ኢዮብ 30:1-31

  • ኢዮብ የደረሰበትን ሁኔታ ገለጸ (1-31)

    • የማይረቡ ሰዎች አፌዙበት (1-15)

    • አምላክ ምንም እየረዳው እንዳልሆነ ተሰምቶት ነበር (20, 21)

    • ‘ቆዳዬ ጠቆረ’ (30)

30  “አሁን ግን ከእኔ በዕድሜ የሚያንሱ፣በእኔ ላይ ይስቃሉ፤+አባቶቻቸው መንጋዬን ከሚጠብቁ ውሾች ጋር እንዲሆኑፈቃደኛ አልነበርኩም።  2  የእጃቸው ብርታት ለእኔ ምን ይፈይድልኝ ነበር? እነሱ ጉልበት ከድቷቸዋል።  3  ከችጋርና ከረሃብ የተነሳ ዝለዋል፤በወደመ እና ወና በሆነ ደረቅ ምድርያገኟትን ነገር ያላምጣሉ።  4  በቁጥቋጦዎች አጠገብ ያለውን ጨው ጨው የሚል ተክል ይሰበስባሉ፤ምግባቸው የክትክታ ዛፍ ሥር ነው።  5  ከማኅበረሰቡ ተባረዋል፤+ሰዎችም ሌባ ላይ እንደሚጮኹ ይጮኹባቸዋል።  6  በሸለቆዎች* ተዳፋት ላይ፣መሬት ላይ ባሉ ጉድጓዶች ውስጥና በዓለቶች መካከል ይኖራሉ።  7  ከቁጥቋጦዎች ውስጥ ይጮኻሉ፤በሳማዎችም መካከል ይከማቻሉ።  8  ማመዛዘን የጎደላቸውና የአልባሌ ሰዎች ልጆች ናቸው፤ከምድሪቱ ላይ ተባረዋል።*  9  አሁን ግን በዘፈኖቻቸው ሳይቀር ይሳለቁብኛል፤+የእነሱ መሳለቂያ* ሆኛለሁ።+ 10  ይጸየፉኛል፤ ከእኔም ርቀዋል፤+በፊቴ ከመትፋት ወደኋላ አይሉም።+ 11  ምክንያቱም አምላክ ትጥቅ አስፈትቶኛል፤* ደግሞም አዋርዶኛል፤እነሱ በፊቴ እንዳሻቸው ይሆናሉ።* 12  በቀኜ በኩል እንደ አድመኛ ተነስተውብኛል፤እንድሸሽ አድርገውኛል፤በመንገዴም ላይ ለጥፋት የሚዳርግ መሰናክል አስቀምጠዋል። 13  መንገዶቼን ያፈርሳሉ፤መከራዬንም ያባብሳሉ፤+የሚገታቸውም የለም።* 14  ሰፊ ክፍተት ባለው ቅጥር እንደሚመጣ ሰው መጡ፤በፍርስራሹ መካከል እየገሰገሱ ገቡ። 15  በሽብር ተዋጥኩ፤ክብሬ በነፋስ እንደሚወሰድ ተወስዷል፤የመዳን ተስፋዬም እንደ ደመና እልም ብሎ ጠፍቷል። 16  አሁን ሕይወቴ* ከውስጤ ተሟጠጠች፤+የጉስቁልና ዘመን+ ያዘኝ። 17  ከባድ ሕመም በሌሊት አጥንቶቼን ይበሳል፤*+የሚመዘምዘኝ ሥቃይ እረፍት አይሰጠኝም።+ 18  ልብሴ በታላቅ ኃይል ተበላሸ፤*እንደ ልብሴ አንገትጌ አንቆ ያዘኝ። 19  አምላክ ጭቃ ውስጥ ጥሎኛል፤አፈርና አመድ ሆንኩ። 20  እርዳታ ለማግኘት ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ አንተ ግን አትመልስልኝም፤+በፊትህ ቆምኩ፤ አንተ ግን ዝም ብለህ ታየኛለህ። 21  በጭካኔ በእኔ ላይ ተነሳህ፤+በእጅህ ብርታት አጠቃኸኝ። 22  ወደ ላይ አንስተህ በነፋስ ወሰድከኝ፤ከዚያም በአውሎ ነፋስ አንገላታኸኝ።* 23  በሕይወት ያለ ሁሉ ወደሚሰበሰብበት ቤት፣ወደ ሞት እንደምታወርደኝ አውቃለሁና። 24  ይሁንና የተሰበረ ሰው አደጋ ደርሶበት ለእርዳታ ሲጮኽ፣እጁን የሚያነሳበት ሰው አይኖርም።*+ 25  መከራ ላይ ለወደቁ ሰዎች* አላለቀስኩም? ለድሃውስ አላዘንኩም?*+ 26  መልካም ነገር በተስፋ ብጠባበቅም ክፉ ነገር ደረሰ፤ብርሃን ብጠባበቅም ጨለማ መጣ። 27  ውስጤ ያለማቋረጥ ተናወጠ፤የጉስቁልናም ዘመን መጣብኝ። 28  በሐዘን ተውጬ እመላለሳለሁ፤+ የፀሐይ ብርሃንም የለም። በጉባኤ መካከል ቆሜ እርዳታ ለማግኘት እጮኻለሁ። 29  የቀበሮዎች ወንድም፣የሰጎንም ሴቶች ልጆች ባልንጀራ ሆንኩ።+ 30  ቆዳዬ ጠቁሮ ተቀረፈ፤+ከሙቀቱ* የተነሳ አጥንቶቼ ነደዱ። 31  በገናዬ ለሐዘን ብቻ ዋለ፤ዋሽንቴም* ለለቅሶ ሆነ።

የግርጌ ማስታወሻዎች

^ ወይም “በደረቅ ወንዞች።”
^ ቃል በቃል “ተገርፈው (ተባረዋል)።”
^ ቃል በቃል “ምሳሌ፤ መተረቻ።”
^ ቃል በቃል “የደጋኔን አውታር አላልቶብኛል።”
^ ወይም “ልጓሙን ይፈታሉ።”
^ “የሚረዳቸው ሳይኖር መከራዬን ያባብሳሉ” ማለትም ሊሆን ይችላል።
^ ወይም “ነፍሴ።”
^ ቃል በቃል “በሌሊት አጥንቶቼ ተቦርቡረዋል።”
^ “የደረሰብኝ ከባድ መከራ ሰውነቴን አበላሸው” ማለትም ሊሆን ይችላል።
^ “በኃይል አላትመህ በታተንከኝ” ማለትም ሊሆን ይችላል።
^ ቃል በቃል “በፍርስራሽ ክምር (ላይ እጁን የሚያነሳ አይኖርም)።”
^ ወይም “የመከራ ቀን ለገጠማቸው ሰዎች።”
^ ወይም “ነፍሴስ ለድሃው አላዘነችም?”
^ “ከትኩሳቱ” ማለትም ሊሆን ይችላል።
^ ወይም “እምቢልታዬም።”