ኢሳይያስ 50:1-11
50 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦
“እናታችሁን በሰደድኳት ጊዜ የፍቺ የምሥክር ወረቀት+ ሰጥቻታለሁ?
እናንተንስ የሸጥኳችሁ ለየትኛው አበዳሪዬ ነው?
እነሆ፣ የተሸጣችሁት በገዛ ጥፋታችሁ+ ነው፤እናታችሁም እንድትሄድ የተደረገው በገዛ በደላችሁ ነው።+
2 ታዲያ በመጣሁ ጊዜ እዚህ ማንም ያልነበረው ለምንድን ነው?
በተጣራሁስ ጊዜ የሚመልስ ሰው የጠፋው ለምንድን ነው?+
እጄ አጭር ሆና እናንተን መዋጀት ተስኗታል?ወይስ እናንተን ለመታደግ የሚያስችል ኃይል የለኝም?+
እነሆ፣ በተግሣጼ ባሕሩን አደርቃለሁ፤+ወንዞችን በረሃ አደርጋለሁ።+
ዓሣዎቻቸው ውኃ ባለማግኘታቸው ይበሰብሳሉ፤በውኃ ጥምም ይሞታሉ።
3 ሰማያትን ጨለማ አለብሳለሁ፤+ማቅንም መሸፈኛቸው አደርጋለሁ።”
4 ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ ለደከመው ትክክለኛውን ቃል በመናገርእንዴት መልስ* መስጠት እንደምችል አውቅ ዘንድ+ የተማሩ ሰዎችን አንደበት* ሰጥቶኛል።+
በየማለዳው ያነቃኛል፤እንደ ተማሪ አዳምጥ ዘንድ ጆሮዬን ያነቃል።+
5 ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ጆሮዬን ከፍቷል፤እኔም ዓመፀኛ አልነበርኩም።+
ጀርባዬን አልሰጠሁም።+
6 ለሚገርፉኝ ጀርባዬን፣ጢም ለሚነጩም ጉንጮቼን ሰጠሁ።
ፊቴን፣ ከሚያዋርዱ ነገሮችና ከትፋት አልሰወርኩም።+
7 ሆኖም ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ይረዳኛል።+
ስለዚህ አልዋረድም።
ከዚህም የተነሳ ፊቴን እንደ ባልጩት አደረግኩ፤+ለኀፍረት እንደማልዳረግም አውቃለሁ።
8 ጻድቅ መሆኔን የሚመሠክርልኝ ቀርቧል።
ታዲያ ማን ሊከሰኝ* ይችላል?+
በአንድነት እንቁም።*
ከእኔ ጋር ሙግት ያለው ማን ነው?
እስቲ ወደ እኔ ይቅረብ።
9 እነሆ፣ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ይረዳኛል።
ታዲያ ጥፋተኛ ነህ ሊለኝ የሚችል ማን ነው?
እነሆ፣ ሁሉም እንደ ልብስ ያረጃሉ።
ብል ይበላቸዋል።
10 ከመካከላችሁ ይሖዋን የሚፈራ፣የአገልጋዩንም ድምፅ የሚሰማ ማን ነው?+
ብርሃን በሌለበት በድቅድቅ ጨለማ የሄደ ማን ነው?
በይሖዋ ስም ይታመን፤ በአምላኩም ይደገፍ።*
11 “እነሆ፣ እናንተ እሳት የምታያይዙ፣የእሳት ፍንጣሪ የምታበሩ ሁሉ፣በእሳታችሁ ብርሃን፣ባያያዛችሁትም እሳት ብልጭታዎች መካከል ሂዱ።
ከእጄ የምትቀበሉት ይህ ነው፦
በከባድ ሥቃይ ትጋደማላችሁ።
የግርጌ ማስታወሻዎች
^ “ማበረታቻ” ማለትም ሊሆን ይችላል።
^ ወይም “በሚገባ የሠለጠነ አንደበት።”
^ ወይም “ሊሟገተኝ።”
^ ወይም “ፊት ለፊት እንጋጠም።”
^ ወይም “ይመካ።”