ኢሳይያስ 13:1-22
13 የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ+ በራእይ ያየው በባቢሎን ላይ የተላለፈ ፍርድ፦+
2 “በተራቆተ ዓለታማ ተራራ ላይ ምልክት* አቁሙ።+
ታላላቅ ሰዎች ወደሚገቡባቸው በሮች እንዲመጡድምፃችሁን ከፍ አድርጋችሁ ጥሯቸው፤ እጃችሁንም አውለብልቡ።
3 እኔ ለሾምኳቸው* ትእዛዝ ሰጥቻለሁ።+
ቁጣዬን ለመግለጥበኩራት ሐሴት የሚያደርጉትን ተዋጊዎቼን ጠርቻለሁ።
4 ስሙ! በተራሮች ላይ እንደ ታላቅ ሕዝብ ድምፅ ያለየብዙ ሰዎች ድምፅ ይሰማል!
አዳምጡ! አንድ ላይ የተሰበሰቡ መንግሥታትናብሔራት+ ሁካታ ይሰማል!
የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ሠራዊቱን ለጦርነት አሰልፏል።+
5 ይሖዋና የቁጣው መሣሪያዎችመላ ምድሪቱን ለመደምሰስ+ከሩቅ አገር፣+ከሰማያትም ዳርቻ እየመጡ ነው።
6 የይሖዋ ቀን ቀርቧልና ዋይ ዋይ በሉ!
በዚያ ቀን ሁሉን ቻይ ከሆነው አምላክ ዘንድ ጥፋት ይመጣል።+
7 ከዚህም የተነሳ እጆች ሁሉ ይዝላሉ፤የሰዎችም ልብ ሁሉ በፍርሃት ይቀልጣል።+
8 ሰዎቹ እጅግ ተሸብረዋል።+
ምጥ እንደያዛት ሴትብርክና ሥቃይ ይዟቸዋል።
እርስ በርሳቸው በታላቅ ድንጋጤ ይተያያሉ፤ፊታቸው በጭንቀት ቀልቷል።
9 እነሆ፣ የይሖዋ ቀን ምድሪቱን አስፈሪ ቦታ ለማድረግናበምድሪቱ ላይ ያሉትን ኃጢአተኞች ለማጥፋትበንዴትና በታላቅ ቁጣጨካኝ ሆኖ እየመጣ ነው።+
10 የሰማያት ከዋክብትና የኅብረ ከዋክብት ስብስቦቻቸው*+ብርሃን አይሰጡም፤ፀሐይ ስትወጣ ትጨልማለች፤ጨረቃም ብርሃኗን አትሰጥም።
11 ምድሪቱን ስለ ክፋቷ፣+ክፉዎችንም ስለ በደላቸው እቀጣለሁ።
የእብሪተኞችን ኩራት አጠፋለሁ፤የጨቋኞችንም ትዕቢት አዋርዳለሁ።+
12 ሟች የሆነውን ሰው ከጠራ ወርቅ፣ሰዎችንም ከኦፊር ወርቅ+ ይበልጥ ብርቅ አደርጋለሁ።+
13 ስለዚህ የሠራዊት ጌታ የይሖዋ ቁጣ በሚነድበት ቀን፣በታላቅ ቁጣ ሰማይን አናውጣለሁ፤ምድርንም ከቦታዋ አናጋለሁ።+
14 እንደሚታደን የሜዳ ፍየል፣ እረኛም እንደሌለው መንጋእያንዳንዱ ወደ ወገኑ ይመለሳል፤እያንዳንዱም ወደ አገሩ ይሸሻል።+
15 የተገኘ ሁሉ ይወጋል፤የተያዘም ሁሉ በሰይፍ ይወድቃል።+
16 ልጆቻቸው ዓይናቸው እያየ ይጨፈጨፋሉ፤+ቤታቸው ይዘረፋል፤ሚስቶቻቸውም ተገደው ይደፈራሉ።
17 እነሆ፣ ለብር ደንታ የሌላቸውን፣በወርቅም ደስ የማይሰኙትንሜዶናውያንን አስነሳባቸዋለሁ።+
18 ቀስታቸው ወጣቶችን ይፈጃል፤+ለማህፀን ፍሬ አያዝኑም፤ለልጆችም አይራሩም።
19 ከመንግሥታትም ሁሉ እጅግ የከበረችው፣*+የከለዳውያን ውበትና ኩራት የሆነችው ባቢሎን፣+አምላክ እንደገለበጣቸው እንደ ሰዶምና እንደ ገሞራ ትሆናለች።+
20 ከዚያ በኋላ የሚቀመጥባት አይኖርም፤እንዲሁም ከትውልድ እስከ ትውልድ ድረስ የመኖሪያ ቦታ አትሆንም።+
በዚያም ዓረብ ድንኳኑን አይተክልም፤እረኞችም መንጎቻቸውን በዚያ አያሳርፉም።
21 የበረሃ ፍጥረታት በዚያ ይተኛሉ፤ቤቶቻቸው በጉጉቶች ይሞላሉ።
ሰጎኖች በዚያ ይኖራሉ፤+የዱር ፍየሎችም* በዚያ ይፈነጫሉ።
22 የሚያላዝኑ ፍጥረታት በማማዎቿ፣ቀበሮዎችም በሚያማምሩ ቤተ መንግሥቶቿ ውስጥ ሆነው ይጮኻሉ።
ጊዜዋ ቀርቧል፤ ቀኖቿም አይራዘሙም።”+
የግርጌ ማስታወሻዎች
^ ወይም “ለምልክት የሚተከል ምሰሶ።”
^ ቃል በቃል “ለቅዱሳኔ።”
^ ቃል በቃል “የእነሱ ከሲል።” ኦርዮንንና በዙሪያው ያሉትን የኅብረ ከዋክብት ስብስቦች ሊያመለክት ይችላል።
^ ወይም “የመንግሥታት ጌጥ የሆነችው።”
^ “ፍየል የሚመስሉ አጋንንትም” ማለትም ሊሆን ይችላል።