ለዕብራውያን የተጻፈ ደብዳቤ 8:1-13

  • ለሰማያዊ ነገሮች ጥላ የሆነ ድንኳን (1-6)

  • አሮጌውና አዲሱ ቃል ኪዳን ሲነጻጸሩ (7-13)

8  እንግዲህ የምንናገረው ነገር ዋና ነጥብ ይህ ነው፦ በሰማያት በግርማዊው ዙፋን ቀኝ የተቀመጠ+ እንዲህ ያለ ሊቀ ካህናት አለን፤+  እሱም የቅዱሱ ስፍራና*+ የእውነተኛው ድንኳን አገልጋይ* ነው፤ ይህም ድንኳን በሰው ሳይሆን በይሖዋ* የተተከለ ነው።  እያንዳንዱ ሊቀ ካህናት የሚሾመው ስጦታና መሥዋዕት ለማቅረብ ነውና፤ በመሆኑም ይሄኛው ሊቀ ካህናትም የሚያቀርበው ነገር ያስፈልገዋል።+  እሱ ምድር ላይ ቢሆን ኖሮ ካህን ባልሆነ ነበር፤+ ምክንያቱም ሕጉ በሚያዘው መሠረት ስጦታ የሚያቀርቡ ሰዎች አሉ።  እነዚህ ሰዎች ለሰማያዊ ነገሮች+ ዓይነተኛ አምሳያና ጥላ+ የሆነ ቅዱስ አገልግሎት ያቀርባሉ፤ ይህም የሆነው ሙሴ ድንኳኑን ለመሥራት በተዘጋጀ ጊዜ “በተራራው ላይ ተገልጦልህ ባየኸው ንድፍ መሠረት ሁሉንም ነገር በጥንቃቄ ሥራ” ተብሎ ከተሰጠው መለኮታዊ ትእዛዝ ጋር በሚስማማ ሁኔታ ነው።+  ይሁንና ኢየሱስ እጅግ የላቀ አገልግሎት* ተቀብሏል፤ ልክ እንደዚሁም ለተሻለ ቃል ኪዳን+ መካከለኛ ሆኗል፤+ ይህም ቃል ኪዳን በተሻሉ ተስፋዎች ላይ በሕግ የጸና ነው።+  የመጀመሪያው ቃል ኪዳን ምንም ጉድለት ባይኖረው ኖሮ ሁለተኛ ቃል ኪዳን ባላስፈለገ ነበር።+  አምላክ በሕዝቡ ላይ ጉድለት ስላገኘ እንዲህ ብሎ ተናግሯልና፦ “‘እነሆ፣ ከእስራኤል ቤትና ከይሁዳ ቤት ጋር አዲስ ቃል ኪዳን የምገባበት ጊዜ ይመጣል’ ይላል ይሖዋ።*  ‘ይህም ቃል ኪዳን አባቶቻቸውን እጃቸውን ይዤ ከግብፅ ምድር እየመራሁ ባወጣኋቸው ቀን+ ከእነሱ ጋር እንደገባሁት ዓይነት ቃል ኪዳን አይሆንም፤ ምክንያቱም እነሱ በቃል ኪዳኔ አልጸኑም፤ በመሆኑም ችላ አልኳቸው’ ይላል ይሖዋ።* 10  “‘ከዚያ ጊዜ በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነውና’ ይላል ይሖዋ።* ‘ሕግጋቴን በአእምሯቸው ውስጥ አኖራለሁ፤ በልባቸውም ላይ እጽፋቸዋለሁ።+ እኔም አምላካቸው እሆናለሁ፤ እነሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።+ 11  “‘እነሱም እያንዳንዳቸው የአገራቸውን ሰው፣ እያንዳንዳቸውም ወንድማቸውን “ይሖዋን* እወቅ!” ብለው ከእንግዲህ አያስተምሩም። ከትንሹ አንስቶ እስከ ትልቁ ድረስ ሁሉም ያውቁኛልና። 12  ለክፉ ሥራቸው ምሕረት አደርግላቸዋለሁና፤ ኃጢአታቸውንም ከእንግዲህ ወዲህ አላስታውስም።’”+ 13  “አዲስ ቃል ኪዳን” ሲል የቀድሞውን ቃል ኪዳን ጊዜ ያለፈበት አድርጎታል።+ ስለዚህ ጊዜ ያለፈበትና እያረጀ ያለው ቃል ኪዳን ሊጠፋ ተቃርቧል።+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ቅድስተ ቅዱሳኑን ያመለክታል።
ወይም “የሕዝብ አገልጋይ።”
ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።
ወይም “ሕዝባዊ አገልግሎት።”
ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።
ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።
ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።
ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።