ኢዮብ 25:1-6

  • የበልዳዶስ ሦስተኛ ዙር ንግግር (1-6)

    • ‘‘ሰው በአምላክ ፊት እንዴት ንጹሕ ሊሆን ይችላል?’ (4)

    • ሰው ንጹሕ አቋሙን ቢጠብቅ ዋጋ እንደሌለው ተናገረ (5, 6)

25  ሹሃዊው በልዳዶስ+ እንዲህ ሲል መለሰ፦   “የመግዛት ሥልጣንና አስፈሪ ኃይል የእሱ ነው፤በሰማይ* ሰላምን ያሰፍናል።   የሠራዊቱ ብዛት ሊቆጠር ይችላል? የእሱ ብርሃን የማያበራበት ማን አለ?   ታዲያ ሟች የሆነ ሰው በአምላክ ፊት እንዴት ጻድቅ ሊሆን ይችላል?+ወይስ ከሴት የተወለደ ሰው እንዴት ንጹሕ* ሊሆን ይችላል?+   ጨረቃ እንኳ ብሩህ አይደለችም፤ከዋክብትም በእሱ ፊት ንጹሕ አይደሉም፤   እጭ የሆነው ሟች የሰው ልጅ፣ትል የሆነው ሰውማ ምንኛ የባሰ ይሆን!”

የግርጌ ማስታወሻዎች

ቃል በቃል “በከፍታዎቹ።”
ወይም “የጠራ።”