ኢሳይያስ 18:1-7

  • ለኢትዮጵያ የተነገረ የማስጠንቀቂያ መልእክት (1-7)

18  በክንፋቸው ጥዝ የሚል ድምፅ የሚያሰሙ ጥቃቅን ነፍሳት ላሉባትበኢትዮጵያ ወንዞች አካባቢ ለምትገኝ ምድር ወዮላት!+   ይህች ምድር በባሕር ላይ፣በደንገል ጀልባ ውኃዎችን አቋርጠው የሚሄዱ መልእክተኞችን እንዲህ በማለት ትልካለች፦ “እናንተ ፈጣን መልእክተኞች፣ረጃጅም የሆኑና ለስላሳ ቆዳ ያላቸው ሰዎች ወደሚገኙበት ብሔር፣*ከቅርብም ሆነ ከሩቅ ወደሚፈራ ሕዝብ፣+ጥንካሬ ወዳለውና ድል አድራጊ ወደሆነው*እንዲሁም መሬቱ በወንዞች ተጠርጎ ወደተወሰደበት ብሔር ሂዱ።”   እናንተ በአገሪቱ የምትኖሩ ሁሉና እናንተ የምድር ነዋሪዎች ሁሉ፣በተራሮች ላይ እንደሚቆም ምልክት* ያለ ነገር ትመለከታላችሁ፤እንዲሁም ቀንደ መለከት ሲነፋ የሚሰማው ዓይነት ድምፅ ትሰማላችሁ።   ይሖዋ እንዲህ ብሎኛልና፦ “በቀን ብርሃን እንዳለ የሚያጥበረብር ሐሩር፣በመከርም ሙቀት እንዳለ የደመና ጠል፣ጸጥ ብዬ ተቀምጬ ጽኑ ሆኖ የተመሠረተውን ስፍራዬን* እመለከታለሁ።   ከመከር በፊት፣አበባው በሚረግፍበትና የወይን ፍሬው በሚበስልበት ጊዜቀንበጦቹ በማጭድ ይቆረጣሉና፤ሐረጎቹም ተቆርጠው ይወገዳሉ።   ሁሉም በተራሮች ላይ ላሉ አዳኝ አሞሮችናለምድር አራዊት ይተዋሉ። አዳኝ አሞሮቹም እነሱን በመመገብ በጋውን ያሳልፋሉ፤በምድር ላይ ያሉ አራዊትም ሁሉ እነሱን በመመገብ የመከሩን ወቅት ያሳልፋሉ።   በዚያን ጊዜ ረጃጅም የሆኑና ለስላሳ ቆዳ ያላቸው ሰዎች የሚገኙበት ብሔር፣*ከቅርብም ሆነ ከሩቅ የሚፈራው ሕዝብ፣ጥንካሬ ያለው፣ ድል አድራጊ የሆነውና*መሬቱ በወንዞች ተጠርጎ የተወሰደበት ብሔርለሠራዊት ጌታ ለይሖዋ ስጦታ ያመጣል፤ስጦታውንም የሚያመጣው የሠራዊት ጌታ የይሖዋ ስም ወዳለበት ወደ ጽዮን ተራራ+ ነው።”

የግርጌ ማስታወሻዎች

ቃል በቃል “ወደተመዘዘና ወደሚያብረቀርቅ ሕዝብ።”
ወይም “ሌሎችን ወደሚረግጥ ታላቅ ጥንካሬ ያለው ብሔር።”
ወይም “ለምልክት እንደሚተከል ምሰሶ።”
“ከተመሠረተው ስፍራዬ” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ቃል በቃል “የተመዘዘና የሚያብረቀርቅ ሕዝብ።”
ወይም “ሌሎችን የሚረግጥ ታላቅ ጥንካሬ ያለው ብሔርና።”