ኢሳይያስ 63:1-19

  • ይሖዋ በብሔራት ላይ የሚወስደው የበቀል እርምጃ (1-6)

  • የይሖዋ ታማኝ ፍቅር (7-14)

  • የንስሐ ጸሎት (15-19)

63  ይህ ከኤዶም የሚመጣው፣+ደማቅ ቀለም ያለው* ልብስ ለብሶ ከቦስራ+ የሚገሰግሰው ማን ነው?ይህ እጅግ ያማረ ልብስ ለብሶናበታላቅ ኃይል ተሞልቶ የሚራመደው ማን ነው? “በጽድቅ የምናገር፣ለማዳን የሚያስችል ታላቅ ኃይል ያለኝ እኔ ነኝ።”  2  መጎናጸፊያህ የቀላውናልብሶችህ በመጭመቂያ ውስጥ ወይን እንደሚረግጥ ሰው ልብስ የሆኑት ለምንድን ነው?+  3  “በወይን መጭመቂያው ውስጥ ወይኑን ብቻዬን ረገጥኩ። ከሕዝቦች መካከል ከእኔ ጋር ማንም አልነበረም። በቁጣዬም ረጋገጥኳቸው፤በታላቅ ቁጣዬም ጨፈላለቅኳቸው።+ ደማቸውም ልብሶቼ ላይ ተረጨ፤ልብሴንም ሁሉ በከልኩ።  4  የምበቀልበት ቀን በልቤ ውስጥ ነውና፤+የምቤዥበትም ዓመት ደርሷል።  5  ተመለከትኩ፤ ሆኖም እርዳታ የሚሰጥ አልነበረም፤ማንም ድጋፍ ባለመስጠቱ ደነገጥኩ። ስለዚህ ክንዴ መዳን* አስገኘልኝ፤+የገዛ ቁጣዬም ድጋፍ ሆነልኝ።  6  ሕዝቦችን በቁጣዬ ረጋገጥኩ፤በታላቅ ቁጣዬም አሰከርኳቸው፤+ደማቸውንም በምድር ላይ አፈሰስኩ።”  7  ይሖዋ በምሕረቱና ታላቅ በሆነው ታማኝ ፍቅሩለእኛ ባደረገልን ነገሮች ሁሉ+ይኸውም ለእስራኤል ቤት ባደረጋቸው በርካታ መልካም ነገሮች የተነሳየይሖዋን የታማኝ ፍቅር መግለጫዎች፣ደግሞም ሊወደሱ የሚገባቸውን የይሖዋን ሥራዎች እናገራለሁ።  8  እሱ እንዲህ ብሏልና፦ “እነሱ በእርግጥ ሕዝቤ፣ የማይከዱ* ወንዶች ልጆች ናቸው።”+ ስለዚህ አዳኝ ሆነላቸው።+  9  በጭንቃቸው ሁሉ እሱ ተጨነቀ።+ የግል መልእክተኛውም* አዳናቸው።+ እሱ በፍቅሩና በርኅራኄው ተቤዣቸው፤+በቀድሞውም ዘመን ሁሉ አነሳቸው እንዲሁም ተሸከማቸው።+ 10  እነሱ ግን ዓመፁ፤+ ቅዱስ መንፈሱንም አሳዘኑ።+ በዚህ ጊዜ ጠላት ሆነባቸው፤+ደግሞም ተዋጋቸው።+ 11  እነሱም የጥንቱን ዘመን፣አገልጋዩ ሙሴ የኖረበትን ጊዜ አስታወሱ፦ “ከመንጋው እረኞች+ ጋር ከባሕሩ ያወጣቸው የት አለ?+ በእሱ ውስጥ ቅዱስ መንፈሱን ያኖረው፣+ 12  የከበረ ክንዱ ከሙሴ ቀኝ እጅ ጋር እንዲሄድ ያደረገው፣+ለራሱ ዘላለማዊ ስም ለማትረፍ+ውኃዎቹን በፊታቸው የከፈለው፣+ 13  አውላላ ሜዳ* ላይ እንዳለ ፈረስ፣በሚናወጡ ውኃዎች* መካከልሳይደናቀፉ እንዲሄዱ ያደረገው የት አለ? 14  የከብት መንጋ ወደ ሸለቋማ ሜዳ ሲወርድ እንደሚሆነው፣የይሖዋ መንፈስ አሳረፋቸው።”+ ለራስህ የከበረ* ስም ለማትረፍ ስትል+ሕዝብህን የመራኸው በዚህ መንገድ ነው። 15  ከሰማይ ተመልከት፤ከፍ ካለው የቅድስናና የክብር* መኖሪያህም ሆነህ እይ። ቅንዓትህና ታላቅ ኃይልህ፣የሚንሰፈሰፈው አንጀትህና+ ምሕረትህ የት አለ?+ እነዚህን ነገሮች ነፍገኸኛል። 16  አንተ አባታችን ነህና፤+አብርሃም ባያውቀን፣እስራኤልም ባያስታውሰን እንኳይሖዋ ሆይ፣ አንተ አባታችን ነህ። ስምህም ከጥንት ዘመን ጀምሮ “እኛን የተቤዠ” የሚል ነው።+ 17  ይሖዋ ሆይ፣ ከመንገዶችህ ወጥተን እንድንቅበዘበዝ የፈቀድከው* ለምንድን ነው? አንተን እንዳንፈራ ልባችን እንዲደነድን የፈቀድከው* ለምንድን ነው?+ ስለ አገልጋዮችህ፣ርስትህ ስለሆኑትም ነገዶች ስትል ተመለስ።+ 18  ቅዱስ ሕዝብህ ለጥቂት ጊዜ ወርሶት ነበር። ጠላቶቻችን መቅደስህን ረግጠዋል።+ 19  እኛ ለረጅም ጊዜ፣ ፈጽሞ እንዳልገዛኻቸው፣ጨርሶ በስምህ እንዳልተጠሩ ሰዎች ሆነናል።

የግርጌ ማስታወሻዎች

^ “ደማቅ ቀይ” ማለትም ሊሆን ይችላል።
^ ወይም “ድል።”
^ ወይም “የማይዋሹ።”
^ ወይም “በፊቱ ያለው መልአክም።”
^ ወይም “ምድረ በዳ።”
^ ወይም “በጥልቅ ውኃዎች።”
^ ወይም “ያማረ።”
^ ወይም “የውበት።”
^ ወይም “ያደረግከው።”
^ ቃል በቃል “ልባችንን ያደነደንከው።”