ዕንባቆም 2:1-20

 • ‘የሚናገረውን ለማየት በንቃት እጠባበቃለሁ’ (1)

 • ይሖዋ ለነቢዩ የሰጠው መልስ (2-​20)

  • ‘ራእዩን በተስፋ ጠብቅ!’ (3)

  • ‘ጻድቅ በታማኝነቱ በሕይወት ይኖራል’ (4)

  • ለከለዳውያን የተነገሩ አምስት ወዮታዎች (6-20)

   • ምድር ይሖዋን በማወቅ ትሞላለች (14)

2  በጥበቃ ቦታዬ ላይ እሰየማለሁ፤+በመከላከያ ግንቧም ላይ እቆማለሁ። በእኔ አማካኝነት ምን መናገር እንደሚፈልግ ለማየትናበምወቀስበት ጊዜ ምን መልስ እንደምሰጥ ለማወቅ በንቃት እጠባበቃለሁ።   ይሖዋም እንዲህ ሲል መለሰልኝ፦ “ድምፁን ከፍ አድርጎ የሚያነበው ሰው በቀላሉ* እንዲያነበው+ራእዩን ጻፈው፤ በጽላትም ላይ ግልጽ በሆነ መንገድ ቅረጸው።+   ራእዩ የተወሰነለትን ጊዜ ገና ይጠብቃልና፤ወደ ፍጻሜውም ይቸኩላል፤ ደግሞም አይዋሽም። ቢዘገይ* እንኳ በተስፋ ጠብቀው!*+ ያላንዳች ጥርጥር ይፈጸማልና። ራእዩ አይዘገይም!   ኩሩ የሆነውን ተመልከት፤*ውስጡ ቀና አይደለም። ጻድቅ ግን በታማኝነቱ* በሕይወት ይኖራል።+   በእርግጥም የወይን ጠጅ አታላይ ስለሆነእብሪተኛው ሰው ግቡን አይመታም። ፍላጎቱን* እንደ መቃብር* ያሰፋል፤እሱ እንደ ሞት ነው፤ ደግሞም ሊጠግብ አይችልም። ብሔራትን ሁሉ ወደ ራሱ መሰብሰቡን ይቀጥላል፤ሕዝቦችንም ሁሉ ለራሱ ያከማቻል።+   እነዚህ ሁሉ ሰዎች በእሱ ላይ አይተርቱም? ደግሞስ አሽሙርና ግራ የሚያጋባ ቃል አይሰነዝሩም?+ እንዲህ ይላሉ፦‘የራሱ ያልሆነውን የሚያጋብስ፣ዕዳውንም የሚያበዛ ወዮለት! ይህን የሚያደርገው እስከ መቼ ነው?   አበዳሪዎችህ በድንገት አይነሱም? ተነስተው በኃይል ይነቀንቁሃል፤በእነሱም እጅ ለብዝበዛ ትዳረጋለህ።+   ብዙ ብሔራትን ስለዘረፍክከሕዝቦቹ መካከል የቀሩት ሁሉ ይዘርፉሃል፤+ምክንያቱም አንተ የሰው ልጆችን ደም አፍስሰሃል፤በምድሪቱ፣ በከተሞችናበዚያ በሚኖሩት ሁሉ ላይ ግፍ ፈጽመሃል።+   ከጥፋት እጅ ያመልጥ ዘንድጎጆውን ከፍ ባለ ቦታ ላይ ለመሥራትለቤቱ አግባብ ያልሆነ ጥቅም የሚሰበስብ ወዮለት! 10  በቤትህ ላይ አሳፋሪ ነገር አሲረሃል። ብዙ ሕዝቦችን ጠራርገህ በማጥፋት በራስህ* ላይ ኃጢአት ሠርተሃል።+ 11  ድንጋይ ከግንቡ ውስጥ ይጮኻል፤ከጣሪያው እንጨቶችም መካከል አንድ ወራጅ ይመልስለታል። 12  ከተማን ደም በማፍሰስ ለሚገነባናበዓመፅ ለሚመሠርታት ወዮለት! 13  እነሆ፣ ሰዎች እሳት ለሚበላው ነገር እንዲደክሙ፣ብሔራትም ከንቱ ለሆነ ነገር እንዲለፉ የሚያደርገው የሠራዊት ጌታ ይሖዋ አይደለም?+ 14  ውኃ ባሕርን እንደሚሸፍን፣ምድርም የይሖዋን ክብር በማወቅ ትሞላለችና።+ 15  እርቃናቸውን ለማየት ሲልታላቅ ቁጣውንና ንዴቱን ቀላቅሎለባልንጀሮቹ መጠጥ በመስጠት እንዲሰክሩ ለሚያደርግ ሰው ወዮለት! 16  በክብር ፋንታ ውርደት ትሞላለህ። አንተ ራስህም ጠጣ፤ ያልተገረዝክ መሆንህንም አሳይ።* በይሖዋ ቀኝ እጅ ያለው ጽዋ ወደ አንተ ይዞራል፤+ክብርህም በውርደት ይሸፈናል፤ 17  በሊባኖስ ላይ የተፈጸመው ግፍ ይሸፍንሃል፤አራዊትንም ያሸበረው ጥፋት በአንተ ላይ ይደርሳል፤ምክንያቱም አንተ የሰዎችን ደም አፍስሰሃል፤በምድር፣ በከተሞቿናበውስጧ በሚኖሩ ሁሉ ላይ ግፍ ፈጽመሃል።+ 18  የተቀረጸ ምስል፣ሠሪው የቀረጸው ከሆነ ምን ጥቅም አለው? ሠሪው እምነት ቢጥልበትም እንኳከብረት የተሠራ ሐውልትና* ሐሰትን የሚናገር አስተማሪ ምን ፋይዳ አለው?መናገር የማይችሉ ከንቱ አማልክት መሥራት ምን እርባና አለው?+ 19  እንጨቱን “ንቃ!” መናገር የማይችለውንም ድንጋይ “ተነስ! አስተምረን!” ለሚል ወዮለት! እነሆ፣ በወርቅና በብር ተለብጧል፤+በውስጡም እስትንፋስ የለም።+ 20  ይሖዋ ግን በቅዱስ ቤተ መቅደሱ ውስጥ ነው።+ ምድር ሁሉ በፊቱ ጸጥ በይ!’”+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “አቀላጥፎ።”
ወይም “የሚዘገይ ቢመስልም።”
ወይም “ቢዘገይ እንኳ በጉጉት ጠብቀው!”
ወይም “እነሆ፣ ነፍሱ በትዕቢት ተወጥራለች።”
“በእምነቱ” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “ነፍሱን።”
ወይም “ሲኦል።” የሰው ልጆችን ሁሉ መቃብር ያመለክታል። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ወይም “በነፍስህ።”
“ተንገዳገድም” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “ቀልጦ የተሠራ ሐውልትና።”