ኢሳይያስ 51:1-23

  • ጽዮን ተመልሳ እንደ ኤደን የአትክልት ስፍራ ትሆናለች (1-8)

  • ጽዮንን የሠራው ኃያል አምላክ የተናገረው ማጽናኛ (9-16)

  • የይሖዋ የቁጣ ጽዋ (17-23)

51  “እናንተ ጽድቅን የምትከታተሉ፣ይሖዋንም የምትፈልጉ ስሙኝ። ተፈልፍላችሁ የወጣችሁበትን ዓለት፣ተቆፍራችሁ የወጣችሁበትንም ካባ ተመልከቱ።  2  አባታችሁን አብርሃምን፣የወለደቻችሁንም* ሣራን+ ተመልከቱ። እሱ በጠራሁት ጊዜ ብቻውን ነበርና፤+እኔም ባረክሁት፤ ደግሞም አበዛሁት።+  3  ይሖዋ ጽዮንን ያጽናናታልና።+ ፍርስራሾቿን ሁሉ ያጽናናል፤+ምድረ በዳዋንም እንደ ኤደን፣+በረሃማ ሜዳዋንም እንደ ይሖዋ የአትክልት ስፍራ ያደርጋል።+ በእሷም ውስጥ ሐሴትና ታላቅ ደስታእንዲሁም ምስጋናና ደስ የሚያሰኝ መዝሙር ይገኛሉ።+  4  ሕዝቤ ሆይ፣ በጥሞና አዳምጡኝ፤አንተም የእኔ ብሔር፣ ጆሮህን ስጠኝ።+ ሕግ ከእኔ ይወጣልና፤+የፍትሕ እርምጃዬም ለሕዝቦች እንደ ብርሃን ጸንቶ እንዲቆም አደርጋለሁ።+  5  ጽድቄ ቀርቧል።+ ማዳኔ ወደ እናንተ ይመጣል፤+ክንዴም በሕዝቦች ላይ ይፈርዳል።+ ደሴቶች በእኔ ተስፋ ያደርጋሉ፤+ክንዴንም* ይጠባበቃሉ።  6  ዓይኖቻችሁን ወደ ሰማያት አንሱ፤ወደታችም ወደ ምድር ተመልከቱ። ሰማያት እንደ ጭስ በነው ይጠፋሉና፤ምድርም እንደ ልብስ ታረጃለች፤ነዋሪዎቿም እንደ ትንኝ ይረግፋሉ። ማዳኔ ግን ለዘላለም ይኖራል፤+ጽድቄም ፈጽሞ አይከስምም።*+  7  እናንተ ጽድቅን የምታውቁ፣ሕጌንም* በልባችሁ ያኖራችሁ ሰዎች፣+ ስሙኝ። ሟች የሆኑ ሰዎች የሚሰነዝሩትን ትችት አትፍሩ፤ስድባቸውም አያሸብራችሁ።  8  ብል እንደ ልብስ ይበላቸዋልና፤የልብስ ብል* እንደ ሱፍ ጨርቅ ይበላቸዋል።+ ሆኖም ጽድቄ ለዘላለም፣ማዳኔም ከትውልድ እስከ ትውልድ ይኖራል።”+  9  የይሖዋ ክንድ ሆይ፣+ተነስ! ተነስ! ብርታትንም ልበስ! ከረጅም ጊዜ በፊት፣ በጥንቶቹ ትውልዶች ዘመን እንደሆነው ተነስ። ረዓብን*+ ያደቀከው፣ግዙፉንም የባሕር ፍጥረት የወጋኸው አንተ አይደለህም?+ 10  ባሕሩን፣ የተንጣለለውን የጥልቁን ውኃ ያደረቅከው አንተ አይደለህም?+ የተቤዠሃቸው ሰዎች እንዲሻገሩ ጥልቁን ባሕር መንገድ ያደረግከው አንተ አይደለህም?+ 11  ይሖዋ የዋጃቸው ይመለሳሉ።+ በእልልታ ወደ ጽዮን ይመጣሉ፤+ማብቂያ የሌለውንም ደስታ እንደ አክሊል ይጎናጸፋሉ።+ ሐሴት ያደርጋሉ፤ ታላቅ ደስታም ያገኛሉ፤ሐዘንና ሲቃም ከእነሱ ይሸሻሉ።+ 12  “የማጽናናችሁ እኔ ራሴ ነኝ።