ኢዮብ 16:1-22

  • ኢዮብ የሰጠው መልስ (1-22)

    • “ሁላችሁም የምታስጨንቁ አጽናኞች ናችሁ!” (2)

    • አምላክ እሱን ዒላማ እንዳደረገው ተናገረ (12)

16  ኢዮብ እንዲህ ሲል መለሰ፦  2  “ከዚህ በፊት እንዲህ ያሉ ብዙ ነገሮች ሰምቻለሁ። ሁላችሁም የምታስጨንቁ አጽናኞች ናችሁ!+  3  ከንቱ* ቃላት ማብቂያ የላቸውም? እንዲህ ብለህ እንድትመልስ ያነሳሳህ ምንድን ነው?  4  እኔም እንደ እናንተ መናገር እችል ነበር። እናንተ በእኔ ቦታ ብትሆኑ ኖሮ፣*አሳማኝ በሆነ መንገድ ልናገራችሁ እችል ነበር፤በእናንተም ላይ ራሴን መነቅነቅ እችል ነበር።+  5  እንዲህ ከማድረግ ይልቅ በአፌ ቃል አበረታችሁ ነበር፤የከንፈሮቼም ማጽናኛ ባሳረፋችሁ ነበር።+  6  ብናገር ከሥቃዬ አልገላገልም፤+ዝም ብልስ ሥቃዬ ምን ያህል ይቀንስልኛል?  7  አሁን ግን አምላክ እንድዝል አድርጎኛል፤+መላ ቤተሰቤን* አጥፍቷል።  8  ደግሞም ያዝከኝ፤ ይህም ምሥክር ሆኖብኛል፤በመሆኑም ክሳቴ ተነስቶ በፊቴ ይመሠክራል።  9  ቁጣው ቦጫጨቀኝ፤ በጥላቻ ተመለከተኝ።+ ጥርሱን አፋጨብኝ። ባላጋራዬ በዓይኑ ወጋኝ።+ 10  እነሱ አፋቸውን በሰፊው ከፈቱብኝ፤+በንቀትም ጉንጬን አጮሉኝ፤ብዙ ሆነው በእኔ ላይ ተሰበሰቡ።+ 11  አምላክ ለልጆች አሳልፎ ሰጠኝ፤በክፉዎችም እጅ ላይ ገፍትሮ ጣለኝ።+ 12  ያለምንም ችግር እኖር ነበር፤ እሱ ግን ሰባበረኝ፤+ማጅራቴን ይዞ አደቀቀኝ፤ከዚያም ዒላማው አደረገኝ። 13  ቀስተኞቹ ከበቡኝ፤+ኩላሊቴን ወጋ፤+ ምንም ርኅራኄ አላሳየኝም፤ሐሞቴን መሬት ላይ አፈሰሰ። 14  እንደ ግንብ ሰንጥቆ ሰነጣጥቆ አፈራረሰኝ፤እንደ ተዋጊ ተንደርድሮ መጣብኝ። 15  ቆዳዬን ለመሸፈን ማቅ ሰፍቻለሁ፤+ክብሬንም* አፈር ውስጥ ቀብሬአለሁ።+ 16  ከለቅሶ የተነሳ ፊቴ ቀልቷል፤+ድቅድቅ ጨለማም* በዓይኖቼ ቆብ ላይ አጥልቷል፤ 17  ይሁንና እጆቼ ምንም ዓመፅ አልሠሩም፤ጸሎቴም ንጹሕ ነው። 18  ምድር ሆይ፣ ደሜን አትሸፍኚ!+ ጩኸቴም ማረፊያ ስፍራ አያግኝ! 19  አሁንም እንኳ ምሥክሬ በሰማያት አለ፤ስለ እኔ መመሥከር የሚችል በከፍታ ቦታዎች ላይ ይገኛል። 20  ጓደኞቼ በእኔ ላይ ያፌዛሉ፤+ዓይኔም ወደ አምላክ ያነባል።*+ 21  በሰውና በባልንጀራው መካከል የሚዳኝ እንደሚኖር፣በሰውና በአምላክ መካከልም የሚዳኝ ይኑር።+ 22  የሚቀሩት ዓመታት ጥቂት ናቸውና፤እኔም በማልመለስበት መንገድ እሄዳለሁ።+

የግርጌ ማስታወሻዎች

^ ወይም “እንደ ነፋስ ያሉ።”
^ ወይም “የእናንተ ነፍስ በእኔ ነፍስ ቦታ ብትሆን ኖሮ።”
^ ወይም “ከእኔ ጋር የሚሰበሰቡትን።”
^ ወይም “ብርታቴንም።” ቃል በቃል “ቀንዴንም።”
^ ወይም “የሞት ጥላም።”
^ “እንቅልፍ አጥቶ ይመለከታል” ማለትም ሊሆን ይችላል።