። ልክ እንደተባለውም አደረገ። 12  ከዚያም እስራኤላውያን ሙሴን እንዲህ አሉት፦ “እንግዲህ መሞታችን ነው፤ በቃ ማለቃችን ነው፤ ሁላችንም ማለቃችን ነው! 13  ወደ ይሖዋ የማደሪያ ድንኳን የሚቀርብ ማንኛውም ሰው ይሞታል!+ በቃ በዚህ መንገድ ሁላችንም መሞታችን ነው?”+

የግርጌ ማስታወሻዎች