ኢዮብ 27:1-23

  • ኢዮብ ንጹሕ አቋሙን ለመጠበቅ ወሰነ (1-23)

    • “ንጹሕ አቋሜን አላጎድፍም!” (5)

    • አምላክ የለሽ ሰው ተስፋ የለውም (8)

    • “ንግግራችሁ ጨርሶ ባዶ የሆነው ለምንድን ነው?” (12)

    • ክፉዎች ባዷቸውን ይቀራሉ (13-23)

27  ኢዮብ ንግግሩን* በመቀጠል እንዲህ አለ፦   “ፍትሕ በነፈገኝ ሕያው በሆነው አምላክ፣+እንድመረር ባደረገኝ*+ ሁሉን ቻይ በሆነው አምላክ እምላለሁ፤   እስትንፋሴ በውስጤ፣ከአምላክ ያገኘሁትም መንፈስ በአፍንጫዬ ውስጥ እስካለ ድረስ፣+   ከንፈሮቼ ክፋት አይናገሩም፤ምላሴም ፈጽሞ የማታለያ ቃል አይወጣውም!   በእኔ በኩል እናንተን ጻድቅ አድርጎ መቁጠር የማይታሰብ ነገር ነው! እስክሞት ድረስ ንጹሕ አቋሜን* አላጎድፍም!*+   ጽድቄን አጥብቄ እይዛለሁ፤ ደግሞም ፈጽሞ አለቀውም፤+በሕይወት ዘመኔም ሁሉ* ልቤ አይኮንነኝም።*   ጠላቴ እንደ ክፉ ሰው ይሁን፤እኔን የሚያጠቁኝ ሰዎች እንደ ዓመፀኛ ይሁኑ።   አምላክ የለሽ የሆነ* ሰው ሲጠፋ፣አምላክ ሕይወቱን* ሲቀጨው ምን ተስፋ ይኖረዋል?+   መከራ ሲደርስበትአምላክ ጩኸቱን ይሰማዋል?+ 10  ወይስ ሁሉን ቻይ በሆነው አምላክ ደስ ይሰኛል? ሁልጊዜስ ወደ አምላክ ይጣራል? 11  እኔ ስለ አምላክ ኃይል* አስተምራችኋለሁ፤ሁሉን ቻይ ስለሆነው አምላክ ምንም የምደብቀው ነገር የለም። 12  ሁላችሁም ራእይ ካያችሁ፣ንግግራችሁ ጨርሶ ባዶ የሆነው ለምንድን ነው? 13  ክፉ ሰው ከአምላክ የሚያገኘው ድርሻ፣+ጨቋኞችም ሁሉን ቻይ ከሆነው አምላክ የሚወርሱት ውርሻ ይህ ነው። 14  ልጆቹ ቢበዙ በሰይፍ ይወድቃሉ፤+ዘሮቹም በቂ ምግብ አያገኙም። 15  ከእሱ በኋላ የተረፉት ወገኖቹ በመቅሰፍት ይቀበራሉ፤መበለቶቻቸውም አያለቅሱላቸውም። 16  ብርን እንደ አፈር ቢቆልል፣ልብስንም እንደ ሸክላ ጭቃ ቢያከማች እንኳ፣ 17  እሱ የሰበሰበውንጻድቁ ሰው ይለብሰዋል፤+ብሩንም ንጹሐን ይከፋፈሉታል። 18  የሚሠራው ቤት ብል እንደሠራው ሽፋን፣ጠባቂም እንደቀለሰው መጠለያ+ በቀላሉ የሚፈርስ ነው። 19  ባለጸጋ ሆኖ ይተኛል፤ ሆኖም ምንም የሚሰበስበው ነገር የለም፤ዓይኑን ሲገልጥ በዚያ ምንም ነገር አይኖርም። 20  ሽብር እንደ ጎርፍ ድንገት ያጥለቀልቀዋል፤አውሎ ነፋስ በሌሊት ይዞት ይሄዳል።+ 21  የምሥራቅ ነፋስ ይወስደዋል፤ እሱም አይገኝም፤ከቦታው ጠርጎ ይወስደዋል።+ 22  ከነፋሱ ኃይል ለማምለጥ ሲፍጨረጨር፣+ያለርኅራኄ ተወርውሮ ይመጣበታል።+ 23  እጁን ያጨበጭብበታል፤ደግሞም ካለበት ቦታ ሆኖ ያፏጭበታል።*+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ቃል በቃል “ምሳሌውን።”
ወይም “ነፍሴን መራራ ባደረጋት።”
ኢዮብ 2:9 ላይ የሚገኘውን የግርጌ ማስታወሻ ተመልከት።
ወይም “ከእኔ አላርቅም! እጠብቃለሁ!”
ወይም “ስለ የትኛውም ቀኔ።”
ወይም “አይዘልፈኝም።”
ወይም “ከሃዲ።”
ወይም “ነፍሱን።”
“በአምላክ እጅ” ማለትም ሊሆን ይችላል።
“እጃቸውን ያጨበጭቡበታል፤ እንዲሁም ካሉበት ቦታ ሆነው ያፏጩበታል” ማለትም ሊሆን ይችላል።