ኢሳይያስ 64:1-12

  • የንስሐ ጸሎት ቀጣይ ክፍል (1-12)

    • ይሖዋ ሠሪያችን ነው (8)

64  በአንተ የተነሳ ተራሮች ይናወጡ ዘንድምነው ሰማያትን ቀደህ በወረድክ!   እሳት ጭራሮን አቀጣጥሎውኃን እንደሚያፈላ ሁሉ፣ያን ጊዜ ጠላቶችህ ስምህን ያውቃሉ፤ብሔራትም በፊትህ ይሸበራሉ!   እኛ ፈጽሞ ያልጠበቅናቸውን እጅግ አስደናቂ ነገሮች ባደረግክ ጊዜ፣+አንተ ወረድክ፤ ተራሮችም በፊትህ ተንቀጠቀጡ።+   ከጥንት ዘመን ጀምሮ፣ እሱን በተስፋ ለሚጠባበቁት* ሲል እርምጃ የወሰደከአንተ በቀር ሌላ አምላክ እንዳለ የሰማም ሆነ በጆሮው ያዳመጠወይም በዓይኑ ያየ ማንም የለም።+   ትክክል የሆነውን ነገር በደስታ ከሚያደርጉ፣+አንተን ከሚያስቡና መንገዶችህን ከሚከተሉ ሰዎች ጋር ተገናኝተሃል። እነሆ፣ ኃጢአት መሥራታችንን በቀጠልን ጊዜ ተቆጣህ፤+ይህን ያደረግነውም ለረጅም ጊዜ ነው። ታዲያ አሁን መዳን ይገባናል?   ሁላችንም እንደረከሰ ሰው ሆነናል፤የጽድቅ ሥራችንም ሁሉ እንደ ወር አበባ ጨርቅ ነው።+ ሁላችንም እንደ ቅጠል እንጠወልጋለን፤በደላችንም እንደ ነፋስ ጠራርጎ ይወስደናል።   ስምህን የሚጠራ የለም፤አንተን የሙጥኝ ብሎ ለመያዝ የሚነሳሳ የለም፤ፊትህን ከእኛ ሰውረሃልና፤+በበደላችን የተነሳ እንድንመነምን* አድርገኸናል።   አሁን ግን ይሖዋ ሆይ፣ አንተ አባታችን ነህ።+ እኛ ሸክላ ነን፤ አንተም ሠሪያችን ነህ፤*+ሁላችንም የእጅህ ሥራ ነን።   ይሖዋ ሆይ፣ እጅግ አትቆጣ፤+በደላችንንም ለዘላለም አታስታውስ። እባክህ ተመልከተን፤ እኛ ሁላችን ሕዝብህ ነንና። 10  የተቀደሱ ከተሞችህ ምድረ በዳ ሆነዋል። ጽዮን ምድረ በዳ፣ኢየሩሳሌምም ጠፍ ምድር ሆናለች።+ 11  አባቶቻችን አንተን ያወደሱበትየቅድስናና የክብር ቤታችን*በእሳት ተቃጥሏል፤+ከፍ አድርገን እንመለከታቸው የነበሩት ነገሮች በሙሉ ፈራርሰዋል። 12  ይሖዋ ሆይ፣ ይህ ሁሉ ሆኖ እያለ እርምጃ ከመውሰድ ትታቀባለህ? ዝም ብለህስ ታያለህ? ደግሞስ ከልክ በላይ እንድንጎሳቆል ትፈቅዳለህ?+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “እሱን በትዕግሥት ለሚጠባበቁት።”
ቃል በቃል “እንድንቀልጥ።”
ወይም “ያበጀኸንም አንተ ነህ።”
ወይም “የውበት ቤተ መቅደሳችን።”