ኢሳይያስ 20:1-6

  • ለግብፅና ለኢትዮጵያ የተሰጠ የማስጠንቀቂያ ምልክት (1-6)

20  የአሦር ንጉሥ ሳርጎን የላከው ታርታን* ወደ አሽዶድ+ በመጣበት ዓመት አሽዶድን ወግቶ ያዛት።+  በዚያን ጊዜ ይሖዋ የአሞጽ ልጅ በሆነው በኢሳይያስ በኩል እንዲህ ሲል ተናገረ፦+ “ሂድ፣ ማቁን ከወገብህ ላይ አስወግድ፤ ጫማህንም ከእግርህ ላይ አውልቅ።” እሱም እንደተባለው አደረገ፤ ራቁቱንና* ባዶ እግሩንም ተመላለሰ።  ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለ፦ “አገልጋዬ ኢሳይያስ በግብፅና+ በኢትዮጵያ+ ላይ ለሚደርሰው ነገር ምልክትና+ ማስጠንቀቂያ እንዲሆን ለሦስት ዓመት ራቁቱንና ባዶ እግሩን እንደተመላለሰ ሁሉ፣  የአሦር ንጉሥም የግብፅን ምርኮኞችና+ የኢትዮጵያን ግዞተኞች፣ ልጆችንና ሽማግሌዎችን ሳይቀር መቀመጫቸውን ገልቦ ራቁታቸውንና ባዶ እግራቸውን እየነዳ ይወስዳቸዋል፤ የግብፅንም እርቃን ያጋልጣል።*  ተስፋቸውን በጣሉባት በኢትዮጵያና በሚኮሩባት* በግብፅ የተነሳ በፍርሃት ይርዳሉ፤ ብሎም ያፍራሉ።  በዚያም ቀን በዚህ የባሕር ዳርቻ የሚኖረው ሕዝብ ‘ተስፋ የጣልንበትን ይኸውም እርዳታ ለማግኘትና ከአሦር ንጉሥ ለመዳን የሸሸንበትን አገር ተመልከቱ! በዚህ ዓይነት እኛስ እንዴት እናመልጣለን?’ ማለቱ አይቀርም።”

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “የጦር አዛዥ።”
ወይም “ከውስጥ በለበሳት ልብስ ብቻና።”
ወይም “ደግሞም ግብፅን ያዋርዳል።”
ወይም “ውበቷን በሚያደንቁላት።”