ኤርምያስ 14:1-22

  • ድርቅ፣ ረሃብና ሰይፍ (1-12)

  • ሐሰተኛ ነቢያት ተወገዙ (13-18)

  • ኤርምያስ ሕዝቡ ኃጢአት መሥራቱን አምኖ ተቀበለ (19-22)

14  ድርቅን አስመልክቶ ወደ ኤርምያስ የመጣው የይሖዋ ቃል ይህ ነው፦+  2  ይሁዳ ታለቅሳለች፤+ በሮቿም ወላልቀዋል። በሐዘን ተውጠው መሬት ላይ ይቀመጣሉ፤ከኢየሩሳሌምም ጩኸት ይሰማል።  3  ጌቶቻቸውም አገልጋዮቻቸውን* ውኃ እንዲፈልጉ ላኳቸው። እነሱም ወደ ውኃ ጉድጓዶቹ* ሄዱ፤ ውኃ ግን አላገኙም። ባዶ ዕቃ ይዘው ተመለሱ። በኀፍረት ተዋጡ፤ ተስፋም ቆረጡ፤ራሳቸውንም ተከናነቡ።  4  በምድሪቱ ላይ ዝናብ ባለመዝነቡ የተነሳመሬቱ ስለተሰነጣጠቀ+ገበሬዎቹ እጅግ አዘኑ፤ ራሳቸውንም ተከናነቡ።  5  በሜዳ ያለች እንስት ርኤም* እንኳምንም ሣር ባለመኖሩ እንደወለደች ግልገሏን ጥላ ትሄዳለች።  6  የዱር አህዮች በተራቆቱ ኮረብቶች ላይ ይቆማሉ። እንደ ቀበሮ አየር አጥሯቸው ያለከልካሉ፤ምንም ዓይነት ተክል ባለመኖሩ ዓይኖቻቸው ፈዘዙ።+  7  ይሖዋ ሆይ፣ የገዛ ራሳችን በደል በእኛ ላይ የሚመሠክርብን ቢሆንምለስምህ ስትል እርምጃ ውሰድ።+ የክህደት ሥራችን በዝቷልና፤+ኃጢአት የሠራነውም በአንተ ላይ ነው።  8  አንተ የእስራኤል ተስፋ፣ በጭንቀትም ጊዜ አዳኙ+ የሆንክ ሆይ፣በምድሪቱ እንደ እንግዳ፣ሌሊቱን ለማሳለፍ ሲል ብቻ ጎራ እንዳለ መንገደኛ የሆንከው ለምንድን ነው?  9  ክው ብሎ እንደቀረ ሰው፣ማዳን እንደማይችል ኃያል ሰው የሆንከው ለምንድን ነው? ይሖዋ ሆይ፣ አንተ በመካከላችን ነህና፤+እኛም በስምህ ተጠርተናል።+ እባክህ አትተወን። 10  ይሖዋ ይህን ሕዝብ አስመልክቶ እንዲህ ይላል፦ “መቅበዝበዝ ይወዳሉ፤+ እግራቸውን አልሰበሰቡም።+ ስለዚህ ይሖዋ በእነሱ ደስ አይሰኝም።+ አሁን በደላቸውን ያስባል፤ በኃጢአታቸውም የተነሳ ተጠያቂ ያደርጋቸዋል።”+ 11  ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ “ይህ ሕዝብ መልካም ሁኔታ እንዲገጥመው አትጸልይ።+ 12  በሚጾሙበት ጊዜ የሚያቀርቡትን ልመና አልሰማም፤+ ሙሉ በሙሉ የሚቃጠሉ መባዎችና የእህል መባዎች በሚያቀርቡበት ጊዜም በእነሱ ደስ አልሰኝም፤+ በሰይፍ፣ በረሃብና በቸነፈር* አጠፋቸዋለሁና።”+ 13  በዚህ ጊዜ እንዲህ አልኩ፦ “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ ወዮ! እነሆ፣ ነቢያቱ ‘ሰይፍ አታዩም፤ ለረሃብም አትዳረጉም፤ ከዚህ ይልቅ በዚህ ስፍራ እውነተኛ ሰላም እሰጣችኋለሁ’ ይሏቸዋል።”