ኢሳይያስ 62:1-12

  • የጽዮን አዲስ ስም (1-12)

62  ጽድቋ እንደ ደማቅ ብርሃን እስኪፈነጥቅ፣+መዳኗም እንደ ችቦ እስኪቀጣጠል ድረስለጽዮን ስል ጸጥ አልልም፤+ለኢየሩሳሌምም ስል ዝም ብዬ አልቀመጥም።+  2  “አንቺ ሴት ሆይ፣+ ብሔራት ጽድቅሽን፣ነገሥታትም ሁሉ ክብርሽን ያያሉ።+ አንቺም የይሖዋ አፍ በሚያወጣልሽአዲስ ስም ትጠሪያለሽ።+  3  በይሖዋ እጅ የውበት ዘውድ፣በአምላክሽ መዳፍ የንጉሥ ጥምጥም ትሆኛለሽ።  4  ከእንግዲህ የተተወች ሴት አትባዪም፤+ምድርሽም ከእንግዲህ ባድማ ተብላ አትጠራም።+ ከዚህ ይልቅ “ደስታዬ በእሷ ነው” ተብለሽ ትጠሪያለሽ፤+ምድርሽም “ያገባች ሴት” ትባላለች። ይሖዋ በአንቺ ደስ ይለዋልና፤ምድርሽም እንዳገባች ሴት ትሆናለች።  5  አንድ ወጣት ድንግሊቱን እንደሚያገባ፣ወንዶች ልጆችሽ አንቺን ያገባሉ። አንድ ሙሽራ በሙሽራይቱ ሐሴት እንደሚያደርግ፣አምላክሽም በአንቺ ሐሴት ያደርጋል።+  6  ኢየሩሳሌም ሆይ፣ በቅጥሮችሽ ላይ ጠባቂዎች አቁሜአለሁ። ቀኑንም ሆነ ሌሊቱን በሙሉ፣ መቼም ቢሆን ዝም ሊሉ አይገባም። እናንተ ስለ ይሖዋ የምትናገሩ፣ፈጽሞ አትረፉ፤  7  ደግሞም ኢየሩሳሌምን አጽንቶ እስኪመሠርታት፣አዎ፣ የምድር ምስጋና እስኪያደርጋት ድረስ ምንም እረፍት አትስጡት።”+  8  ይሖዋ በቀኝ እጁ፣ ብርቱ በሆነውም ክንዱ እንዲህ ሲል ምሏል፦ “ከእንግዲህ እህልሽን ለጠላቶችሽ መብል እንዲሆን አልሰጥም፤የደከምሽበትንም አዲስ የወይን ጠጅ የባዕድ አገር ሰዎች አይጠጡትም።+  9  ሆኖም እህሉን፣ የሚሰበስቡት ሰዎች ይበሉታል፤ ይሖዋንም ያወድሳሉ፤ወይኑንም፣ የሚለቅሙት ሰዎች ቅዱስ በሆኑት ቅጥር ግቢዎቼ ውስጥ ይጠጡታል።”+ 10  በበሮቹ በኩል እለፉ፤ እለፉ። ለሕዝቡ መንገዱን ጥረጉ።+ ሥሩ፤ አውራ ጎዳናውን ሥሩ። ድንጋዮቹን አስወግዱ።+ ለሕዝቦችም ምልክት* አቁሙ።+ 11  እነሆ፣ ይሖዋ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ አውጇል፦ “ለጽዮን ሴት ልጅ‘እነሆ፣ መዳንሽ ቀርቧል።+ እነሆ፣ የሚከፍለው ወሮታ ከእሱ ጋር ነው፤የሚመልሰውም ብድራት በፊቱ አለ’ በሏት።”+ 12  ቅዱስ ሕዝብ፣ ይሖዋ የተቤዣቸው+ ተብለው ይጠራሉ፤አንቺም “እጅግ የምትፈለግ፣” “ያልተተወች ከተማ” ተብለሽ ትጠሪያለሽ።+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “ለምልክት የሚተከል ምሰሶ።”