ኢሳይያስ 4:1-6

  • ሰባት ሴቶች ለአንድ ወንድ (1)

  • ይሖዋ እንዲያቆጠቁጥ ያደረገው ተክል ክብር የተላበሰ ይሆናል (2-6)

4  በዚያን ቀን ሰባት ሴቶች አንድን ወንድ ይዘው እንዲህ ይሉታል፦+ “የራሳችንን ምግብ እንበላለን፤የራሳችንንም ልብስ እንለብሳለን፤ብቻ በእኛ ላይ የደረሰው ውርደት* እንዲወገድ+በአንተ ስም እንድንጠራ ፍቀድልን።”  በዚያን ቀን፣ ይሖዋ እንዲያቆጠቁጥ ያደረገው ተክል ያማረና ክብር የተላበሰ ይሆናል፤ የምድሪቱም ፍሬ ከጥፋት ለተረፉት እስራኤላውያን የኩራት ምንጭና ውበት ይሆንላቸዋል።+  በጽዮን የቀሩትና በኢየሩሳሌም የተረፉት ሁሉ ይኸውም በኢየሩሳሌም እንዲኖሩ የተመዘገቡት በጠቅላላ ቅዱሳን ተብለው ይጠራሉ።+ 4  ይሖዋ በፍርድ መንፈስና በሚነድ* መንፈስ+ የጽዮንን ሴቶች ልጆች ቆሻሻ* አጥቦ ያስወግዳል፤+ የኢየሩሳሌምንም የደም ዕዳ ከመካከሏ አጥቦ ያነጻል፤  ያን ጊዜ ይሖዋ በመላው የጽዮን ተራራ ላይና በመሰብሰቢያ ቦታዋ ላይ በቀን ደመናና ጭስ፣ በሌሊት ደግሞ የሚንበለበል የእሳት ብርሃን ይፈጥራል፤+ እንዲሁም ክብራማ በሆነው ቦታ ሁሉ ላይ መጠለያ ይኖራል።  ደግሞም በቀን ካለው ንዳድ ጥላ+ እንዲሁም ከውሽንፍርና ከዝናብ መጠጊያና መሸሸጊያ+ የሚሆን ዳስ ይኖራል።

የግርጌ ማስታወሻዎች

አለማግባታቸውና ልጅ አለመውለዳቸው ያስከተለባቸውን ውርደት ያመለክታል።
ወይም “በሚያስወግድ።”
ቃል በቃል “እዳሪ።”