ኢሳይያስ 31:1-9

  • አስተማማኝ እርዳታ የሚገኘው ከሰው ሳይሆን ከአምላክ ነው (1-9)

    • የግብፅ ፈረሶች ሥጋ ናቸው (3)

31  እርዳታ ለማግኘት ወደ ግብፅ ለሚወርዱ፣+በፈረሶች ለሚመኩ፣+ብዛት ባላቸው የጦር ሠረገሎችናብርቱ በሆኑ የጦር ፈረሶች* ለሚታመኑ ወዮላቸው! ነገር ግን በእስራኤል ቅዱስ ተስፋ አያደርጉም፤ይሖዋንም አይሹም።   ይሁንና እሱም ጥበበኛ ነው፤ ጥፋትም ያመጣል፤ቃሉንም አያጥፍም። በክፉ አድራጊዎች ቤት ላይ፣እንዲሁም መጥፎ ነገር የሚሠሩ ሰዎችን በሚረዱ ላይ ይነሳል።+   ግብፃውያን ግን ተራ ሰዎች እንጂ አምላክ አይደሉም፤ፈረሶቻቸው ሥጋ እንጂ መንፈስ አይደሉም።+ ይሖዋ እጁን ሲዘረጋ፣እርዳታ የሚሰጥ ሁሉ ይሰናከላል፤እርዳታ ተቀባዩም ሁሉ ይወድቃል፤ሁሉም አንድ ላይ ይጠፋሉ።   ይሖዋ እንዲህ ብሎኛልና፦ “አንበሳ ይኸውም ደቦል አንበሳ ባደነው እንስሳ ላይ ቆሞ እንደሚያገሳ፣ብዙ እረኞች ተጠራርተው ሲመጡበትምጩኸታቸው እንደማያሸብረው፣የሚያሰሙትም ሁካታ እንደማያስፈራው ሁሉየሠራዊት ጌታ ይሖዋም ለጽዮን ተራራና ለኮረብታዋ ሲልለመዋጋት ይወርዳል።   ተወርውረው እንደሚወርዱ ወፎች፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋም እንዲሁ ኢየሩሳሌምን ይከልላታል።+ ይከልላታል፤ ደግሞም ያድናታል። ከአደጋ ያስጥላታል፤ እንዲሁም ይታደጋታል።”  “የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፣ እጅግ ወዳመፃችሁበት አምላክ ተመለሱ።+  በዚያ ቀን እያንዳንዱ ሰው በገዛ እጆቻችሁ በኃጢአት የሠራችኋቸውን የማይረቡ የብር አማልክቱንና ከንቱ የሆኑ የወርቅ አማልክቱን ያስወግዳልና።   አሦራዊውም የሰው ባልሆነ ሰይፍ ይወድቃል፤የሰው ያልሆነም ሰይፍ ይበላዋል።+ እሱም ሰይፉን ፈርቶ ይሸሻል፤ወጣቶቹም የግዳጅ ሥራ ይሠራሉ።   ቋጥኙ እጅግ ከመፍራቱ የተነሳ ደብዛው ይጠፋል፤መኳንንቱም ምልክት ሆኖ የሚያገለግለውን ምሰሶ ሲያዩ ይሸበራሉ” ይላልብርሃኑ* በጽዮን፣ እቶኑም በኢየሩሳሌም የሆነው ይሖዋ።

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “ፈረሰኞች።”
ወይም “እሳቱ።”