ኢዩኤል 3:1-21
3 “እነሆ፣ በዚያ ዘመንና በዚያ ጊዜየይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ምርኮኞች ስመልስ፣+
2 ብሔራትን ሁሉ ሰብስቤወደ ኢዮሳፍጥ* ሸለቆ* አወርዳቸዋለሁ።
ለሕዝቤና ርስቴ ለሆነው ለእስራኤል ስልበዚያ ከእነሱ ጋር እፋረዳለሁ፤+በብሔራት መካከል በትነዋቸዋልና፤ደግሞም ምድሬን ተከፋፍለዋታል።+
3 በሕዝቤ ላይ ዕጣ ይጣጣላሉና፤+ዝሙት አዳሪ ለማግኘት ሲሉ ወንድ ልጅን አሳልፈው ይሰጣሉ፤የወይን ጠጅ ለመጠጣት ሲሉም ሴት ልጅን ይሸጣሉ።
4 ጢሮስ፣ ሲዶና እና የፍልስጤም ግዛቶች ሁሉ፣ከእኔ ጋር ምን ጉዳይ አላችሁ?
ላደረግኩባችሁ ነገር ብድራት ልትመልሱልኝ ነው?
ብድራት የምትመልሱልኝ ከሆነብድራታችሁን ወዲያውኑ፣ በፍጥነት በራሳችሁ ላይ እመልሳለሁ።+
5 ምክንያቱም እናንተ ብሬንና ወርቄን ወስዳችኋል፤+እጅግ ምርጥ የሆነውን ውድ ንብረቴንም ወደ ቤተ መቅደሶቻችሁ አስገብታችኋል፤
6 ደግሞም ከምድራቸው ርቀው እንዲሄዱ ለማድረግ ስትሉየይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ሕዝብ ለግሪኮች ሸጣችሁ፤+
7 እነሆ፣ እነሱን ከሸጣችሁባቸው ቦታዎች እንዲመለሱ አነሳሳቸዋለሁ፤+ብድራታችሁንም በራሳችሁ ላይ እመልሳለሁ።
8 ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁን ለይሁዳ ሕዝብ እሸጣለሁ፤+እነሱም በሩቅ ላለ ብሔር ይኸውም ለሳባ ሰዎች ይሸጧቸዋል፤ይሖዋ ራሱ ይህን ተናግሯልና።
9 በብሔራት መካከል ይህን አውጁ፦+
‘ለጦርነት ተዘጋጁ!* ኃያላን ሰዎችን አነሳሱ!
ወታደሮቹ ሁሉ ቀርበው ጥቃት ይሰንዝሩ!+
10 ማረሻችሁን ሰይፍ፣ ማጭዳችሁንም ጦር ለማድረግ ቀጥቅጡ።
ደካማው ሰው “እኔ ብርቱ ነኝ” ይበል።
11 እናንተ ዙሪያውን ያላችሁ ብሔራት ሁሉ፣ ኑና ተረዳዱ፤ አንድ ላይም ተሰብሰቡ!’”+
ይሖዋ ሆይ፣ ኃያላንህን* ወደዚያ ቦታ አውርድ።
12 “ብሔራት ይነሱና ወደ ኢዮሳፍጥ ሸለቆ* ይምጡ፤ዙሪያውን ባሉት ብሔራት ሁሉ ላይ ለመፍረድ በዚያ እቀመጣለሁና።+
13 መከሩ ስለደረሰ ማጭድ ስደዱ።
የወይን መጭመቂያው ስለሞላ ኑ፣ ወርዳችሁ እርገጡ።+
ማጠራቀሚያዎቹ ሞልተው አፍስሰዋል፤ ክፋታቸው እጅግ በዝቷልና።
14 ብዙ ሕዝብ፣ በጣም ብዙ ሕዝብ የፍርድ ውሳኔ በሚሰጥበት ሸለቆ* ተሰብስቧል፤የፍርድ ውሳኔ በሚሰጥበት ሸለቆ* የይሖዋ ቀን ቀርቧልና።+
15 ፀሐይና ጨረቃ ይጨልማሉ፤ከዋክብትም ብርሃናቸውን አይሰጡም።
16 ይሖዋም ከጽዮን እንደ አንበሳ ያገሳል፤ከኢየሩሳሌም ድምፁን በኃይል ያሰማል።
ሰማይና ምድር ይናወጣሉ፤ይሖዋ ግን ለሕዝቡ መጠጊያ፣+ለእስራኤል ሕዝብ ምሽግ ይሆናል።
17 እናንተም እኔ በተቀደሰው ተራራዬ+ በጽዮን የምኖር አምላካችሁ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።
ኢየሩሳሌም ቅዱስ ስፍራ ትሆናለች፤+እንግዶችም* ከእንግዲህ በእሷ አያልፉም።+
18 በዚያ ቀን ተራሮቹ ጣፋጭ የወይን ጠጅ ያንጠባጥባሉ፤+ኮረብቶቹ ወተት ያፈሳሉ፤የይሁዳ ጅረቶችም ሁሉ በውኃ ይሞላሉ።
ከይሖዋም ቤት ምንጭ ይፈልቃል፤+የሺቲምንም* ሸለቆ* ያጠጣል።
19 ግብፅ ግን ባድማ ትሆናለች፤+ኤዶምም በምድራቸው ንጹሕ ደም በማፍሰስ+በይሁዳ ሕዝብ ላይ ግፍ ስለፈጸመች+ጠፍ ምድረ በዳ ትሆናለች።+
20 ይሁንና ይሁዳ ምንጊዜም፣ኢየሩሳሌምም ከትውልድ እስከ ትውልድ የሰው መኖሪያ ትሆናለች።+
21 ንጹሕ አድርጌ ያልቆጠርኩትን ደማቸውን* ንጹሕ አድርጌ እቆጥረዋለሁ፤+ይሖዋም በጽዮን ይኖራል።”+
የግርጌ ማስታወሻዎች
^ “ይሖዋ ፈራጅ ነው” የሚል ትርጉም አለው።
^ ወይም “ረባዳማ ሜዳ።”
^ ቃል በቃል “ጦርነትን ቀድሱ!”
^ ወይም “ይሖዋ ሆይ፣ ተዋጊዎችህን።”
^ ወይም “ረባዳማ ሜዳ።”
^ ወይም “ረባዳማ ሜዳ።”
^ ወይም “ረባዳማ ሜዳ።”
^ ወይም “ባዕዳንም።”
^ “የግራር ዛፎች” የሚል ትርጉም አለው።
^ ወይም “ደረቅ ወንዝ።”
^ ወይም “የደም ዕዳቸውን።”