+ 14  ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ “ነቢያቱ በስሜ የሐሰት ትንቢት ይናገራሉ።+ እኔ አልላክኋቸውም፤ አላዘዝኳቸውም ወይም አላናገርኳቸውም።+ የሐሰት ራእይን፣ ከንቱ የሆነ ሟርትንና የገዛ ልባቸውን ማታለያ ይተነብዩላችኋል።+ 15  ስለዚህ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እኔ ሳልካቸው በስሜ የሚተነብዩትና በዚህች ምድር ላይ ሰይፍም ሆነ ረሃብ አይከሰትም የሚሉት እነዚህ ነቢያት በሰይፍና በረሃብ ይጠፋሉ።+ 16  የሚተነብዩለትም ሕዝብ ከረሃቡና ከሰይፉ የተነሳ አስከሬኑ በኢየሩሳሌም ጎዳናዎች ላይ ይጣላል፤ እነሱን፣ አዎ እነሱን፣ ሚስቶቻቸውን፣ ወንዶች ልጆቻቸውንም ሆነ ሴቶች ልጆቻቸውን የሚቀብራቸው አይኖርም፤+ የሚገባቸውን ጥፋት በላያቸው ላይ አመጣለሁና።’+ 17  “ይህን ቃል ንገራቸው፦‘ዓይኖቼ ሌት ተቀን ሳያቋርጡ እንባ ያፍስሱ፤+ድንግሊቱ የሕዝቤ ሴት ልጅ እጅግ አስከፊ በሆነ ቁስል ሙሉ በሙሉ ደቃለችና፤ደግሞም ተሰብራለች።+ 18  ወደ መስክ ብወጣ፣እነሆ፣ በሰይፍ የተገደሉትን አያለሁ!+ ወደ ከተማም ብገባ፣በረሃብ የተነሳ የታመሙ ሰዎችን አያለሁ!+ ነቢዩና ካህኑ በማያውቁት አገር ተቅበዝብዘዋልና።’”+ 19  ይሁዳን ጨርሶ ትተኸዋል? ወይስ ጽዮንን ተጸይፈሃታል?*+ ታዲያ ፈውስ እስከማይገኝልን ድረስ የመታኸን ለምንድን ነው?+ ሰላምን ተስፋ አደረግን፤ ሆኖም መልካም ነገር አልመጣም፤የፈውስ ጊዜ ይመጣል ብለን ጠበቅን፤ ነገር ግን ሽብር ነገሠ!+ 20  ይሖዋ ሆይ፣ ክፋት መሥራታችንን፣አባቶቻችንም በደል መፈጸማቸውን አምነን እንቀበላለን፤በአንተ ላይ ኃጢአት ሠርተናልና።+ 21  ስለ ስምህ ስትል አትናቀን፤+ክብር የተላበሰውን ዙፋንህን አታቃልል። ከእኛ ጋር የገባኸውን ቃል ኪዳን አስታውስ፤ አታፍርሰውም።+ 22  ከንቱ ከሆኑት የአሕዛብ ጣዖቶች መካከል ዝናብ ሊያዘንብ የሚችል አለ?ሰማያትስ በራሳቸው ዝናብ ማውረድ ይችላሉ? አምላካችን ይሖዋ ሆይ፣ ይህን የምታደርገው አንተ ብቻ አይደለህም?+ እነዚህን ሁሉ ነገሮች ያደረግከው አንተ ብቻ ስለሆንክአንተን ተስፋ እናደርጋለን።

የግርጌ ማስታወሻዎች

^ ወይም “ታናናሾቻቸውን።”
^ ወይም “ወደ ቦዮቹ፤ ወደ ውኃ ማጠራቀሚያዎቹ።”
^ ቅርንጫፍ የሚመስሉ ቀንዶች ያሉት አጥቢ እንስሳ፤ ከአጋዘን ጋር ይመሳሰላል።
^ ወይም “በበሽታ።”
^ ወይም “ነፍስህ ተጸይፋታለች?”