+ ሟች የሆነውን ሰው፣እንደ ሣርም የሚጠወልገውን የሰው ልጅ የምትፈሪው ለምንድን ነው?+ 13  ሰማያትን የዘረጋውንና+ የምድርን መሠረት የጣለውንሠሪህን ይሖዋን+ የምትረሳው ለምንድን ነው? ደግሞም ጨቋኙ* ሊያጠፋህ የተዘጋጀ ይመስልከእሱ ቁጣ የተነሳ ቀኑን ሙሉ በፍርሃት ተውጠህ ነበር። ታዲያ አሁን የጨቋኙ ቁጣ የት አለ? 14  በሰንሰለት ታስሮ ያጎነበሰው እስረኛ ቶሎ ይፈታል፤+ሞትን አያይም፤ ወደ ጉድጓድም አይወርድም፤የሚበላውም ነገር አያጣም። 15  ባሕሩን የማናውጥና ኃይለኛ ማዕበል የማስነሳ፣+እኔ ይሖዋ አምላክህ ነኝ፤ስሙ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ነው።+ 16  ሰማያትን እዘረጋና የምድርን መሠረት እጥል ዘንድ፣+ጽዮንንም ‘አንቺ ሕዝቤ ነሽ’+ እል ዘንድቃሌን በአፍህ አኖራለሁ፤በእጄም ጥላ እጋርድሃለሁ።+ 17  ከይሖዋ እጅ የቁጣውን ጽዋ የጠጣሽኢየሩሳሌም ሆይ፣ ተነሺ! ተነሺ! ቁሚ።+ ዋንጫውን ጠጥተሻል፤የሚያንገዳግደውን ጽዋ ጨልጠሻል።+ 18  ከወለደቻቸው ወንዶች ልጆች ሁሉ መካከል አንድም የሚመራት የለም፤ካሳደገቻቸውም ወንዶች ልጆች ሁሉ መካከል እጇን ይዞ የወሰዳት ማንም የለም። 19  እነዚህ ሁለት ነገሮች ደርሰውብሻል። ማን ያስተዛዝንሻል? ጥፋትና ውድመት እንዲሁም ረሃብና ሰይፍ መጥቶብሻል!+ ማንስ ያጽናናሻል?+ 20  ወንዶች ልጆችሽ ራሳቸውን ስተዋል።+ በመረብ እንደተያዘ የዱር በግበየመንገዱ ማዕዘን ላይ* ይተኛሉ። የይሖዋ ቁጣ፣ የአምላክሽም ተግሣጽ ሙሉ በሙሉ ወርዶባቸዋል።” 21  ስለዚህ አንቺ የተጎሳቆልሽና ያለወይን ጠጅ የሰከርሽ ሴት ሆይ፣እባክሽ ይህን ስሚ። 22  ለሕዝቡ የሚሟገተው ጌታሽና አምላክሽ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ የሚያንገዳግደውን ጽዋ፣+ ይኸውም ዋንጫውን፣የቁጣዬን ጽዋ ከእጅሽ እወስዳለሁ፤ከእንግዲህ ዳግመኛ አትጠጪም።+ 23  ጽዋውን ‘በላይሽ ላይ እንድንሻገር አጎንብሺልን!’ ባሉሽ፣*አንቺን በሚያሠቃዩት እጅ ላይ አደርገዋለሁ፤+ አንቺም ጀርባሽን እንደ መሬት፣እንደሚሄዱበትም መንገድ አደረግሽላቸው።”

የግርጌ ማስታወሻዎች

^ ወይም “አምጣ የወለደቻችሁንም።”
^ ወይም “ኃይሌንም።”
^ ወይም “አይንኮታኮትም።”
^ ወይም “መመሪያዬንም፤ ትምህርቴንም።”
^ “ትል” ማለትም ሊሆን ይችላል።
^ ወይም “እንዳትንቀሳቀስ ያገደህ።”
^ ቃል በቃል “በመንገዶቹ ሁሉ ራስ ላይ።”
^ ወይም “ነፍስሽን ‘በላይሽ ላይ እንድንሻገር አጎንብሺልን!’ ባሏት።”